የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

አገር አቀፍ የስብከተ ወንጌል አልግሎትን ለማጠናከር የሚያስችል የምክክር መድረክ ተካሔደ።

February 1, 2024

ጥር ፲፰ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም
“”””””””””””””””””””””””””
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
******
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ አገር አቀፍ የስብከተ ወንጌልን አገልግሎት በተጠና፣ተቋማዊ በሆነና ለውጥ ሊያመጣ በሚያስችል መልኩ ማከናወን የሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከሚመለከታቸው አካላትና ከስባቱ ክፍላተ ከተማ ሥራ አስኪያጆችና የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊዎች ጋር ጥር ፲፮ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መሰብሰቢያ አዳራሽ የምክክር መድረክ አካሔደ።

በውይይት መድረኩ ላይ የመምሪያው ዋና ኃላፊ መ/ሰ ቆሞስ አባ ቃለጽድቅ ሙሉጌታ ዶ/ር ስብከተ ወንጌል የቤተክርስቲያናችን ዋነኛ ተልዕኮና ተቀዳሚ ሥራ ሞሆኑን አውስተው ይህን ተቀዳሚ የቤተክርስቲያናችን ሥራ በቂ መምህራንና ምቹ ሁኔታዎች ባሉበት ሁኔታ የሚፈለገውን ውጤት ማምጣት በሚያስችል መልኩ ሥራውን ማከናወን አለመቻል በእጅጉ አሳዛኝ መሆኑን ጠቁመው ዘመኑን በሚመጥንና በሚዋጅ መልኩ የስብከተ ዘንጌል ሥራችንን በተጠናና ውጤት ሊያመጣ በሚችል አግባብ በማከናወን ስኬታማ ሥራ ለመሥራት መዘጋጀት ይኖርብናል ብለዋል።

የመምሪያው የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ በጉባኤው ላይ በመገኘት ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክትም ቤተክርስቲያን የሰጠችንን ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት በስብከተ ወንጌል ዘርፍ የሚታየውን ክፍተት ለመሙላት መወያየት፣ችግሩን ማወቅና ለችግሩ መፍትሔ መስጠት የሚያስችል ስልቶችን ቀይሶ በመስራት ተጨባጭ ለውጥ ማስመዝገብ እንደሚቻል ጠቁመው ቤተክርስቲያናችን የምሁራንና የሰባኪያነ ወንጌል እጥረት የሌለባት ተቋም ስለሆነች ይህኔን የመሰለ የውይይት መድረኮችን በማመቻቸት በችግሮቹና በመፍትሔዎቹ ዙሪያ በመምከር አገር አቀፉን የስብከተ ወንጌል አገልግሎታችንን ለማስፋፋትና ለማጠናከር በጋራ መስራት ይኖርብናል ብለዋል።

በውይይት መርሐ ግብሩ ላይ የተሳተፉት የሥራ ኃላፊዎችም የስብከተ ወንጌል አገልግሎቱን ለማጠናከርና ለማስፋፋት ይህን የመሰለ የውይይት መድረክ ማመቻቸት ተገቢ መሆኑን ጠቅሰው አገር አቀፉን የስብከተ ወንጌል አገልግሎት መርሐ ግብርን ውጤታማ ለማድረግ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በቅርብ ጊዜ ውስጥም አገር አቀፍ የስብከተ ወንጌል አገልግሎትን ለማስፋፋትና ታላላቅ ጉባኤዎችን በማከናወን የስብከተ ወንጌል አገልግሎቱን በተጠናከረ መንገድ የማከናወን ሥራ መሰራት እንደሚጀምርም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ገልጿል።በተጨማሪም የዚህ ምክክር ዓላማ ጥር ፴ እና የካቲት ፩ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም ለሚካሔደው አገር አቀፍ የስብከተ ወንጌል ጉባኤ ግንዛቤ መፍጠር መሆኑንም መምሪያው ጨምሮ አስታውቋል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: በቦሰት ወረዳ ቤተ ክህነት የመርቆ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ፡መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ባልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች ተቃጥሏል፡፡ Link to: በቦሰት ወረዳ ቤተ ክህነት የመርቆ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ፡መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ባልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች ተቃጥሏል፡፡ በቦሰት ወረዳ ቤተ ክህነት የመርቆ መካነ ሕይወት... Link to: የመርካቶ ደብረ አሚን ዳግሚት ደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን እድሳት ተጠናቆ በብፁዕ ወቅዱስ አባታችን ተባርኮለአገልግሎት መስጠት ጀመረ። Link to: የመርካቶ ደብረ አሚን ዳግሚት ደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን እድሳት ተጠናቆ በብፁዕ ወቅዱስ አባታችን ተባርኮለአገልግሎት መስጠት ጀመረ። የመርካቶ ደብረ አሚን ዳግሚት ደብረ ሊባኖስ አቡነ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top