የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

አዲስ በሚሾሙት ኤጲስቆጶሳት የአመራረጥ አካሄድ ዙሪያ በአስመራጭ ኮሚቴ አባላት ብፁዓን አባቶች ማብራሪያ ተሰጠ።

July 6, 2023

ሰኔ ፳፱ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የግንቦት ርክበ ካህናት ምልአተ ጉባዔ ለ፯ የኦሮሚያ እና ለ፪ የደቡብ ክልል አህጉረ ስብከት በኤጲስቆጶስነት የሚሾሙ ቆሞሳትን መልምለው ለምልአተ ጉባዔ እንዲያቀርቡ የተመረጡት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ባከናወኑት የምልመላ ሂደት ዙሪያ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ተሰጥተዋል።

በተሰጠው ማብራሪያ መሠረት በእጩነት የቀረቡት ቆሞሳት በመንፈሳዊ ትምህርት፣ በአገልግሎት፣ በግብረገብነትና የሚመደቡበትን ሀገረ ስብከት ምእመናን በቋንቋቸው በማስተማር ረገድ በቂ ዝግጅት ያላቸው ስለመሆናቸው ጥቆማውን ካቀረቡት አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና ከቀረቡት ተያያዥ ሠነዶችና የሕይወት ታሪኮች መረዳት መቻላቸውንና ይህንንም ለምልአተ ጉባኤ ማቅረባቸውን በዚህም መሠረት ድምጽ ተሰጥቶ ተሿሚዎች መለየታቸውን አብራርተዋል። ምንም እንኳ ለምልአተ ጉባኤ የቀረቡት ቆሞሳት ቁጥር ፲፰ ቢሆኑም ቀድሞ በጥቆማ የቀረቡት አባቶች ቁጥር ፸፭ እንደነበሩ በኮሚቴው ጸሐፊ በብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ተገልጿል።

ጥቆማው፣ ግምገማውና ምርጫው ምእመናንና ካህናት አልተሳተፉበትም በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄም:- ምንም እንኳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የካህናት እና የምእመናን የጋራ የአገልግሎት ቦታ የሰማያዊት ኢየሩሳሌም አምሳል ስለመሆኗ ሁሉም የሚያምነው እውነት እንደሆነ ሁሉ ቤተክርስቲያናችን ከራሷ ልጆች ሊቃነ ጳጳሳትን መሾም ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ የምርጫ ሂደት የሚካሄደው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ብቻ በመሆኑ የዛሬውም ከቀድሞ አሠራር የተለየ አይደለም ቢሆንም ግን የካህናትንና የምእመናንን ይሁንታ ለማወቅ በተለያዩ መንገዶች ተጠቋሚዎቹ አባቶች ካገለገሉባቸው አህጉረ ስብከት እና አጥቢያዎች መረጃ ጠይቀናል ከዚህም ባሻገር ሊቃውንትንና ምእመናንን ለማሳተፍ የተሠራ ሥርዓት ሳይሠራ ወደማሳተፍ ቢገባ ችግር ሊያመጣ ይችላል የሚል ስጋት ስለመጣ በነበረው የአመራረጥ ልማድ ተከናውኗል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

ጥር ፲፬ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም ከቀኖና ቤተክርስቲያን ውጪ ከተሾሙ አባቶች መካከል የተወሰኑት ለምን ተካተቱ በሚል ለተነሳው ጥያቄም ምላሽ የሰጡት አበው ሊቃነ ጳጳሳት አስቀድሞ የቤተክርስቲያናችንን ሰላምና መዋቅራዊ አንድነት ለመጠበቅ በተደረገው የሰላም ስምምነት መሠረት ውግዘቱ ሲነሣ ፍጹም ሰላም ስለመፈጠሩ ቅዱስ ሲኖዶስ እምነት ስላደረበት ለሲመቱ ብቁ መሆናቸው የታመነባቸው ለንስሐ የበቁ አባቶችን መግፋት አስፈላጊ ባለመሆኑ የተወሰኑት አባቶች በእጩነት ቀርበው በቅዱስ ሲኖዶስ የታመነባቸው መመረጣቸውን እንዲሁም ቀድሞ በችግሩ ወቅት በነበረው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በተደረገው ውይይት በጓዳ ለመግባት የተደረገውን ሙከራ አወገዘ እንጂ በተደረገው ጥናት ያለእውቀት በተለያየ ወቅታዊ ስብከትና ጫና ተታለው የገቡ መኖራቸው በመረጋገጡ ሊመረጡ ችለዋል ሲሉ ገልጸዋል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/favicon.png 169 151 tc https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg tc2023-07-06 12:41:042023-07-06 12:42:04አዲስ በሚሾሙት ኤጲስቆጶሳት የአመራረጥ አካሄድ ዙሪያ በአስመራጭ ኮሚቴ አባላት ብፁዓን አባቶች ማብራሪያ ተሰጠ።
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ሲያካሂድ የነበረውን አስቸኳይ ስብሰባ በማጠናቀቅ የተሰጠ መግለጫ Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ሲያካሂድ የነበረውን አስቸኳይ ስብሰባ በማጠናቀቅ የተሰጠ መግለጫ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን... Link to: ቅዱስ ፓትርያርኩ አልሾምም ወደ ትግራይም ፤ አልሔድም አላሉም Link to: ቅዱስ ፓትርያርኩ አልሾምም ወደ ትግራይም ፤ አልሔድም አላሉም ቅዱስ ፓትርያርኩ አልሾምም ወደ ትግራይም ፤ አልሔድም...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top