የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የጉባላፍቶ ወረዳ ቤተክህነት የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤውን አካሒዷል

September 24, 2024

መስከረም 14 ቀን 2017 ዓ.ም

በሰሜን ወሎ መንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት ቤተክህነት የጉባላፍቶ ወረዳ ቤተክህነት ጽ/ቤት 43ኛ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤውን ትናንት በወልድያ የጁ የባሕል ማዕከልና ቤተመዘክር አካሒዷል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የሀገረ ስብከታችን ዋና ሥራ አስኪያጅና ዋና ጸሓፊ ወረዳ ቤተክህነቱ ያስገነባውን ባለ 3 (፫) ወለል የገቢ ማስገኛ ሕንጻ ጎብኝተዋል፤ ብፁዕነታቸው በመሰብሰቢያ አዳራሹ ተገኝተው ጉባኤውን በመምራት ትምህርትና አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል።

በ2016 የአገልግሎት ዓመት ወረዳ ቤተክህነቱን ጨምሮ በገዳማት፣ አድባራትና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት የተከናወኑ የተግባራት አፈጻጸም ሪፖርትና የሀገረ ስብከቱን ዓመታዊ እቅድ መነሻ በማድረግ የተዘጋጀውን የወረዳ ቤተክህነት የ2017 ዓ.ም ዓመታዊ እቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

የመረጃ ምንነት፣ አስፈላጊነትና አደረጃጀትን አስመልክቶ በሀገረ ስብከቱ የዳታቤዝ ባለሙያ ገለጻ ተደርጓል። የቤተክርስቲያኗን አጠቃላይ መረጃዎች አደራጅቶ ለመያዝ ታስቦ የተዘጋጀው ቅጽ ላይም ማብራሪያ ተሰጥቷል። በብፁዕ አቡነ ኤርምያስ መመሪያ ሰጭነት በሀገረ ስብከቱ በተያዘው የአገልግሎት ዓመት ልዩ ትኩረት የተደረገባቸው ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በተመለከተ በሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሓፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ሊቀ ጳጳስ በእቅድ የተያዙ ተግባራት በሀገረ ስብከቱ፣ በወረዳ ቤተክህነቱ፣ ገዳማትና አድባራት በመደጋገፍ መሥራት እንደሚገባ የቤተክርስቲያኗ ገንዘብና ሀብትን በአግባቡ ማስተዳደር፣ ብልሹ አሠራርን መቀነስና የአብነት ትምህርት ቤቶች ላይ በትኩረት እንዲሠራ አባታዊ መመሪያ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም በወረዳ ቤተክህነቱ ከሚገኙት 182 አብያተ ክርስቲያናት መካከል በተጠናቀቀው የአገልግሎት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሰበካ ጉባኤያትና ግለሰቦች ዕውቅና ተሰጥቷል።

ደብረ ሮሐ ቅዱስ ላሊበላን ጨምሮ በሀገረ ስብከቱ 14 ወረዳ አብያተ ክህነት እንደሚገኙ የሚታወስ ነው።

መረጃው የሀገረ ስብከቱ ሕዝብ ግንኙነት ነው።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የመስቀል ደመራ በዓል ፍጹም ደማቅ እና ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር የከተማ አስተዳደሩ እያደረገ ላለው ስራ ምስጋና አቅርበዋል። Link to: ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የመስቀል ደመራ በዓል ፍጹም ደማቅ እና ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር የከተማ አስተዳደሩ እያደረገ ላለው ስራ ምስጋና አቅርበዋል። ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የመስቀል ደመራ በዓል... Link to: በሲዳማ ሀገረ ስብከት የ2017 ዓ/ም የመስቀል በዓል ዝግጅትን አስመልክቶ በብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ሰብሳቢነት ውይይት ተደረገ። Link to: በሲዳማ ሀገረ ስብከት የ2017 ዓ/ም የመስቀል በዓል ዝግጅትን አስመልክቶ በብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ሰብሳቢነት ውይይት ተደረገ። በሲዳማ ሀገረ ስብከት የ2017 ዓ/ም የመስቀል በዓል...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top