የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

በቤተክርስቲያን ለውጥና እድገት እንዲመጣ በመሻት ምእመናን የሚሰጡትን በቅንነት ተቀብሎ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ።

October 10, 2024

መስከረም 26 ቀን 2017 ዓ.ም
+ + +

በሰሜን ወሎ መንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት ቤተክህነት የወልድያ ከተማ አስተዳደር ቤተክህነት ጽ/ቤት 43ኛ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤውን ትናንት መስከረም 25 ቀን 2017 ዓ.ም በወልድያ መንበረ ንግሥት ኪዳነ ምሕረት የሰንበት ት/ቤት አዳራሽ አካሒዷል።

በብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቡራኬና መሪነት በተካሄደው በዚሁ ጉባኤ የ2016 ዓ.ም የከተማ አስተዳደር ቤተክህነቱ የሥራ ክንውን ሪፖርትና ከቤተ ክርስቲያኗ የ10 ዓመት መሪ ዕቅድ የተቀዳ መንፈሳዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የ2017 ዓ.ም ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

ስብከተ ወንጌልን በማጠናከር፣ ገዳማትና አድባራት የራስ አገዝ ልማትን በማስፋፋትና ሰንበት ትቤቶችን በማጠናከር አበረታች ሥራዎች መከናወናቸውን የወረዳ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ጥበባት አክሊለ ብርሃን ተመስገን ባቀረቡት ሪፖርት አመላክዋል፡፡

የመረጃ ምንነት፣ አስፈላጊነትና አደረጃጀትን አስመልክቶ በሀገረ ስብከቱ የዳታቤዝ ባለሙያ ገለጻ የተደረገ ሲሆን የቤተክርስቲያኗን አጠቃላይ መረጃዎች አደራጅቶ ለመያዝ ታስቦ የተዘጋጀ ቅጽ ላይም ማብራሪያ ተሰጥቷል። የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ብርሃን ፍሥሐ ጌታነህ በመሪ እቅድ ትግበራ፣ በሰንበት ትምህርት ቤቶች መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት ታስቦ የተዘጋጀው ሥርዓተ ትምህርት አተገባበር፣ ብልሹ አሠራርን መቀነስና በአገልጋይነት መንፈስ መሥራት እንዲሁም መልካም አስተዳደር ማሻሻልን አስመልክተው መልእክት አስተላልፈዋል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቃለ ምዕዳንና የሥራ መመሪያ የሰጡ ሲሆን ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ያሏቸውን አገልጋዮችና ተገልጋዮች ልማድን አስወግደው ለምሥጢራተ ቤተክርስቲያን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ፣ በቤተክርስቲያን የሚስተዋሉ ብልሹ አሠራሮችን ለማስቀረት የቤተክርስቲያኗን መሪ እቅድ በአግባቡ እንዲተገበር፣ የልኅቀት ማእከላትን በማስፋፋት ተተኪ ሊቃውንትንና መነኮሳትን ለማፍራት በትኩረት እንሠራለን ብለዋል።

ቤተክርስቲያን በመንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዋ ተጨባጭ ለውጥ እንድታስመዘግብ መሪ እቅዱን በቁርጠኝነት መተግበር ይገባል ያሉት ብፁዕነታቸው የአብነት ትምህርት ቤቶችና የሰንበት ትምህርት ቤቶችን በማጠናከር ተተኪ ሊቃውንትንና ምእመናንን ለማፍራት ኹሉም የድርሻውን እንዲወጣ አባታዊ መመሪያ አስተላልፈዋል።

በቤተክርስቲያን ለውጥና እድገት እንዲመጣ በመሻት ምእመናን የሚሰጡትን ሀሳብ ኸሉም በተሠማራበት በቅንነት ተቀብሎ ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ብለዋል። በጉባኤው ብፁዕነታቸውን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የወልድያ ከተማ አስተዳደር ቤተ ክህነትና የጉባላፍቶ ወረዳ ቤተ ክህነት ኀላፊዎች፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎችና የሰበካ ጉባኤ አባላት ፣ የሰንበት ትምህርት ቤትና የማኅበረ ቅዱሳን ወልድያ ማእከል ተወካዮች ተሳትፈዋል።

በተጠናቀቀው የአገልግሎት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሰበካ ጉባኤያት፣ ተቋማትና ግለሰቦች የዕውቅና ሽልማት ተሰጥቷል።

መረጃው የሀገረ ስብከቱ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ነው

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በመንበረ ጵጵስናና ወናጎ ወረዳ ቤተክህነት ለሚገኙ አብያተክርስቲያናት በልማት ዙሪያ ሥልጠና ተሰጠ!! Link to: በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በመንበረ ጵጵስናና ወናጎ ወረዳ ቤተክህነት ለሚገኙ አብያተክርስቲያናት በልማት ዙሪያ ሥልጠና ተሰጠ!! በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በመንበረ ጵጵስናና... Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የማኅበራት ምዝገባ፣ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ ፈቃድ ከተሰጣቸው ማኅበራት ጋር የምክክርና የውይይት መርሐ ግብር እየተካሔደ ነው። Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የማኅበራት ምዝገባ፣ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ ፈቃድ ከተሰጣቸው ማኅበራት ጋር የምክክርና የውይይት መርሐ ግብር እየተካሔደ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top