የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

በኮቸሬ ገደብና ጮርሶ ወረዳ ቤተክህነት የሰንበት ት/ቤት አንድነት ተመሠረተ!!!

September 23, 2024

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በኮቸሬ ገደብና ጮርሶ ወረዳ ቤተክህነት የሰንበት ት/ቤት አንድነት ተመሠረተ!!
የሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ ሊቀትጉሃን ቀሲስ ሀብታሙ አበበ  ከፊት ይልቅ ትጉ!! በ፪ኛ ጴጥ ፪:፲ ያለውን አምላካዊ ቃል መነሻ በማድረግ የሰንበት ት/ቤት አባላት መጠራታቸውን መመረጣቸውን በመመልከት ከበፊት ይልቅ መትጋትና የቅድስት ቤተክርስቲያን ሥርዓት በመጠበቅና በማስጠበቅ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ በሰፊው አስተምረዋል።

የኮቸሬ ገደብና ጮርሶ ወረዳ ቤተክህነት ዋና ፀሐፊ በኩረ ትጉሃን ቀሲስ አስቻለሁ ገ/መድኀን በመርሐ ግብሩ ያስተላለፉት መልዕክት ጥሩ ዜጋ መሆን እንደሚገባቸው፣ ወደ አገልጋይነት እንዲመጡ ሰንበት ት/ቤቶች ማጠናከር እንደሚገባን ፣ከአለባበስ እና ከአነጋገርን ጀምሮ መንጠንቀቅ እንዳለባቸው አሳስበዋል ። የአንድነቱ መመሥረት ሰንበት ት/ቤትች የልምድ ልውውጥ ማድረግ እንዲችሉ የሰንበት ተማሪዎችን በቃሉ ለማስታጠቅና ቴክኖሎጂን በአግባቡ መጠቀም እንዲሁም የማንበብ ልምዳችንን ማጎልበት የሚቻልበት መንገድ የሚፈጥር በመሆኑ አጽራረ ቤተክርስቲያን እንቅስቃሴ ለመገዳደር የሚያስችል መሆኑና አያሌ ጥቅሞቹን ዘርዘር አድርገው ገልጸዋል።

የአንድነቱ አባላት አስተያየትና ሃሳብ የሰጡ ሲሆን የእርስ በርስ ትውውቅ መፍጠር ብቁ ዜጋና በሥነ ምግባርና በሃይማኖት ተኮትኩቶ ማድረግ ቢቻል በዕቅድ መመራት ቢቻል ሥርዓተ ትምህርት መማር የሚችሉበት በቀጣይ ለሰንበት ት/ቤት አንድነት ተከታታይ ኮርስ እንዲሰጥ በተመረጡ ርዕሰ ጉዳዮች ትምህርት እንዲሰጥ የጠየቁ ሲሆን የሀገረ ስብከተ ወንጌል ክፍል ተተኪ ሰባኪያን ለማፍራት ሥልጠናውን ከሚመለከተው የሀገረ ስብከቱ ክፍል ጋር ተቀናጅቶ ተግባሩን ለመፈጸም ቃል ተገብቷል።

የሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ ሊቀትጉሃን ቀሲስ ሀብታሙ አበበ የሰንበት ት/ቤች አንድነት ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጠው ጥቅም ጥቂቶቹን እንደሚከተለው አቅርበዋል ።

– ዐቅምን ለማስተባበር
በየትም ቦታ ያሉ ሰንበት ት/ቤቶች በተናጠል ለቤተ ክርስቲያን በመስጠት ላይ ያሉት አገልግሎት ከፍተኛ ነው፡፡

– ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ለመጠበቅ
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ተባብሮ ለመጠበቅ እና ለማስጠበቅ እንደሚረዳ ፡፡

– ልምድ ለመለዋወጥ
የሰንበት ት/ቤቶችን ዕድገት አዝጋሚ ካደረጉት ምክንያቶች ዋነኛው የልምድ አለመለዋወጥ ነው፡፡ አዳዲስ ሰንበት ት/ቤቶች ከቀደምቶቹ ስህተትም ሆነ ጠንካራ ጎን የሚማሩበት አጋጣሚ በጣም አነስተኛ ነው ማለት ይቻላል፡፡

– መንፈሳዊ ጉባኤዎችን በማዘጋጀት፡-
ሰንበት ት/ቤቶች በየሳምንቱ በየደብራቸው ከሚያደርጉት መርሐ ግብር በተጨማሪ እንደ ጊዜው አመቺነት የተወሰነ ወቅት በአንድነት የሚያዘጇቸው ጉባኤያት ቢኖሩ ከፍተኛ ጥቅም ያስገኛሉ፡፡ አያጠያይቅም ፡፡

– የውይይት መድረኮችን በመፍጠር፡-
ከመንፈሳዊ ትምህርት በተጨማሪ ስለ ሰንበት ት/ቤቶች ችግሮችና መፍትሔያቸው፤ ስለ አሠራርና አወቃቀራቸው፤ ስለ ወቅታዊ ሁኔታዎች…ወዘተ የሚነጋገሩበት /የሚወያዩበት/ ጉባኤ ሊዘጋጅ ይገባል፡፡
በውይይትና በጥናታዊ ጉባኤዎቻቸንም ላይ በሚገባ የተጠኑ የመፍትሔ ሐሳብን የሚያመላክቱ ጥናቶች እንዲቀርቡ ሰንበት ት/ቤቶች የዐቅማቸውን መሞከር አለባቸው፡፡

– ትምህርታዊ ጉብኝቶችን በማድረግ፡-
በአሁኑ ወቅት በሰንበት ት/ቤቶቻችን መካከል የአሠራር ልዩነት እንዳለ ይታወቃል፡፡ በርግጥ መሠረታዊ ከሆኑ ጉዳዮች ሌላ የግድ አንድ ዓይነት አሠራር ይኑር ማለት ያስቸግራል፡፡ ምክንያቱም የአሠራር ዘዴው የየሰንበት ት/ቤቶቹን የሰው ኃይል፤ልምድና ዐቅም ይጠይቃልና ነው፡፡

– ዝግጅትን መለዋወጥ
የአንዱ ሰንበት ት/ቤት የተወሰኑ አባላት ወደሌላ ሰንበት ት/ቤት ሄደው ዝግጅቶቻቸውን፤ ትምህርት፤ መዝሙር፤ ሥነ ጽሑፍ፤ድራማ…ቢያቀርቡ መልካም ልምድ የመለዋወጫ አጋጣሚ እንደሚሆን ገልጸዋል።

በመጨረሻም የሰንበት ት/ቤቱን አንድነት የሚመሩ ሥራ አስፈፃሚ የተመረጡ ሲሆን በአባላቱ ፊት ቃለ መሐላ በመፈጸም መርሐ ግብሩ ተጠናቋል።
መረጃው የሀገረ ስብከቱ ሕዝብ ግንኙነት ነው።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • የድሬዳዋ ሳባ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ያስገኘባው ባለ ሦስት ወለል ሁለገብ ሕንጻ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጸሎተ ቡራኬ በዛሬው ዕለት ተመረቋል።
  • የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን ዕድሳት ተጠናቆ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ተባረከ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ ወደ ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ተጓዘ።
  • አሐዱ ባንክ ላደረገው ሁለተናዊ እገዛ በቋሚ ሲኖዶስ የእውቅናና የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበረከተለት።
  • የመቱ ፈለገ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ የመጀመሪያውን ዙር እጩ መምህራን በደማቅ ሥነ ሥርዓት አስመረቀ

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የቤተክርስቲያን ተወካዮች በግብፁ ጉባኤ ላይ ያልተገኙት በግል በገጠማቸው እክል ምክንያት መሆኑን የውጭ ግንኙነቱ መምሪያ አስታወቀ። Link to: የቤተክርስቲያን ተወካዮች በግብፁ ጉባኤ ላይ ያልተገኙት በግል በገጠማቸው እክል ምክንያት መሆኑን የውጭ ግንኙነቱ መምሪያ አስታወቀ። የቤተክርስቲያን ተወካዮች በግብፁ ጉባኤ ላይ ያልተገኙት... Link to: ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የመስቀል ደመራ በዓል ፍጹም ደማቅ እና ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር የከተማ አስተዳደሩ እያደረገ ላለው ስራ ምስጋና አቅርበዋል። Link to: ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የመስቀል ደመራ በዓል ፍጹም ደማቅ እና ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር የከተማ አስተዳደሩ እያደረገ ላለው ስራ ምስጋና አቅርበዋል። ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የመስቀል ደመራ በዓል...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top