የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ወላዴ አእላፍ መምህር የኔታ ሐረገ ወይን ምሕረቱ የሕይወት ታሪክ

March 11, 2023

ወላዴ አእላፍ መምህር የኔታ ሐረገ ወይን ምሕረቱ በወሎ ክፍለ ሀገር ሰገራት (ኩታበር ወደ ግሸን መሔጃ) ከወላጅ አባታቸው ከአለቃ ምሕረቱ ካሣ ከእናታቸወ ወ/ሮ አበቡ ወልደ ጻድቅ በየካቲት 16 ቀን 1916 ዓ.ም ተወለዱ። የፊደልና ንባብ ትምህርት የጀመሩት በእናታቸው ሀገር በቦሩ ሥላሴ ነው።

ግብረ ዲቁናን በ1935 ዓ.ም ከግብጻዊው አቡነ ቄርሎስ በአዲስ አበባ ቅድስት ማርያም ገዳም ተቀበሉ። ጸዋትወ ዜማ፣ ዳውንት፣ ምዕራፍ፣ ጾመ ድጓን የኔታ ሐረገ ወይን ቦሩ በድጋሚ ተመልሰው ተማሩ እርሳቸው እንደተናገሩት “ቦሩ እያለን አንድ ጓደኛችን ቅኔ ተቀኝቶ መጣ እኛም በቅንዓት ወደ ቅኔ ገባን” በማለት ገልጸው ነበረ፡፡

መምህራቸው ወደ ግሸን ሲሄዱ ተነስተው ደላንታ ጉርባ ጊዮርጊስ ከየኔታ ብሩ ድጋሚ ሙሉ ቅኔ ከነአገባቡ ተምረዋል ። የአቋቋም ትምህርት በጋይንት አንሳሳ ጊዮርጊስ የኔታ የማነ ብርሃን ክብረ በዓል እስከ አስተርእዮ ተማሩ። መምህሩ ወደ አማራ ሳይንት ሲሄዱ እርሳቸው በዚያው በመቅረት “አለቃ ታደሰ የሚባሉ መምህር መጡልን ሙሉ ክብረ በዓል አዘለቁን” ሲሉ ወላዴ አእላፍ መምህር የኔታ ሐረገ ወይን ገልጸዋል።

ጋይንት ልዳ ጊዮርጊስ በየኔታ ዓለሙ መዝሙሩን፣ ዝማሜና ማንሻውን፤ በበጌ ምድር መድኃኔ ዓለም በየኔታ አለልኝ መዝሙር፣ የመንና መረግዱን እንዲሁም ጽፈቱን ተምረዋል።

የኔታ ስለ አብነት ትምህርታቸው ሲተርኩ “ወገራ ቅዱስ ሚካኤል ሄድን ረሀብ ነበረ ተማሪ ተበትኖ ስለአገኘነው ወደ በለሳ ላኩን፡፡ በለሳ መድኃኔ ዓለም የኔታ አፈ ወርቅ የጎንደር ማርያም አለቃ ናቸው ከእኚህ ሊቅ መዝሙርና ክብረ በዓል ከለስን፣ በዞዝ አምባ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከየኔታ እፁብ ክብረ በዓል፣ ወርሃ በዓል መዝሙር ከነዓመሉ የወሰንነው እዛው ነው። (አንድ ደቀ መዝሙር ወደ ምስክር ከመሔዱ በፊት የወሰነ ከሆነ አድራሽ ይባላል አድራሽ የሆንነው እዛው ነው) ” በማለት ይነገሩ ነበር።

የኔታ ትምህርታቸውን ቀጥለው ድምጫ ላይ ቤት፣ ታች ቤት፣ ሳንኳ ፊት ሚካኤል ወይም አደባባይ ኢየሱስ /በዓታ/ቂርቆስ እስከ ሦስት ዓመት አጠናክረዋል።

ስለ መምህርነት ሕይወታቸው ሲናገሩ “የኔታ እፁብ መረቁኝ አስተምር ብለው ፈቀዱልኝ የመጀመሪያ የማስተማር ጊዜ በጎንደር ክፍለ ሀገር በበለሳ በታች አባሽካ ጊዮርጊስ በ1940 ማስተማር ጀመርኩ። 7 ዓመት አስተማርኩ፡፡ በመቀጠልም በጣራሽ ማርያም 8 ዓመት አስተምሬ ቤተሰብ ለመጠየቅ ወደ አዲስ አበባ መጣሁ። እዚሁ ተቀመጥ አሉኝ አክስቴ ባይሆን ተማሪዎቼን አሰናብቼ እኔም ተሰናብቼ ልምጣ ብዬ ተመልሼ ሂጄ ተማሪዎቼን ሸኝቼ ተመለስኩ” በማለት ወደ አዲስ አበባ የመጡበትን አጋጣሚ ይተርካሉ።

አዲስ አበባ እንደመጡ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ተቀጠሩ ከዚያም ኮልፌ ትምህርት ቤት በመግባት ሰባት ዓመት ሐዲስ ኪዳን ተማሩ፣ በዘመናዊ ትምህርትም እስከ ዘጠነኛ ክፍል ዘልቀዋል፡፡

ታላቁ አባት የኔታ ሐረገ ወይን ምሕረቱ በኤሊባቡር የሀገረ ስብከቱ ስብከተ ወንጌል ኃላፊና አቡነ ቀሲስ የሊቀ ጳጳሱ እንደ ራሴ ሆነው ለ2 ዓመት አገልግሎት ሰጥተዋል ። ቤተ ክህነቱ ጋሞ ጎፋ ጅንካ መድቧቸው ወደ ጋሞ ጎፋ በመሄድ አቡነ ሰላማ ዘንድ የሀገረ ስብከቱ ትምህርት ክፍል ሰባኬ ወንጌል ሆነው 10 ዓመት አገልግለዋል ።

አርባ ምንጭ እያሉ ብፁዕ አቡነ ሰላማ ወደ ደብረ ሊባኖስ ልከዋቸው በደብረ ሊባኖስ ገዳም መንኩስናን ተቀብለዋል።
ታላቁ አባት የኔታ ሐረገ ወይን ምሕረቱ በአዲስ አበባ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጸሐፊ ሆነው 1 ዓመት ሠርተዋል።
የመንበረ ፓትርያርክ የጊቢ ኃላፊ በመሆን በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጊዜ 4 ዓመት አገልግሎት ተሰጥተዋል።

ወደ ኬንያ ናይሮቢ በማቅናት በመድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን የስብከተ ወንጌል ኃላፊ ሆነው ከብፁዕ አቡነ ኤልያስ ጋር ሠርተዋል። ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ወደ ጅቡቲ ሲሄዱ የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ ሆነው አንድ ዓመት አገልግለዋል ።

የኔታ ሐረገ ወይን ምሕረቱ ወደ ዝዋይ ያቀኑበትን አጋጣሚ ሲገልጹ “አቡነ ጎርጎርዮስ አገኙኝ ሹመት ይፈልጋሉ ወይ አሉኝ? እኔም ኧረ አልፈልግም መምህራችን ሹመት የሚባል ነገር እንዳትፈልጉ ብለውኛል አልኳቸው፡፡ ማስተማር የሚፈልጉ ከሆነ ዝዋይ እንሂድ ብለውኝ በ1980 ዓ.ም ወደ ገዳሙ ገባሁ በማለት ገልጸዋል።

ይህንን የሕይወት ታሪካቸውን የከተቡት አባ አትናቴዎስ ወልደ ጎርጎርዮስ እንደገለጹት የኔታ ወደ ዝዋይ ገዳም ከመጡ ጀምሮ ወዴትም አልሔዱም የገዳሙ በረከት ናቸው። በዝዋይ ገዳም ብቻ በዓት አጽንተው 35 ዓመት አስተምረዋል ብለዋል።

የታላቁ አባት የኔታ ሐረገ ወይን ምሕረቱ በእርግና ምክንያት በ99 ዓመታቸው መጋቢት 1ቀን 2015 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

በረከታቸው ይደርብን።

Search Search

Recent Posts

  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ለቤተ ክርስቲያኗ ከፍተኛ መሪዎች «የእንኳን አደረሳችሁ» ስጦታ አበረከተ።
  • የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ተምሮ ማስተማር ሰንበት ትምህርት ቤት ላለፉት ሁለት ዓመታት ያሰተማራቸውን ደቀ መዛሙርት አስመረቀ !!!
  • ጳጉሜ የሚለው ስያሜ ‹‹ኤፓጉሜኔ›› ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ‹‹ጭማሪ›› ማለት ነው፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መዝገበ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገብ ቃላት፤ ገጽ ፱፻፭)
  • የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሠራተኞች ለተባባሪ ፕሮፌሰር ለብፁዕ አቡነ ፊልጶስ(ዶ/ር) የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በመመረቃቸው ልዩ የደስታና የምስጋና መርሐ ግብር አካሄዱ።
  • “መስከረም በአታ የሃያ ሺህ ሰዎች ምሥረታ” በሚል የታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም የአብነት ትምህርት ቤት ሕንጻ ግንባታ ድጋፍ ማስጀመሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ በተገኙበት ተሰጠ።

Archives

  • September 2026
  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: በቦረና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ የማሰባሰብ እንቅስቃሴውን የሚያስተባብሩ በብፁዓን አባቶች የሚመራ አምስት አባላት ያሉት ዐቢይ ኮሚቴ ተመደበ፤ Link to: በቦረና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ የማሰባሰብ እንቅስቃሴውን የሚያስተባብሩ በብፁዓን አባቶች የሚመራ አምስት አባላት ያሉት ዐቢይ ኮሚቴ ተመደበ፤ በቦረና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ የማሰባሰብ... Link to: የመምህር የኔታ ሐረገወይን ምሕረቱ የሽኝት መርሐ ግብር Link to: የመምህር የኔታ ሐረገወይን ምሕረቱ የሽኝት መርሐ ግብር የመምህር የኔታ ሐረገወይን ምሕረቱ የሽኝት መርሐ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top