የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት የሕግ አገልግሎት መምሪያ ሥር የተቋቋመው የሕግ ባለ ሙያዎች ዐቢይ ኮሚቴ ጠቅላላ ጉባኤ አካሔደ።

October 15, 2024

ጥቅምት 3 ቀን 2017 ዓ.ም.
+ + +

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት የሕግ አገልግሎት መምሪያ ሥር የተቋቋመው የሕግ ባለሙያዎች ዐቢይ ኮሚቴ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ለቅድስት ቤተክርስቲያን ሕግ ተኮር የሆኑ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እየሠራ የቆየ መሆኑን ተገልጿል።

ጉባኤው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕዳርና የሰሜን ጎጃም እህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የየመሪያ ኀላፊዎች ፣ የሕግ ባለሙያዎች ዐቢይ ኮሚቴ አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው የሕግ ባለሙያዎች በተገኙበት ተካሂዷል።

ጉባኤው በሕግ አገልግሎት መምሪያ ኀላፊው አፈ መምህር አባ ገብረ ሥላሴ (ቆሞስ) የተመራ ሲሆን ጠበቃ አያሌው ቢታኔ የአፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል። በሪፖርቱም የሕግ ባለሙያዎች በቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪ ተደርጎላቸው ሥራ ከጀመሩበት ከጥቅምት 3 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ለቤተክርስቲያን ዘርፈ ብዙ የሙያ አገልግሎት እየሰጠ የቆየ መሆኑ ተገልጿል።

ይህ የባለሙያዎች ዐቢይ ኮሚቴ ለቤተክርስቲያን ሲሰጣቸው ከነበረውና ወደፊትም የሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል የችሎት ክርክርና የምክር አገልግሎት ፣ የሕግ ማርቀቅና የሰነድ ዝግጅት፣ የሕግ ጥናት፣ ምርምርና ስልጠና፣ የመረጃ መሰብሰብ ፣ ማጠናቀርና መተንተን ፣ የንቃተ ሕግ ግንዛቤ መፍጠር እና የመሳሰሉትን አገልግሎቶች እንደሆነ ተገልጿል።

በጉባኤው ላይ የተገኙት ነባርና አዳዲስ ባለሙያዎች ለአገልግሎቱ መሳካት ትልቅ አስተዋጽዖ እንደሚያደርጉ በመግለጽ የአባልነት ፎርም ያልሞሉ አባላትም በተዘጋጀው የአባልነት መሙያ ሰንጠረዥ ላይ ሞልተዋል ።

ከአፈጻጸም ሪፖርቱ በመቀጠል ወደፊት ከአህጉረ ስብከት ጋር በሚካሄደው ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ላይ አቅጣጫ የሚያሳይ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቧል። በቀረበው ጥናታዊ ጽሑፍ መሠረት ዐቢይ ኮሚቴው በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ብቻ ተወስኖ እንዳይቀር ወደ ሀገረ ስብከቶች እንዴት ማውረድ እንደሚቻል አቅጣጫ ሰጥቷል።

በመጨረሻም ጥሩ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ጠበቆች በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክልነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣በባሕርዳር እና ሰሜን ጎጃም አሕጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቡራኬ የምስጋናና የምስክር ወረቀት ተሰጥቶ በምዕራብ ጎንደር ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሰላማ ጸሎት ተደርጎ የጉባኤው ፍጻሜ ሆኗል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • የድሬዳዋ ሳባ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ያስገኘባው ባለ ሦስት ወለል ሁለገብ ሕንጻ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጸሎተ ቡራኬ በዛሬው ዕለት ተመረቋል።
  • የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን ዕድሳት ተጠናቆ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ተባረከ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ ወደ ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ተጓዘ።
  • አሐዱ ባንክ ላደረገው ሁለተናዊ እገዛ በቋሚ ሲኖዶስ የእውቅናና የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበረከተለት።
  • የመቱ ፈለገ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ የመጀመሪያውን ዙር እጩ መምህራን በደማቅ ሥነ ሥርዓት አስመረቀ

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ኹለተኛው የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃና መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የ12ኛ ክፍልን ያጠናቀቁ ተማሪዎች የምርቃት መርሐ ግብር በጠቅላይ ቤተክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ ተከናወነ። Link to: ኹለተኛው የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃና መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የ12ኛ ክፍልን ያጠናቀቁ ተማሪዎች የምርቃት መርሐ ግብር በጠቅላይ ቤተክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ ተከናወነ። ኹለተኛው የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃና መምሪያ የሰንበት... Link to: ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በ፵፫ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ያስተላለፉት መልዕክት፤ Link to: ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በ፵፫ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ያስተላለፉት መልዕክት፤ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በ፵፫ኛው አጠቃላይ የሰበካ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top