የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የጌታችን፣ የአምላካችን፣ የመድኀኒታችን፣ የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል ሰላማዊ በሆነ መልኩ ተከብሮ እንዲውል ላደረጋችሁ ሁሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምስጋናዋን ታቀርባለች፤

January 22, 2024

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የጌታችን፣ የአምላካችን፣ የመድኃኒታችን፣ የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም ተከብሮ እንዲውል ለማድረግ ልዩ ልዩ ኮሚቴዎችን በማቋቋም ስትሠራ የሰነበተች ሲሆን ከሚመለከታቸው የፌደራልና የክልል መንግሥታትና የጸጥታ አካላት ጋርም በመነጋገር በዓሉ ያለ አንዳች የጸጥታ ችግር ተከብሮ እንዲውል ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ስታደርግ ሰንብታለች።

በዚህም  መሰረት የከተራ፣ የጥምቀት፣ የቃና ዘገሊላ፣ የቅዱስ እግዚአብሔር አብ እና የቅዱስ ሩፋኤል በዓላት ፍጹም ሰላማዊና ሃይማኖታዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ በተረጋጋ፣ መንፈሳዊ በሆነና ፍጹም ክርስቲያናዊ ግብረ ገብነትን በጠበቀ ሁኔታ በመላ አገራችን ተከብሮ ውሏል። በተለይም በአዲስ አበባ በጃን ሜዳ በማዕከል ደረጃ የተከበሩት በዓላት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሊቀ አእላፍ በላይ መኮንን የጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ሥራአስኪያጅ፣ የፌደራልና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣የጠቅላይ ቤተክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች፣ ሊቀ ማዕምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የዋና ክፍል ኃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች፣ በሚሊየን የሚቆጠሩ ምእመናንና ምእመናት በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ውሏል።

የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የጥምቀት በዓል በዚህ መልኩ ባማረና በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ መዋል ይችል ዘንድ ምዕመናንና ምዕመናት እንዲሁም ወጣት የቤተክርስቲያን ልጆቻችን የቤተክርስቲያንን ድምጽ በመስማትና በማክበር ላደረጋችሁት ከፍተኛ ጥረት ቅድስት ቤተክርስቲያን ምስጋናዋን ታቀርባለች። በዓሉ ያለምንም የጸጥታ ችግር ተከብሮ መዋል ይችል ዘንድ ቀን ከሌሊት የጸጥታውን ሥራ በማከናወንና አመራር በመስጠት፣ የትራፊክ ፍሰቱ በዓሉን በማያውክ መልኩ እንዲከናወን ያደረጋችሁ የከተማችን አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች፣ የጸጥታ አካላቱ አመራሮችና የጸጥታ መዋቅሩ አባላት እንዲሁም የትራፊክ ፓሊስ አመራሮችና አባላቱ ላበረከታችሁት አስተዋጽኦ ቅድስት ቤተክርስቲያን ልባዊ ምስጋናዋን ታቀርባለች።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት አዳነች አቤቤ በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲውል ለሰጡት አመራርና በዓሉ በተከበረበት በጃንሜዳ ደረጃውን የጠበቀ ስቴጅ፣ የድምጽ መሣሪያ፣ የክብር እንግዶች ወንበርና ለበዓሉ ድምቀት የሚያስፈልገውን ሁሉ በማሟላትና ወጪውን በመሸፈን በዓሉ አገራዊ መሆኑን በተግባር በማሳየት ላደረጉልን ድጋፍ በድጋሚ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ልባዊ ምስጋናዋን ታቀርባለች።

በአጠቃላይ የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የጥምቀት በዓላችን ፍጹም መንፈሳዊና ደማቅ በሆነ መልኩ ተከብሮ እንዲውል ልዩ ልዩ ድጋፍ ያደረጋችሁ አካላትና የተለያዩ ዕምነት ተከታይ ወገኖቻችን ያደረጋችሁትን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ቤተክርስቲያናችን በልዩ አድናቆት የምትመለከተው ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ  ምስጋናዋን ታቀርባለች። ወደፊትም በመሰል የአደባባይ በዓላቶቻችን ላይ በጋራ መሥራታችንን አጠናክረን እንድንቀጥል አደራ ትላለች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት
ጥር ፲፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/favicon.png 169 151 tc https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg tc2024-01-22 15:20:452024-01-22 15:20:45የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የጌታችን፣ የአምላካችን፣ የመድኀኒታችን፣ የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል ሰላማዊ በሆነ መልኩ ተከብሮ እንዲውል ላደረጋችሁ ሁሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምስጋናዋን ታቀርባለች፤
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: በዓለ ጥምቀትን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች የቤተክርስቲያን አስተምህሮ ላይ ብቻ ያተኮረ ምላሽ እንዲሰጥ መመሪያ ተላለፈ። Link to: በዓለ ጥምቀትን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች የቤተክርስቲያን አስተምህሮ ላይ ብቻ ያተኮረ ምላሽ እንዲሰጥ መመሪያ ተላለፈ። በዓለ ጥምቀትን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች የቤተክርስቲያን... Link to: የከተራ፣የጥምቀትና የቃና ዘገሊላ በዓላት በአላማጣ በድምቀት ተከብሮ ዋለ። Link to: የከተራ፣የጥምቀትና የቃና ዘገሊላ በዓላት በአላማጣ በድምቀት ተከብሮ ዋለ። የከተራ፣የጥምቀትና የቃና ዘገሊላ በዓላት በአላማጣ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top