ሰኔ ፳፪ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ/ ም
******
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
+++++++++++++
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ተምሮ ማስተማር ሰንበት ትምህርት ቤት ዘመናዊ ስቱዱዮ ተዘጋጅቶ የሚተላለፉ ማንኛቸውም ትምህርቶች ፣ መዝሙራት ፣ ቪዲዮዎች ፣ ቃለ መጠይቆች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዶግማና ቀኖናን የጠበቁ መሆናቸው ሙሉ የአርትኦት / ኦዲቶርያል ስራዎች/ ከገዳማችንና ከሰንበት ትምህት ቤታችን በተመደቡ አባቶች እና መምህራን አማካኝነት ሲረጋገጥ ብቻ እንዲተላለፍ በማድረግ የሚሰራ ሲሆን በዚህ መሠረት የቤተ ክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ መንፈሳዊ ጽሑፎችን ፣ ትምህርቶችን እና መዝሙራትን በማቅረብ ምዕመናን ወደ ንስሀና ወደ ቅዱስ ቁርባን እንዲቀርቡ ለማድረግ ፣ የቤተ ክርስቲያንን ታሪካዊ ቦታዎች ማስተዋወቅ ፣ የቤተ ክርስቲያን አባቶችንና መምህራንን የህይወት ተሞክሮ ለትውልዱ በማስተዋወቅ አሰረ ፍኖታቸውን እንዲከተሉ ፣ የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያም ፣ የጻድቃን ሰማዕታት ተጋድሎ እና ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን ጸጋ ለማስተዋወቅ ብቻ እንዲተላለፉ በማድረግ የሚሰራ ሲሆን ፣የቤተክርስትያንን ስርዓቶች ለትዉልዱ ለማስተዋወቅ፣ ትዉልዱ ምንነታቸዉን ተረድቶ እንዲጠቀምባቸዉ እና እንዲጠብቃቸው ፣መስማት ለተሳናቸዉ የቤተክርስትያኒቱ ልጆች በቋንቋቸዉ ተከታታይ ትምህርቶችን እንዲማሩ ለማድረግ፤ የቤተክርስትያናችንን፤ የገዳማችንን እና የሰንበት ት/ቤታችንን መንፈሳዊ እና የልማት ስራዎችን ለምዕመና ይሀንን ለትዉልዱ እና ለቤተክርስትያን ጠቃሚነቱ የታመነበትን (ዘመናዊ ስቱዱዮ ) ገንብተን ስራ ለማስጀመር፣ ለዚሀ የምረቃ ቀን እንድንበቃ ለረዳን ለመድኃኔዓለም ክብርና ምስጋና ይሁን በማለት ብፁዕነታቸውን እና የገዳሙን አስተዳደር ጽ/ቤት አመስግነዋል ።
በዕለቱም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ የቅድስት ሥላሴ መንፋሳዊ ዩንቨርስቲ የቦርድ ሰብሳቢ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የደቡብ ምሥራቅ ትግራይና የራያ አህጉረ ስብከት፣ ሊቀ ጳጳስ፣ በመንበረ ፓትርያርክ የቅርሳ ቅርስ ጥበቃና ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ሙዚየም መምሪያ የበላይ ኃላፊ እና የማኅበራት ማደራጃ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የኢትዮ ሶማሊያ ጅግጅጋ አህጉረ ስብከት ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ጳጳስ መልዓከ ምህረት አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ የአዲስ አበባ ሥራ አስኪያጅ ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያው ኃላፊዎች ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የየመምሪያው ኃላፊዎች ፣ መጋቤ ኅሩያን አባ ኤልያስ በልሁ የጋዳሙ ዋና አስተዳዳሪ፣ የገዳሙ የአስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፣ የተምሮ ማስተማር ሥራ እልስፈጻሚዎች በመርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል ።
በመቀጠል ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በመልዕክታቸውም ይህ ዘመናዊ ስቱዱዮ መልካም ነገር የሚሰራበት የቤተ ክርስቲያንን ህግ ደንብ የጠበቀ አገልግሎት የሚሰጥ መሆን እንዳለበት ለቤተ ክርስቲያን ለቀጣይ ጉዞዋ አስፈላጊ ስለሆን እናንተም መበርታት መጠንከር ፣ መጸለይ አለባችሁ እኛም ይህንን መልካም ነገር ማየታችን በጣም ደስ ብሎናል ሲሉ አባታዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።
በተጨማሪም ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ከ24 ዓመት በፊት በዚህ ገዳም አስተዳዳሪ በነበርኩበት ወቅት ተምሮ ማስተማር አንጋፋ እና ስመጥር የሆኑ የሀገር ባለውለታዎች የሚፈልቁበት ነው በሰንበት ትምህርት ቤት በማኅበራት እንዲሁም በዘመናዊ ትምህርት ቤት በመጀመር ምስካየ ኅዙናን ቀዳሚ ነው እና ብዙ መልካም ስራዎች ከዚህ በኃላም እንደሚሰሩ ተስፋ አለኝ ሲሉ አባታዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈው በጸሎት የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል ።
©ምስካየኅዙናን መድኀኔዓለም ገዳም ሚዲያ