የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ኮሚቴው የማጣራት ሥራው የደረሰበትን ደረጃ በተመለከተ ለጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ ሪፖርት አቀረበ።

October 10, 2024

መስከረም ፳፰ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
“”””””””””””””””””””””””””””””””
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
=============

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተዳደር ጉባኤ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚስተዋለውን የግብረ ሙስናና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እንዲሁም እሱን ተከትሎ በጠቅላይ ቤተክህነት የሚታዩ ክፍተቶችን በመመርመር የውሳኔ ሐሳብ ጭምር እንዲያቀርብ የተቋቋመው ኮሚቴ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ እስካሁን ያከናወናቸውንና ወደፊት የሚያከናውናቸውን ተግባራት በተመለከተ ሪፖርት አቅርቧል።

ጉባኤውም በቀረበለት ሪፖርት ዙሪያ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ በቀጣይ ኮሚቴው በትኩረት ሊሰራባቸው በሚገቡ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ መመሪያ ሰጥቷል።በተለይም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ምርመራን ተከትሎ ሀገረ ስብከቱን ለመገንጠልና የቤተክርስቲያን አካላት የሆኑ ምዕመናን ሊያጣሩን አይገባም የሚለው ሀሳብ ቤተክርስቲያንን የሚከፋፍል ተግባር በመሆኑ ጉባኤው በጽኑ አውግዞታል።

አጣሪ ኮሚቴው አስተዳደር ጉባኤው በሰጠው አቅጣጫ መሰረት ቤተክርስቲያንን ወደ ክብሯ ለመመለስ በሚያስችል መልኩ ተቋምን መሰረት በማድረግ ብቻ ቤተክርስቲያንን ሊታደግና ለውጥ ሊያመጣ በሚችል አግባብ ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጦል መመሪያ በመስጠት የሚከተለውን ውሳኔ አስተላልፏል።

የአስተዳደር ጉባኤው ፍላጎትም ሆነ የአጣሪ ልዑኩ ተልዕኮ በተለያዩ ሚዲያዎች የጠፋውን የቤተ ክርስቲያንን ክብር በማስመለስ ቤተ ክርስቲያናችንን ወደጥንተ ክብሯ መመለስ በመሆኑ፡-
፩. አሁን ያለንበት ወቅት 43ኛው አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የሚካሔድበት ወቅት በመሆኑና ጠቅላይ ጽ/ቤቱም ይህ ታሪካዊ ጉባኤ በስኬት እንዲጠናቀቅ እየሠራ የሚገኝ በመሆኑ የጠቅላይ ጽ/ቤቱን እና የቤተ ክርስቲያናችንን ሥራ የሚያደናቅፍ በሀ/ስብከቱ እና በአንዳንድ አድባራትና ገዳማት ኢ-መደበኛ የሆነ ሰላምን የሚያደፈርስ ሁከትን የሚያስከትል ምንም ዓይነት ስብሰባ እንዳይካሔድ ለሀ/ስብከቱ መመሪያ እንዲተላለፍ ሆኖ የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ዓለም አቀፍ ስብሰባ ለማካሔድ በዝግጅት ላይ መሆኑን በመገንዘብ ጉዳዩን በመከታትል እርምት እንዲያደርጉና የሕግ ከለላ እንዲሰጡ በደብዳቤ እንዲገለጽ ይደረግ፤

፪.ቅዱስ ሲኖዶስ ከማጣራት ሒደቱ ተነስቶ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ከመሬት ኪራይ እንዲሁም ተመሳሳይ ከሆኑ የቋሚ ንብረቶች ጋር ተያይዞ የሚደረጉ ውሎች እንዳይፈጸሙ ለሀ/ስብከቱ ጥብቅ መመሪያ በጽሑፍ እንዲተላለፍ ይደረግ፤

፫. በጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ጉባኤ በሀ/ስብከቱ የተፈናቀሉ አገልጋዮችን እንዲያስመልስ ከተሰየመው ኮሚቴ ጋር በመነጋገር የተፈናቀሉ ሠራተኞችን ከመመለስ ውጪ በዚህ ሰበብ የሚደረጉ ቅጥሮችና ዝውውሮች ተቀባይነት የሌላቸው መሆኑ ታውቆ ምንም ዓይነት ቅጥርና ዝውውር እንዳይፈጸም ለሀ/ስብከቱ ጥብቅ መመሪያ በጽሑፍ እንዲተላለፍ ይደረግ፤

፬. የማጣራት ሒደቱን ተከትሎ ሀ/ስብከቱ ጉዳዩን ለማድበስበስና የተለየ ስያሜ ለመስጠት ከሀ/ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች ጀምሮ የአንዳንድ አድባራትና የገዳማት አስተዳዳሪዎችን፣ጸሐፊዎችን፤ ሒሳብ ሹሞችንና ቁጥጥሮችን በመሰብሰብ የሚደረገው የአድማ ስብሰባ የቤተ ክርስቲያንን ክብር ዝቅ የሚያደርግና ለችግሩ መፍትሔ የማይሆን ከመሆኑም በላይ በሁሉም የቤተ ክርስቲየናችን ሕጎችና ደንቦች አድማ ማድረግ የተከለከለ መሆኑ ታውቆ ሀ/ስብከቱ ከዚህ ድርጊቱ እንዲቆጠብ መመሪያ እንዲተላለፍ እንዲሁም የሚመለከተው የመንግሥት የጸጥታ አካል ይህን የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ህገወጥ ድርጊትን በተመለከተ ድርጊቱ ከጠቅላይ ጽ/ቤቱ እውቅና ውጭ መሆኑን ተገንዝቦ አስፈላጊውን የሕግ ማስከበር ሥራ እንዲሠራ በደብዳቤ እንዲገለጽ ይደረግ፤

፭..አጣሪ ኮሚቴው አስተዳደር ጉባኤው በሰጠው አቅጣጫ መሠረት ቤተ ክርስቲያንን ወደ ክብሯ ለመመለስ በሚያስችል መልኩ ተቋምን መሠረት በማድረግ ብቻ ቤተ ክርስቲያንን ሊታደግና ለውጥ ሊያመጣ በሚችል አግባብ ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ይደረግ በማለት ወስኖ የዕለቱ ስብሰባ በብፁዕነታቸው ጸሎት ተጠናቋል፡፡

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጅ ሀገረ ስብከት ጳጳስ በልዩ ልዩ የሙያ ዘርፍ ተሰማርተው በአዲስ አበባ ከሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ጋር በሀገረ ስብከቱ በሚከናወኑ ዕቅዶች ዙሪያ ውይይት አደረጉ። Link to: ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጅ ሀገረ ስብከት ጳጳስ በልዩ ልዩ የሙያ ዘርፍ ተሰማርተው በአዲስ አበባ ከሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ጋር በሀገረ ስብከቱ በሚከናወኑ ዕቅዶች ዙሪያ ውይይት አደረጉ። ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጅ ሀገረ ስብከት... Link to: በህገ ወጥ መንገድ ተሠብሮ ከአገልግሎት ውጪ የነበረው  የምዕራብ ወለጋ መንበረ ጵጵስና   ጥገና ተደገርጎለት  በሰባቱ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ተባርኮ  ዳግም አገልግሎት  መስጠት ጀመረ። Link to: በህገ ወጥ መንገድ ተሠብሮ ከአገልግሎት ውጪ የነበረው  የምዕራብ ወለጋ መንበረ ጵጵስና   ጥገና ተደገርጎለት  በሰባቱ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ተባርኮ  ዳግም አገልግሎት  መስጠት ጀመረ። በህገ ወጥ መንገድ ተሠብሮ ከአገልግሎት ውጪ የነበረው ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top