ጥር ፲፰ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
=================
አዳማ – ኢትዮጵያ
“””””””””””””””

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በቦሰት ወረዳ ቤተ ክህነት የመርቆ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን በአሳዛኝ ሁኔታ ባልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች ትናንት ጥር 17/2016 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ተቃጥሏል፡፡

የሚዲያ ክፍላችን ባገኘው መረጃ መሠረት በቦታው ላይ በተደጋጋሚ ጊዜ ዛቻና ማስፈራሪያ ሲያደርጉ የቆዩ ቢሆንም በትናንትናው ዕለት ሙሉ በሙሉ ንዋዬ ቅድሳቱ የተቃጠለ ሲሆን የቤተ መቅደሱ የውስጥና የውጭ ክፍል ጉዳት ያደረሰ ከፍተኛ ቃጠሎ አድርሰዋል፡፡ በጉዳዬ ላይ ሀገረ ስብከቱ አስፈላጊውን የማጣራት ሥራ እየሠራ ይገኛል፡፡

ለአካባቢው ኦርቶዶክሳውያን ይኼ ትልቅና ከባድ ቁስም የሚሰብር አስጸያፊ ድርጊት በመሆኑ የሚመለከተው አካል አስፈላጊ ጥበቃ ሊያደረግላቸው ይገባል ሲል ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ ሏላከልን ዘገባ ገልጿል።