የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ቅዱስ ፓትርያርኩ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ለሚያስገነባው ባለ ሰባት ወለል ሕንጻ የመሠረት ደንጊያ አስቀመጡ።

January 13, 2024

ጥር 4 ቀን 2016 ዓ.ም
“”””” “”””””””””””””””
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
+++++++++++++
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ለሚያስገነባው ባለ ሰባት ወለል ሕንጻ የመሠረት ደንጊያ አስቀመጡ። በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት እና የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሚመራው ፣የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የካህናት ማሰልጠኛ ሆኖ ከዘመናዊ ትምህርት ቤት እስከመንፈሳዊ ኮሌጅና ኃላም ከፍተኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ነገረ መለኮት ወይም ቲዎሎጂ ትምህርት ማስተማሪያ ፣የጥናትና ምርምር ማዕከል ሆኖ ለ60 ዓመታት ያህል መንፈሳዊ አገልግሎት መስጠቱ ይታወቃል።

ተቋሙ በእነዚህም ዘመናት ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን በርካታ ሊቃውንትን አፍርቷል። አብዛኞቹ ምሁራን በመንፈሳዊዉ ዓለም ከዲቁና እስከ ጵጵስና ፣በማኅበራዊዉ ዘርፍ ደግሞ ከመምህርነት እስከ አምባሳደርነት፣አልፎም እስከ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ በመድረስ ከዚሁ ከፍተኛ መንፈሳዊ ተቋም ባገኙት ዕውቀት እና ጥበብ በተለያዩ የሥራ መስኮች ሀገራቸውንና ቤተ ክርስቲያናቸውን በከፍተኛ ሐላፊነት ሲያገለግሉ መቆየታቸው አይዘነጋም።አንጋፋውና የዕድሜ ባለጸጋው የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ ጊዜ ከትምህርትና አስተዳደር ዘርፍ ጎን ለጎን በራስ አገዝ ልማት ከፍተኛ የለውጥ ሥራዎች ግሥጋሴ ላይ የሚገኝ ሲሆን ከዚህ ቀደም ከፓርላማ እስከወክማ ከተገነባው ሽንጠ ረጅምና ሰማይ ጠቀስ ሕንጻ በተጨማሪ ከሦስት ሺህ በላይ ባለው የካሬ ሜትር ስፋት ላይ ባለሰባት ወለል ሁለገብ ሕንጻ ለመገንባት ጥር 4 ቀን 2016 ዓ.ም ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ክቡር ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ፣የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ሐላፊዎች፣የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት የሥራ ሐላፊዎች፣የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብና ደቀመዛሙርት በተገኙበት የመሠረት ደንጊያ የማኖር መርሐ ግብር ተካሂዷል።መርሐ ግብሩ በጸሎተ ወንጌል የተከፈተ ሲሆን በማያያዝም ዕብነ መሠረቱ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩና በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተቀምጧል።የ

ሕንጻውን የዲዛይን ይዘት በተመለከተ በባለሙያ ማብራሪያ ተሰጥቷል። በተያያዘም በዩኒቨርሲቲው ግቢ ዕድሳት ተደርጎለት አገልግሎት የጀመረው መንበረ ጵጵስና በቅዱስ ፓትርያርኩና በብፁዓን አባቶች ተጎብኝቷል።ዛሬ ለመንበረ ጵጵስና የበቃው ቤት በንጉሠ ነገሥት ግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን መጻሕፍትን የምትተረጉምበት፣ በኮፕቲክ ሲኖዶስ ተሹመው ወደሀገራችን የመጡት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት (የመጀመሪያዎቹ አምስቱ ሊቃነ ጳጳሳት )ማረፊያ የነበረ ሲሆን አሁን እስከተደረሰበት የመንበረ ጵጵስና ደረጃ ድረስ ደግሞ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብና ደቀ መዛሙርት የጸሎት ማዕከል ሆኖ ሲያገለግል መቆዩቱን የዩኒቨርሲቲው የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያምና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል በ22 ሚሊዮን ብር ወጪ ያስገነባው የእንጀራ ማምረቻ በቅዱስ ፓትርያርኩ ተመረቀ። Link to: የደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያምና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል በ22 ሚሊዮን ብር ወጪ ያስገነባው የእንጀራ ማምረቻ በቅዱስ ፓትርያርኩ ተመረቀ። የደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያምና... Link to: ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የጥምቀት በዓልን ለማክበር ጋምቤላ ገቡ፤ከአሥር ሚሊየን ብር በላይ ንዋያተ ቅዱሳን ይዘው ተጉዘዋል። Link to: ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የጥምቀት በዓልን ለማክበር ጋምቤላ ገቡ፤ከአሥር ሚሊየን ብር በላይ ንዋያተ ቅዱሳን ይዘው ተጉዘዋል። ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የጥምቀት በዓልን ለማክበር...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top