የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ቅዱስ ሲኖዶስ መጋቢት ፳፩ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም ምልአተ ጉባኤ እንዲካሄድ ጥሪ ተላለፈ

March 15, 2023

*በህገ ወጥ መንገድ የተሾሙት ግለሰቦች በአምስት ቀናት ውስጥ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት መገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላለፈ።

ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ መጋቢት ፮ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የሰጠው መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል።

25ቱ ግለሰቦች ግን የሰላም ጥሪውን ከመቀበል ይልቅ እስከአሁን ድረስ በሕገ-ወጥ አድራጐታቸው ቀጥለውና በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠውን እግድ በመጣስ የአህጉረ ስብከትን ጽ/ቤት እየሰበሩ በመግባት በሌላቸው ሥልጣን ክህነት በመስጠት፣ በመዋቅራችን ላይ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞችን በመመደብ በሕገ-ወጥ አድራጐታቸው በመቀጠል ላይ ይገኛሉ፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቤተ ክርስቲያናችን የተከሰተውን ወቅታዊ ችግር አስመልክቶ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ አንቀጽ 19 ንዑስ ቁጥር 3 የሕግ ድንጋጌ መሠረት አስቸኳይ የምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ በማድረግ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንና አስተዳደራዊ ጥሰት በመፈጸም ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም. በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሰዶ ዳጩ ወረዳ በሀሮ ባለወልድ ቤተ ክርስቲያን የተፈጸመውን ሕገ-ወጥ የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ሕገ ቤተ ክርስቲያንንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የጣሰ ሕገ-ወጥ አድራጐት መሆኑን አጽንኦት በመስጠት በጉዳዩ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ፡-

ሕገ-ወጥ ሹመቱ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንና ሕገ ቤተ ክርስቲያንን የጣሰ በመሆኑ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን፤

ሕገ-ወጥ ሹመቱን ያከናወኑት 3ቱ የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳትና ተሹመናል ባዮችን 25 ግለሰቦች ከዲቁና ጀምሮ ያላቸውን ሙሉ ሥልጣነ ክህነት በመሻር እና ከቤተ ክርስቲያኒቱ አባልነት በማውገዝ መለየቱ ፤

ምንም እንኳን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሁሉንም አውግዞ የለየ ቢሆንም እናት ቤተ ክርስቲያን ዘወትር ለሰላም በሯ ክፍት እንደመሆኑ መጠን የተወገዙት ግለሰቦች የቤተ ክርስቲያኒቱን የሰላም ጥሪ ተቀብለውና የተከናወነው ድርጊት ሕገ-ወጥ መሆኑን አምነው በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት ለፈጸሙት ሕገ-ወጥ አድራጐት የሚሰጣቸውን ቀኖና ለመቀበል ፈቃደኛ ከሆኑና ይህንንም ሐሳባቸውን በጽሑፍ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በማቅረብ ሪፖርት ካደረጉ የቤተ ክርስቲያናችን የሰላም በር ክፍት መሆኑን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥር 18 ቀን 2015ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ መግለጹን እናስታውሳለን፡፡

በመሆኑም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የሰላም በሩን ክፍት በማድረግ ትዕግስት የተሞላበት ጥረት ቢያደርግም የሰላም ጥሪውን ተቀብሎ ለቀኖና ቤተ ክርስቲያን ከመቅረብ ይልቅ በሕገ-ወጥ አድራጐታቸው በመቀጠል ሕጋዊ የቤተ ክርስቲያናችን መዋቅር የሆኑትን አህጉረ ስብከት ጽ/ቤትና የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን መንበረ ጵጵስና ቁልፍ በመስበር የንብረትና የመዋቅር ወረራ በመፈጸም በሕገወጥ አድራጐታቸው በመቀጠላቸውና በተከፈተው የሰላም በር ተጠቅመው ለሰላም ዝግጁ ባለመሆናቸው ቤተ ክርስቲያናችን በሀገሪቱ ሕግ የተረጋገጠ ሕጋዊ ሰውነት ያላት ጥንታዊትና ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያን እንደመሆኗ መጠን ሕጋዊቱን ቤተ ክርስቲያን በሕገ-ወጥ መንገድ ተቋሞቿ የተያዙባት መሆኑን በመግለጽ መንግሥት ያለበትን ሕግን የማስከበር ኃላፊነት በመወጣት ተቋማዊ ክብራችንና ሕጋዊ ባለቤትነቷን እንዲያረጋግጥ ያደረገችውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት በቅድሚያ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ከቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተወከሉ ብፁዓን አባቶችን በማነጋገርና ለቀጣይ የውይይት አቅጣጫ በሰጡት አመራር ከቅዱስ ሲኖዶስ የተወከሉ ብፁዓን አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የቀድሞውን ሦስቱን ሊቃነ ጳጳሳት ራሳቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት በተደረገው ሰፊ ውይይት በ10 ነጥቦች ላይ የጋራ ስምምነት መድረሱን እናስታውሳለን፡፡

እናት ቤተ ክርስቲያን በተደረሰው ስምምነት መሠረት አሥሩን የስምምነት ነጥቦች ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን በመግለጫ አረጋግጣና በሮቿን ክፍት አድርጋ ለሰላም ከፍተኛ ጥረት በምታደርግበት ወቅት ሦስቱ የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳት የሰላም ጥሪውን ተቀብለው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሪነት ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ የመጡ ቢሆንም 25ቱ ግለሰቦች ግን የሰላም ጥሪውን ከመቀበል ይልቅ እስከአሁን ድረስ በሕገ-ወጥ አድራጐታቸው ቀጥለውና በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠውን እግድ በመጣስ የአህጉረ ስብከትን ጽ/ቤት እየሰበሩ በመግባት በሌላቸው ሥልጣን ክህነት በመስጠት፣ በመዋቅራችን ላይ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞችን በመመደብ በሕገ-ወጥ አድራጐታቸው በመቀጠል ላይ ይገኛሉ፡፡

በመሆኑም የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በአዲስ አበባና በአካባቢው የሚገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሆኑትን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ለስብሰባ በመጥራት መጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ሦስቱ የቀድሞ ብፁዓን አባቶች በአካል ቀርበው በሰጡት ቃል በተከናወነው ድርጊትና ድርጊቱን ተከትሎ በተፈጸሙት ክስተቶች ማዘናቸውንና በቀጣይ ሕገ-ወጥ ድርጊቱን እንደሚቃወሙና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶሱን መመሪያ አከብረው ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን ቅዱስ ሲኖዶሱም የሦስቱን የቀድሞ አባቶች ሐሳብ በመቀበል ጉዳዩን አስመልክቶ በሰፊው ከተወያየ በኋላ የሚከተለውን የሰላም ጥሪ አስተላልፏል፡፡
በዚህም መሠረት፡-
ሦስቱ የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳትን በተመለከተ በስምምነቱ መሠረት ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ መጥተው በበዓታቸው ተወስነው እየኖሩ ስለሆነ ደመወዛቸው እንዲከፈላቸው እንዲደረግ፣

ሃያ አምስቱን ግለሰቦችን በሚመለከት ምንም እንኳን በሕ-ወጥ አድራጐታቸው የቀጠሉ ቢሆንም ቤተ ክርስቲያናችን ለሀገሪቱ ሰላም ካላት የጸና አቋም አንጻር አሁንም በድጋሚ ለመጨረሻ ጊዜ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፊት በተደረሱት 10 የስምምነት ነጥቦች መሠረት ከዛሬ መጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት አምስት ቀናት ውስጥ የሰላም ጥሪውን ተቀብለው በጽሑፍ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሪፖርት እንዲያደርጉና በቤተ ክርስቲያናችን ቀኖና መሠረት ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ቀኖናቸውን ተቀብለው እንዲፈጽሙ፣

ክቡር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድና የኦሮምያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለሰላም ስምምነቱ ላደረጉት አስተዋጽኦ ቤተ ክርስቲያናችን ምስጋናዋን እያቀረበች በቀጣይ በተደረሰው 10 የስምምነት ነጥቦች መሠረት ሕገ-ወጦቹ ግለሰቦች የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ለሕግ ተገዥ እንዲሆኑ የበኩላቸውን መንግሥታዊ ሚና እንዲወጡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን በድጋሚ ታስተላልፋለች፡፡

ሃያ አምስቱን ግለሰቦች በሚመለከት ከኦሮምያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር በተደረገው ውይይት ክቡር ርእሰ መስተዳድሩ በተደረሰው 10ሩ ስምምነት ነጥቦች መሠረት ሃያ አምስቱንም ግለሰቦች አጠቃልዬ ወደ አዲስ አበባ አመጣቸዋለሁ በማለት በገቡት ቃል መሠረት በአሁኑ ሰዓት ግለሰቦቹ በክልሉ መንግሥት አማካኝነት ወደ አዲስ አበባ መግባታቸውን ስለሰማን የክልሉ መንግሥት በገባው ቃል መሠረት ለፈጸመው አድራጐት ቤተ ክርስቲያናችን እያመሰገነች ያልገቡትንም ግለሰቦች በአጭር ጊዜ ውስጥ በተገባው ቃል መሠረት እንዲገቡ እንዲደረግ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፣

ውግዘቱን በሚመለከት ውግዘቱን የማንሳት ሥልጣን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንደመሆኑ መጠን ሁሉም የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ለመጋቢት 21 ቀን 2015ዓ.ም. ተጠቃለው ወደ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት እንዲመጡ ጥሪ ተላልፏል፣

መጋቢት 6 ቀን 2015ዓ.ም.
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: በምሥራቅ አውሮፖ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ተባርኮ አገልግሎት መስጠት ጀመረ። Link to: በምሥራቅ አውሮፖ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ተባርኮ አገልግሎት መስጠት ጀመረ። በምሥራቅ አውሮፖ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ... Link to: ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ በጀርመን ከሙንስተር የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ጋር ውይይት አደረጉ። Link to: ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ በጀርመን ከሙንስተር የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ጋር ውይይት አደረጉ። ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ በጀርመን ከሙንስተር የካቶሊክ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top