መስከረም 16/2017 ዓ/ም

በበዓሉ ላይ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ፣ ክቡር ሊቀ ኅሩያን ቆሞስ አባ ፍቅረ ዮሐንስ ብርሃኑ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ መልአከ ምሕረት አበበ ወ/አማኑኤል የሀገረ ስብከቱ ም/ሥራ አስኪያጅ ፣ የሀገረ ስብከቱ የየክፍል ኃላፊዎች ፣ የየአድባራቱ አስተዳዳሪዎችና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ የከተማው ዋና ከንቲባ አቶ መሐመድ(ቡሌ) ዑመር፣ የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር በያን እና በርካታ የከተማው ሕዝበ ክርስቲያን የተገኙ ሲሆን፣ በበዓሉ ላይ ብፁዕነታቸው ትምህርተ ወንጌልና ቃለ-ምዕዳን የሰጡ ሲሆን፣ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ቆሞስ አባ ፍቅረ ዮሐንስ ብርሃኑ የከተማው ከንቲባና የከተማው ፖሊስ አዛዥ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም ደመራው በብፁዕነታቸው ተባርኮ ተለኩሶ የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል። በዓሉ ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም ተከብሯል። ጸጥታውን በማስከበር የበኩላቸውን ድርሻ ለተወጡ የጸጥታ አካላት በሙሉ ሀገረ ስብከቱ ልባዊ ምስጋናውን አቅርቧል!

መረጃው የምዕራብ ሀረርጌ ህዝብ ግንኙነት ክፍል ነው።