የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የቦሌና ለሚ ኩራ ክፍላተ ከተሞች ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት የ፳፻ ፲ወ፭ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አደረገ፤ በሥራ አፈጻጸም ውጤት ያስመዘገቡ አድባራትን ሸለመ።

October 5, 2023

መስከረም ፳፬ ቀን ፳፻ ፲ወ ፮ ዓ.ም

አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ

ዛሬ በቦሌና ለሚ ኩራ ክፍላተ ከተማ በተደረገ የ፳፻ ፲ወ፭ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ግምገማና የአዲሱ ዓመት ዕቅድ ዙሪያ በተደረገ ስብሰባ ላይ በክፍላተ ከተማው ሥር የሚሚገኙ አድባራትና ገዳማት በተለይም ውጤታማ የሥራ ክንውን ላደረጉት የሽልማት መርሐ ግብር ተከናውኗል።

በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል አዳራሽ ዛሬ በተከናወነው መርሐ ግብር ሊይም ብፁዕ አቡነ ሔኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተገኝተው በክፍለ ከተማው በተካሔደው መርሐ ግብር ላይ አባታዊ መልዕክት፣ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ የሰጡ ሲሆን በሥራ አፈጻጸማቸው ውጤታማ ለሆኑ አድባራትና ገዳማት እንዲሁም ለክፍለ ከተማው የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የተዘጋጀላቸውን ሽልማት አበርክተዋል።

በዚሁ መርሐ ግብር ላይም በበጀት ዓመቱ የክፍላተ ከተማው ቤ/ክህነት ጽ/ቤት ከመንግሥት አካላት ጋር ተቀራርቦ መሥራት በመቻሉ በሰላም፤በልማትና በመልካም አስተዳደር የሚታይ ጉልህ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉ በልዩ ልዩ አካላት ተገልጿል።

የክፍለከማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዓለምፀሐይ ሽፈራው በመርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር ይህን በማረጋገጥ ለተገኘው ውጤት የመሪነት ሚናቸውን ለተወጡት መልአከ ብርሃን ሩፋኤል የማነብርሃን ምስጋና አቅርበዋል።ሥራ አስፈጻሚዋ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ በመጠቀም የቤተ ክርስቲያን መብት እንዲከበር እና መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን በማድረጋቸው ከብፁእ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ልዩ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በሁለቱም ክፍላተ ከተሞች በሚገኙ ገዳማትና አድባራት ሰላምና ልማት እንዲሰፍን ያደረጉ የክፍለከተማው ሠላምና ፀጥታ የሠራተኛ ራ ኃላፊዎችና የክፍለከተማው ፖሊሰም በዚሁ መርሐ ግብር ላይ በልዩ ሁኔታ ተሸልመዋል።

የክፍላተ ከተሞቹ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በ፳፻ ፲ወ፭ ዓ፡ም ካከናወናቸው ዋና ዋና የልማት ሥራዎች መካከልም የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ይዞታ መብት ማስከበር፡ የአዳዲስ አብያተ ክርስቲያናት ምስረታ፥ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ማስገኘት፤ የክፍለከተማ ዋና ጽ/ቤት መስሪያ ከ፩ሺህ ፱፻ ካሬ ሜትር እና ፬ሺህ ካሬ ሜትር ለልማት የሚውል ቦታ ከመንግሥት ማግኘቱ ተጠቅሷል።

ከዚህ በተጨማሪ የጥምቀት ማክበሪያ ቦታዎችን ማግኘቱንና ከ፳፻ ፲ወ፬ ዓ፡ም በጀት ዓመት የ፴፰ ሚልዮን ብር ብልጫ ያለው ፐርሰንት ከገዳማትና አድባራት መሰብሰቡ ተገልጿል።

ብፁእ አቡነ ሄኖክ በበዓሉ ላይ ለተገኙ እንግዶችና ውጤታማ ለሆኑ ገዳማትና አድባራት ሽልማት ከሰጡ በኋላ በሰጡት አባታዊ መመሪያ በ፳፻ ፲ወ፭ ዓ፡ም የታየው የሥራ መነሳሳትና ውጤት በ፳፻ ፲ወ፮ ዓ፡ም ተጠናክሮ እንዲቀጥል መመሪያ ሰጥተዋል።

በዚሁ ደማቅና በአርአያነቱ በሚደነቀው በመርሐ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎች ፣ በክፍለ ከተማው ሥር የሚገኙ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ፣ ካህናት ፣ ዲያቆናት ፣ ዘማርያን ፣ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪ ወጣቶች ተገኝተዋል።

መልአከ ብርሃን ሩፋኤል የማነብርሃን የቦሌና ለሚኩራ ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የክፍላተ ከተማው አሰራር ዘመናዊነትን የሚከተል፣ውጤታማ ሥራ የሚከናወንበት፣የታቀደ የሚለካና ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጣ መሆን ይችል ዘንድ የመሪነት ድርሻቸውን በሚገባ የተወጡ መሆኑን በየ ዓመቱ የሚያካሒዱት የሥራ አፈጻጸም ግምገማና የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎች ጠቋሚ መርሐ ግብሮች በቂ ማሳያ ናቸው።መልአከ ብርሃን ሩፋኤል የማነብርሃን ቀድሞ በነበሩበት ደብር ተቋማዊ፣ሕጋዊና ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ያስጠበቀ ውጤታማ ሥራ ያከናወኑ ብርቱ መሪ መሆናቸውም ይታወቃል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል በመንገሺና ጎደሬ ወረዳዎች የተተከሉ ሦስት አብያተክርስቲያናትን ባርከው ቅዳሴ ቤታቸውን አክበሩ በቢሻን ዋዩ ሐርቅ ለሚተከለው የቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የመሰረት ድንጋይ አኖሩ። Link to: ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል በመንገሺና ጎደሬ ወረዳዎች የተተከሉ ሦስት አብያተክርስቲያናትን ባርከው ቅዳሴ ቤታቸውን አክበሩ በቢሻን ዋዩ ሐርቅ ለሚተከለው የቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የመሰረት ድንጋይ አኖሩ። ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል በመንገሺና ጎደሬ ወረዳዎች... Link to: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሰሜን አሜሪካን የነበራቸውን ቆይታ በማጠናቀቅ ላይ ናቸው። Link to: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሰሜን አሜሪካን የነበራቸውን ቆይታ በማጠናቀቅ ላይ ናቸው። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top