መስከረም 9/2017 ዓ/ም

ስልጠናው በሀገረ ስብከቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ በመጋቤ ሃይማኖት ነጻነት አክለወግ የተሰጠ ሲሆን የስልጠናው ዋና ዓላማ ከዚህ በፊት የተለያየ የማኅበራት ስያሜ ይዘው ቤተ ክርስቲያንን ሲያገለግሉ የነበሩ ማኅበራት ፈቃድ ለማግኘት እስከ አሁን ሲመሩበት የነበረውን መተዳደሪያ ደንብ በመምሪያ ደረጃ የወጣውን የማኅበራት ደንብ መሠረት አድርገው ማስተካከል እንዲችሉ ነው።

ከስልጠናው በኋላ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የቀረቡ ሲሆን በመጨረሻም ማኅበራቱ ደንባቸውን አሻሽለው እንዲያመጡና በሀገረ ስብከቱ በኩልም አስፈላጊው ድጋፍ እንደ ሚደረግ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

መረጃው ሲዳማ ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት ነው።