የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተዳደር ጉባኤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰጠውን መግለጫ መነነሻ በማድረግ በጉዳዩ ላይ ተወያይቶ ልዩልዩ ውሳኔዎችን አስተላለፈ።

September 10, 2024

ጷጉሜ ፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
“”””””””””””””””””””””””””””””
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
+++++++++++++

የጠቅላይ ቤተክህነቱ አስተዳደር ጉባኤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በቅርቡ የሰጠውን መግለጫ በተመለከተ በሰፊው ተወያይቶ ልዩልዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

አስተዳደር ጉባኤው ሀገረ ስብከቱ በሰጠው  መግላጫ ላይ ሕግና ሥርዓትን አክብሮ እንዲሁም ከጠቅላይ ቤተክህነት ጋር በመመካከር የሚሰራ መሆኑን የገለጸበት ሁኔታ አግብነት የሌለውና ከግብረ ሙስና ጋር በተያያዘ በተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች ለተነሳበት ወቀሳ ከለላ ለመፈለግ የተሰጠ የሽፋን መግለጫ መሆኑን በማውሳት መግለጫውን በአጽንኦት ተችቶቷል።

ጠቅላይ ጽሕፈት ቤቱ በተለያዩ ጊዜያት  ሀገረ ስብከቱ ሕግና መመሪያን አክብሮ ብቻ እንዲሰራ በተለያዩ ጊዜያት ልዩሎዩ መመሪያዎችን በተደጋጋሚ ሲያስተላልፍ መቆየቱን ያስታወሰው  ጉባኤው ሀገረ ስብከቱ ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የሚተላለፍለትን የሥራ መመሪያ ወደ ጎን በመተውና በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ ሥራ ላይ የዋለውን የሀገረ ስብከቱን መተዳደሪያ ደንብ በመጣስ ልዩልዩ የሥራ ግድፈቶችን ሲፈጽም ከቆየ በኋላ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ አካላት በተደራጀ ሁኔታ እየተነሱበት ያሉትን ጥያቄዎች ለመሸሽ ሲል አላሰራ ብሎኛል በማለት ሲተቸው የከረመውን የሀገረ ስብከቱን መተዳደሪያ ደንብ እንደ መሸሸጊያ ለመጠቀም መሞከሩ እጅጉን አሳፋሪና እርባና ቢስ መሆኑን ጉባኤው ገልጿል።

ከሁሉ በላይ ጠቃሚ የሚሆነው ሕግና ሥርዓትን አክብሮ መስራት እንደሆነ የገለጸው ጉባኤው ሀገረ ስብከቱ በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ ሥራ ላይ እንዲያውለው የተሰጠውን መተዳደሪያ ደንብ ወደ ጎን በማለት ያከናወናቸው ሕገ ወጥ ተግባራት በጊዜ እንዲታረሙ አለመደረጋቸው ቤተክርስቲያናችንን ለተጨማሪ ኪሳራና  ለመልካም ስሟ መጉደፍ ምክንያት ሆኗል ብሏል።

በአሁኑ ጊዜ የሚታየውን የሙስና መስፋፋትና የመልካም አስተዳደር እጦት ያስከተለውን ብልሹ አሰራር አምረን ካልተቃወምንና የተሻለ ተቋማዊ የአሰራር ስርዓትን በመዘርጋት በሕግ፣በመመሪያና በደንብ የሚመራ ተቋም በመፍጠር
ቤተክርስቲያንን መታደግ ካልቻልን በእግዚአብሔርም በታሪክም በሕግም በሞራልም ከተጠያቂነት ስለማንድን ችግሩን በይፋ አውጥተን ዳግመኛ በማይደገምበት ሁኔታ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፍታት ይጠበቅብናል ያለው ጉባኤው የቤተክርስቲያንን መልካም ስም ወደ ቀደመ ክብሯ ለመመለስ ይቻል ዘንድ እስከ መጨረሻው በጽናት የሚጠበቅብንን ሁሉ እንሰራለን ብሏል።

በመሆኑም በሀገረ ስብከቱ የሚስተዋለውን የሙስናና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመሰረቱ መፍታት ይቻል ዘንድ በአጭር ቀናት ውስጥ ዝርዝር ጉዳዩን ከመፍትሔ ሀሳብ ጋር በማጥናት የሚያቀርብ ከጠቅላይ ቤተክህነት፣ከምሁራን፣ከወጣቶችና ከማኅበራት የተውጣጣ ጠንካራ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ እንዲገባና በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጥንቶ በሚያቀርበው ሰነድ መነሻነት ተቋማዊ ለውጥ ሊያስመዘግብ የሚያስችል ሥራ እንዲሰራ ወስኗል።

ይህንን ሥር ነቀል የአሰራርና አደረጃጀት ለውጥን ለማምጣት የሚደረገው ተጋድሎ ሀገረ ስብከቱንም ሆነ ቤተክርስቲያናችንን የሚጠቅም፣መልካም ስምና ልዕልናዋን የሚመልስ እንዲሆን በማድረግ የምዕመናንን እምነት በድጋሜ ማግኘት በሚያስችል ስልት በመምራት ለአፈጻጸሙም አስፈላጊውን መስዋዕትነትን ለመክፈል ቁርጠኛ መሆኑን የገለጸው አስተዳደር ጉባኤው ይህ ጉዳይ ግቡን እስከሚመታ ድረስ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪና እንደ አንድ ልብ መካሪ በጋራ የምንሰራ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን በማለት ያለ ምንም ልዩነት በአንድ ድምጽ ወስኗል።

ከዚህ ጋር በተያያዘም ያልተጠናና እውነትን መሰረት ያላደረገ መግለጫ በመስጠት ሕዝበ ክርስቲያኑን ያሳዘኑ የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎችም ለፈጸሙት ተቋማዊ መናጋትና ላስተላለፉት በሐሰት ላይ ለተመሰረተ መረጃ በአስቸኳይ ተገቢውን ተመጣጣኝ የሆነ አስተዳደራዊ የእርምት ውሳኔ ሀገረ ስብከቱ በመስጠት ለጠቅላይ ቤተክህነት በሪፖርት እንዲገለጽ ጉባኤው ወስኗል።

በሌላ በኩል ከደመወዝ ጭማሪ ጋር ተያይዞ አስተዳደር ጉባኤው የሚከተለውን ውሳኔ አስተላልፏል።

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ሠራተኞችን ከአጥቢያ ወደ ሀገረ ስብከት አዛውሮ በሚመድብበት ወቅት በሠራተኛ መተዳደሪ ደንቡን አንቀጽ 8 ንዑስ ቁጥር 6 የሕግ ድንጋጌ መሠረት የቦታውን መነሻ በጀት እንዲያገኙ ማድረግ ሲገባው ሕጉ ተጥሶ አስቀድሞ በቦታው ላይ ይሠራ የነበረው ሠራተኛ በአገልግሎት ብዛት የሚያገኘውን ደመወዝ እንዲያገኝ መደረጉ አግባብነት የሌለውና የዋናው መ/ቤትም እንዲህ አይነቱን
ጥያቄ እየተቀበለ ሲያጸድቅ መቆየቱ የሠራተኛ መተዳደሪያ ደንቡን የጣሰ አድራጎት በመሆኑ ከዛሬ ነሐሴ 28 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እንዲህ አይነቱ ተግባር እንዳይፈጸም አስተዳደር ጉባኤ ወስኗል፡፡

ሀገረ ስብከቱ ከአጥቢያ በዝውውር ወደ ሀገረ ስብከቱ የሚዛወሩ ሠራተኞች በጀት በተመለከተ ከመደበኛ የደመወዝ በጀት ውጭ የፋይናንስ እና የሠራተኛ መተዳደሪያ ደንቡ ተጥሶ የነዳጅና የልማት ገቢ አበል በማለት የሚተከለው በጀት እንዲቆም፣ሀገረ ስብከቱ ያለምንም ሥራና በቂ ምክንያት በዝውውር በሀገረ ስብከቱ ውስጥ እየተገበረው ያለውን የሠራተኛ ክምችት እንዲያቆም፤ከክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት እስክ ሀገረ ስብክት ባሉት የሥራ መደቦች የሚፈጸም የሠራተኛ ቅጥር ዝውውር እና እድገት በሀገረ ስብከቱ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 10 ንዑስ ቁጥር 4 እና በአንቀጽ 20 ንዑስ አንቀጽ 1 ተራ ቁጥር 3 የሕግ ድንጋጌ መሠረት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሲጸድቅ እና ሲፈቀድ ብቻ ይፈጸም በማለት ወስኗል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ አዲሱን ዓመት አስመልክቶ ለመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው ያስተላለፉት አባታዊ መልእክት። Link to: ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ አዲሱን ዓመት አስመልክቶ ለመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው ያስተላለፉት አባታዊ መልእክት። ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ አዲሱን ዓመት አስመልክቶ ለመንፈስ... Link to: እግዚአብሔር አምላክ አገራችን ኢትዮጵያን ይጠብቅልን። Link to: እግዚአብሔር አምላክ አገራችን ኢትዮጵያን ይጠብቅልን። እግዚአብሔር አምላክ አገራችን ኢትዮጵያን ይ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top