የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የቤተ ክርስቲያን ነገዎችን የተሻለ ለማድረግ ሥልጠና አስፈላጊ ነው ሲሉ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ ገለጹ።

February 10, 2026

የካቲት ፪/፳፻፲፰ ዓ/ም

የቤተ ክርስቲያን ነገዎችን የተሻለ ለማድረግ ሥልጠና አስፈላጊ ሲሉ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባና የስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ገለጹ።

ብፁዕነታቸው ይሄንን ያሉት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ከጥር 25_ የካቲት 6/2018 ዓ/ም በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች በሀገረ አቀፍ ደረጃ እንዲሰጥ ባስተላላፈው መምሪያ መሠረት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከአራዳ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት እየተሠጠ በሚገኘው የሥልጠና መርሐ ግብር ላይ ነው።

በሥልጠናው የመክፈቻ አባታዊ መምሪያና መልእክት ያስተላለፉት ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ ሥልጠናው በቤተ ክርስቲያን የሚኖረው ጥቅም ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

በተለይም ሥልጠና ሳይሠሩ ከትናትና ጋር ቆሞ ከመቅረትና ከመቆዘም የሚያድን የቤተ ክርስቲያን ነገዎችንም የተሻለ የሚያደርግ ነው ብለዋል።

ብፁዕነታቸው አክውም ዘመኑ ዋጅተን በሥልጠና ራሳችንን እያሻሻልን ማገልገል ካልቻልን የዘመን ተከታዮች እንጂ ቀዳሚ መሆን ታሪክ እንዳይሆንብን በጥንቀቄ መጓዝ አለብን ብለዋል።

በሥልጠናው የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አመሰራረት ታሪክ፣ሰበካ ጉባኤ የተመሰረተበት ዓላማ፣የሚስተዋሉትን ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው፣የሪፖሪት አቀራረብና አዘገጃጀት አስመልክቶ መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ቃለ ጽድቅ ሙሉጌታ (ዶ/ር) ስልጠና ሰጥተዋል።

በመቀጠልም “የሚዲያ አጠቃቀም በመንፈሳዊ ሕይወት ያለው ፋይዳ” በሚለው ርእስ መ/ር ማርቆስ ሥልጠናውን ሰጥተዋል።

በተነሡ የተለያዩ መወያያ ነጥቦች ላይ ውይይትና አስተያያት እንዲሁም ጥያቄ በተሳታፊዎች የተነሱ ሲሆን ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

ለጠቅላይ ቤተክህነት ልኡካን ከክፍለ ከተማው ቤተ ክህነት የምስጋና ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

የሰበካ ጉባኤ አሠራር ማጠናከርና ተደራሽነቱንጨማስፋት እንዲሁም ከዘመኑ ጋር ራሳችንን ማብቃት እንዳለብን መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አስገንዘበዋል።

በሥልጠናውና በምክክር መርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕነታቸውን ጨምሮ መልአከ ሰላም አባ ቃለ ጽድቅ ሙሉጌታ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰበካ ጉባኤ ማደረጃ መምሪያ ሐላፊና የዕለቱ አሰልጣኝ፣ መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ መምህር ማርቆስ ተበቃ በስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ የዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅና የዕለቱ አሠልጣኝ፣ መጋቤ ሠናያት የቻለው ለማ የክፍለ ከተማው ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው ሌሎች የሥራ ሐላፊዎች ተገኝተዋል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅጣጫ ሰጪነት እየታደሰ የሚገኘውን ዕድሜ ጠገቡን የወንጪ ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም ጎበኙ
  • ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ እየተገነባ ያለውን ዓለም አቀፍ የሥብሰባ አዳራሽ ጎበኙ
  • በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ተጀምሮ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ትጋት ለፍጻሜ የበቃው ባለ 480 ካሬ ሜትር ሁለገብ ሕንጻ ተመረቀ
  • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
  • ቅዱስ ሲኖዶስ በልማትና ዘመናዊ አሠራር ላይ ያተኮሩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ለ6 ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን የ2018 ዓ.ም የርክበ ካህናት ጉባኤውን አጠናቀቀ

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በሰበታ ገላን ጉዳና ፉሪ ክፍለ ከተማ የወለቴ ደብረ ገሊላ ቅዱስ በዓለ ወልድና ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የአዲስ ሕንፃ ቤተመቅደስ መሰረት ድንጋይ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገረ ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተቀመጠ። Link to: በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በሰበታ ገላን ጉዳና ፉሪ ክፍለ ከተማ የወለቴ ደብረ ገሊላ ቅዱስ በዓለ ወልድና ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የአዲስ ሕንፃ ቤተመቅደስ መሰረት ድንጋይ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገረ ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተቀመጠ። በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በሰበታ ገላን ጉዳና... Link to: በ18 ወራት ውስጥ ተሠርቶ ለፍጻሜ የበቃው የሔንቤቾ ደብረ ፀሐይ ብዙኃን ማርያም አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የወላይታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ተባርኮ በዛሬው ዕለት ከፍተኛ የመንግሥት ባለ ሥልጣናት በተገኙበት ቅዳሴ ቤቱ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ። Link to: በ18 ወራት ውስጥ ተሠርቶ ለፍጻሜ የበቃው የሔንቤቾ ደብረ ፀሐይ ብዙኃን ማርያም አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የወላይታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ተባርኮ በዛሬው ዕለት ከፍተኛ የመንግሥት ባለ ሥልጣናት በተገኙበት ቅዳሴ ቤቱ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ። በ18 ወራት ውስጥ ተሠርቶ ለፍጻሜ የበቃው የሔንቤቾ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top