የካቲት ፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፰ ዓ.ም
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣
የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ቤተክርስቲያን ለምታስገነባወቸው ሕንጻዎች የጨረታ ኮሚቴ በመሆንና በልዩልዩ የሙያ ዘርፎች ድጋፍ ላደረጉ ባለሙያዎች የዕወቅናና የምስጋና መርሐ ግብር በተካሔደበት ጊዜ ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት ክቡራን ልጆቻችን ቅድስት ቤተክርስቲያን ያደረገችላችሁን ጥሪ ተቀብላችሁ
ላበረከታችሁት ሙያዊ አስተዋጽኦ ምስጋናችን ይድረሳችሁ ካሉ በኋላ ይህንን የቤተክርስቲያን ጥሪ ተቀብላችሁ ጊዜና እውቀታችሁን አስተባብራችሁ ፈተናውን ሁሉ በጽናት አልፋችሁ ሠራችሁን በውጤታማነት ስላከናወናችሁ ቅድስት ቤተ ከርስቲያን ታመሰግናችኋለች ወደፊትም ጥሪዋን ተቀብላችሁ ተግባራዊ ምላሽ እንደምትሰጡ እምነታችን የጸና ነው
ብለዋል።

ባለሙያዎቹም ቤተክረስቲያን ላደረገችላቸው ምስጋናና ለሰጠቻቸው ዕውቅና በማመስገን የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው በማንኛውም ጊዜ ቤተክርስቲያን በምታደርግላቸው ጥሪና ሙያዊ አገልግሎታቸውን በምትፈልግበት ጊዜ ሁሉ ድጋፋቸውን ያለ ስስት ለመስጠት ቁርጠኛ መሆናቸውን በመግለጽ ቃል ገብተዋል።

ቤተክርስቲያን ሞሁራን ልጆቿን በማሳተፍ ለመጪው ትውልድ የሚተላለፍ ሁለንተናዊ የልማት ሠራዋን አጠናክራ የምትቀጥል መሆኑም የማኅበራዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጁ ፕሮፌሰር ግርማ ባቱ በመርሐ ግብሩ ላይ ገልጸው ለባለሙያዎቹ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በመቀጠልም ሊቀ ሥዩማን እስክንድር ገብረክርስቶስ የጠቅላይ
ቤተክህነት ሕዝብ ግኔኙነት መሥሪያ ኃላፊና የቤ/ሕ/አ/ል/ድርጅት ዋና ሥራ አክኪያጅ በበኩላቸው ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በመንፈሳዊ፣ማኅበራዊና ልማታዊ የሥራ ዘርፎች እያስመዘገቡ ያለውን ውጤት አድንቀው የቤተክርስቲያን ልጆች የሆናችሁ ባለሙያዎች የምታደርጉት ሙያዊ ድጋፍ ለቤተክርስቲያን ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ስላለው ምስጋና ይገባችኋል ካሉ በኋላ ለኸደፊትም ይኸው ትብብራችሁፐተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

በመጨረሻም ለኮሚቴ አባላቱ ቤተክርስቲያን ያዘጋጀችላቸውን የምስጋና የምስክር ወረቀት ከብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ተቀብለው የመርሐግብሩ ፍጻሜ ሆኗል።