የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የሸገር ማረሚያ ቤት ታራሚዎች እውቀትና ጉልበታቸውን በማስተባበር ቤተክርስቲያን በማነጽ ላይ ናቸው።

December 27, 2024

ታኅሣሥ ፲፬ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም

በሸገር ማረሚያ ቤት የሚገኙ የሕግ ታራሚዎች ማረሚያ ቤቱ ለአምልኮ ቦታ በሚል በሰጣቸው ቦታ ላይ እውቀታቸውንና ጉልበታቸውን በማስተባበር ልዩ ስሙ ዳለቲ በተባለ ቦታ የማርያም ቤተክርስቲያንን በማነጽ ላይ መሆናቸው ተገለጸ።

የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ በማረሚያ ቤት የሚገኙ የሕግ ታራሚዎችን ለማጽናናትና ለማስተማር በያዘው ዕቅድ መሰረት ታኅሣሥ ፲፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም በማረሚያ ቤቱ በመገኘት የማጽናኛ ትምህርት በመስጠት የታራሚዎችን የልማት ሥራ ጎብኝቷል።

የመምሪያው የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ፣የመምሪያው ዋና ኃላፊ መ/ሰ ቆሞስ አባ ቃለጽድቅ ሙሉጌታ( ዶ/ር) ማረሚያ ቤቱን በጎበኙበት ወቅት በሕግ ታራሚዎቹ እየታነጸ የሚገኘውን ሕንጻ ቤተክርስቲያን ተዛውረው ከተመለከቱ በኋላ በሕግ ታራሚዎቹ እየተሰራ ያለውን መልካም ሥራ በማድነቅ በመምሪያው በኩል አስፈላጊው ድጋፍ ሁሉ እንደሚደረግላቸው ቃል ገብተዋል።

በዚሁ ጊዜም ትምህርተ ወንጌል በመምሪያ ኃላፊው የተሰጠ ሲሆን ቀመምሪያው ሊቀ ጳጳስም ቃለ በረከትና ቡራኬ ተሰጥቷል።የጉብኝቱ ዓላማም ስብከተ ወንጌልን በማረሚያ ቤቶች ጭምር ለማዳረስ ነው።

የማረሚያ ቤቱ ኃላፊ ኢኒስፔክተር ቀበና ለሕግ ታራሚዎቹ የአምልኮ ቦታ የተሰጠው ታራሚዎቹ ከቤተክርስቲያን በሚያገኙት የወንጌል አገልግሎት በስነምግባር የበለጠ የሚታነጹበት አእድል እንደሚፈጠር ተቋማቸው ስለሚያምን መሆኑን ገልጸው ይህ ቤተክርስቲያን እንዲታነጽ መቀቀዱንና በፍጥነት ቤተክርስቲያኑ ታንጾ አገልግሎት መስጠት ይችል ዘንድ የሚመለከታቸው ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ በሌሎች ማረሚያ ቤቶችም ተመሳሳይ ጉብኝት እኔደሚያደርግና የስብከተ ወንጌል አገልግሎቱንም በተጠናከረ መልኩ ለመቀጠል ዕቅድ መያዙ የሚታወቅ ሲሆን በሸገር ማረሚያ ቤት በመታነጽ ላይ ለሚገኘው ሕንጻ ቤተክርስቲያንም በጎ አድራጊዎችን በማስተባበር ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው ቃል መገባቱን ከመምሪያው ዋና ኃላፊ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች
  • ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በሀገረ ስብከቱ ለካህናት የሚሰጠውን ሥልጠና በጸሎትና በቡራኬ አስጀመሩ።
  • ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ተገኝተው የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዐን አባቶችን መደበ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን የልዑካን ቡድን ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የአባታችን የጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በእዣ ወረዳ ቤተክህነት በገጨ ምዕራፈ ቅዱሳን ቅዱስ አቡነ ሳሙኤል ወቅዱስ ዕሩፋኤል ገዳም በድምቀት ተከብሮ ዋለ። Link to: የአባታችን የጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በእዣ ወረዳ ቤተክህነት በገጨ ምዕራፈ ቅዱሳን ቅዱስ አቡነ ሳሙኤል ወቅዱስ ዕሩፋኤል ገዳም በድምቀት ተከብሮ ዋለ። የአባታችን የጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ዓመታዊ ክብረ... Link to: በቡፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንየልዑካን ቡድን ድሬዳዋ አየር ማረፊያ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። Link to: በቡፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንየልዑካን ቡድን ድሬዳዋ አየር ማረፊያ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። በቡፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ የኢትዮጵያ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top