የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት የድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት አቀረበ ።

February 26, 2026

የካቲት፱ቀን ፳፻ ፲ወ፰ ዓ.ም
++++++++++++++++
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
=============

በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ በተደረገው ሥራና ሠራተኛን የማገናኘት ሥራ ወደ ቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት የተመደቡት ክቡር ሊቀ ስዩማን እስክንድር ገብረክርስቶስ በፈጠሩት የአስተዳደር ንድፍ አማካኝነት የተጀመረው ደንበኛ ተኮር የአመራር ስልት መሠረት ሆድና ጀርባ በመሆን ለዘመናት ይኖሩ የነበሩ የድርጅቱን ሠራተኞች ደንበኞች የቤተሰብነት ስሜት መፍጠራቸውን ባለፉት 6 ወራት ውስጥ የተሠሩ ዝርዝር ሥራዎችን፣ እየተሠሩ ያሉና ወደፊት ሊሠሩ የታቀዱ ሥራዎችን የሚገልጽ ሪፖርት ቀርቧል።

ሪፖርቱ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የምስካየ ኅዙናን መድኀኔዓለም ገዳም የበላይ ኀላፊ ፣ ንቡረ ዕድ አልያስ አብርሃ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት በመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ፣ ረ/ፕ ግርማ ባቱ (ቀሲስ) የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ፣ ሊቀ መዘምራን ሐረገወይን ጫኔ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት የአስተዳደር መምሪያ ኃላፊ ፣ ሊቀ ስዩማን እስክንድር ገብረ ክርስቶስ የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅና የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ዋና ኀላፊ ፣ የቤቶችና ሕንፃዎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት በድረጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አማካኝነት ቀርቦ ከድርጅቱ የሥራ ኀላፊዎች ተጨማሪ ሐሳብ ተሰጥቶበታል።

በሪፖርቱ ድርጅቱ ደንበኛ ተኮር ስርዓት ዘርግቶ በሁሉም ሕንፃዎች ላይ የሚገኙ የነዋሪ ተዎካዮች በማቋቋም ሥራ እንዲጀምሩ በማድረግ ከሁሉም ነዋሪዎች ጋር ውይይት በማድረግ ሆድና ጀርባ ሆነው ሲኖሩ የነበሩት የድርጅቱ ደንበኞችና ሠራተኞች ወንድማማችነትን በማጎልበት በየኔነት ስሜት ድርጅቱ በሚያከናውናው የልማት ሥራውዎች ላይ ንቁ ተሳቶፎ እያደረጉ መሆኑ ተገልጿል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ድርጅቱና ነዋሪዎች እንዲሁም መላው የሚመለከተቸው አካላት የሚናቡበት የፌስቡክና የቴሌግራም ገጽ እንዲሁም የነዋሪዎች፣ የድርጅቱ ሠራተኞች የቴሌግራም ምዕላድ በመክፈት የተግባቦት ሥራውን በቀላል መንገድ እንዲካሄድ መደረጉንም የተገለፀ ሲሆን ዓለም አቀፍ ተደራሽነቱን ለማስፋት ድረ-ገጽ መክፈት መቻሉንም አብራርተዋል ድርጅቱ እስከዛሬ በመጣበት የገንዘብና የንብረት አስተዳዳር ስርዓት ወደፊት አንድ ደረጃ መራመድ እንደማይችል በመረዳት የቴክኖሎጂ አገልግሎት ጥቅም ላይ ለማዋል ከባንኮችና ከድርጅቶች ጋር ምክክር እየተደረገ መሆኑም ተገልጿል።

የድርጅቱ ሠራተኞች ሆነው በድርጅቱ ስም የግል ጥቅማቸውን ሲያሳድዱ የነበሩ ግለሰቦች ላይ እርምት በመውሰድ ድርጅቱን ከጥፋት ለመታደግ እንደተቻለና በርካታ ገንዘብ ወጥቶባቸው ተሠርተው የጥራት ጥያቄ የተነሰባቸውን የድረጅቱ ሕንፃዎች ማስተካከያ እንደተረገባቸው ተገልጿል።

ድርጅቱ በጽርሐ ምኒልክ ሕንፃና በተለያዩ የንግድ ቦታዎች ላይ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የጨረታ ኮሚቴዎች ጋር በመሆን እንዲከራዩ ያደረገ ሲሆን ከካሳ ክፍያዎች ጋር ተያይዞ ከየክፍላተ ከተማ ጋር በመናባብ እየሠራ መሆኑንም ገልጿል።

በተያያዘ ዜና ያልተመለሱ ይዞታዎችን ለማስመለስ ያላሰለሰ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ፣ ለሥራ ኀላፊዎች ቤት የሚያገኙበትን ስርዓት ከመንግሥት የመኖሪያ ቤት አስጣጥን ተመኮሮ በመውሰድ ጥናት ለማቅረብ ጥረት እየተደረገ መሆኑን፣ ሕንፃዎቹ የሚገኙበትን አካባቢ የሚመጥን የቤት ኪራይ ማሻሻያና የቤት ኪራይ ውል አሰጣጥ ማሻሻያ ጥናቶችን አጠናቆ በቅርቡ ለጽሕፈት ቤቱ እንደሚያቀርብና ለቤተክርስቲያን ገቢ የሚያስገኙ ሥራዎችን ለመስራት እቅድ መያዙ ተገልጿል።

በመጨረሻም ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ምክትል ሥራ አስኪያጆች የቀረበውን ሪፖርት በአድናቆት በመቀበል ለቤተክርስቲያን በመቆርቆር በባለቤትነት ስሜት ለማገዝ ከሚመጣው ይልቅ የራሱን ጥቅም ዓላማው ትችን ስንቁ ያደረገ ሠራተኛ በበዛበት ዘመን በነፍሳችሁ ተወራርዳች ለቤተክርስቲያን ለመስራት ቁርጠኛ ሰለሆናችሁ ከታሪክ ወቀሳ ድናችኋል ብለዋል። የቀረበው ሪፖርት ፈር ቀዳጅና በአጭር ጊዜ ውስጥ ትልቅ አፈፃፀም የታየበት መሆኑን አጽንዖት በመስጠት በዚህ ሥራ ላይ መሪ ተዋናይ የሆኑትን ሁሉ በማመስገን በቀጣይ ጠንክረው እንዲሠሩ አባታዊ መመሪያ ሰጥተዋል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳምን የሕንጻ ቤተክርስቲያን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸም ሂደትን ተዘዋውረው ተመለከቱ።
  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያንን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸምን ለመጎብኘት ወደ ድሬዳዋ ተጓዙ።
  • ለብፁዕ አቡነ ኤፍሬም በደምቢ ዶሎ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት የገንዘብ አስተዳደሩን ለማዘመን የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝ ወጋገን ባንክ አማራጭ መንገድ አቀረበ። Link to: የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት የገንዘብ አስተዳደሩን ለማዘመን የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝ ወጋገን ባንክ አማራጭ መንገድ አቀረበ። የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት ... Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ትምህርት ቤት ለተማሪዎች አገልግሎት የሚውል ልዩ ልዩ ንብረቶችን ድጋፍ አደረገ። Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ትምህርት ቤት ለተማሪዎች አገልግሎት የሚውል ልዩ ልዩ ንብረቶችን ድጋፍ አደረገ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top