የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ለዘመናት የቤተክርስቲያንን ተልእኮ በማሳለጥ የሚታወቀው የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ በበጀት ዓመቱ ለሦስተኛ ጊዜ ዐቢይ ጉባኤ አካሄደ

April 27, 2026

ሚያዚያ ፲፱ ቀን ፳፻፲ወ፰ዓ.ም.
ኢኦተቤክ ሕዝብግንኙነት
አዲስአበባ ኢትዮጵያ
👉 እስከ ምድር ዳርቻ ምስክሮች ሊሆኑ ለተጠሩት ለቅዱሳን ሐዋርያት በመጀመሪያ የታወጀው አዋጅ የማይሻር፣ ለዘለዓለም ጸንቶ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ ያለና ሲተላለፍ የሚኖር ሕያው ቃል በመሆኑ ብርሃናተ ዓለም ሐዋርያት፣ ሰባ ሁለቱ አርድዕት የስብከታቸውን ማዕከል ክርስቶስንና የአዳኝነቱን ሥራ በማድረግ አስዋከ ረሲዓንን እየነቀሉ፣ የወንጌልን ምርጥ ዘር በምዕመናን የልቡና ማሳ ላይ እየዘሩ በጋራም በተናጠልም ከፍተኛ ሐዋርያዊ ተጋድሎ የፈጸሙ ሲሆን ዘሩም በቅሎ አፍርቶ ፍሬው ከሐዋርያት ለሐዋርያነ አበው፣ ከሐዋርያነ አበው ለሊቃውንት ከሊቃውንት ወደ እኛ ዘመን መተላለፉ የሚታወቅ ነው፡፡
👉 የክርስቲያኖች ቁጥር እየጨመረ ሲመጣ በጥንድ እና በግል ሲመራ የነበረው የአመራር ስርዓት በመዋቅር የመምራት ስሌት ከመጣ በኋላም ብዙ አባቶቻችን ስለ ቤተክርስቲያን አያሌ ተግባራትን ማከናወናቸው ሌላኛው የስብከተ ወንጌል ፍሬ መሆኑም ይገለጻል።
👉 ለዘመናት በብዙ ፈተና ያለፈችው ቅድስት ቤተክርስታያናችን በ1950ዓ.ም ከግብፅ የአመራር
ስርዓት ወጥታ የራሷን ፓትርያርክ ከሾመች በኋላ በ1952ዓ.ም የመጀመሪያ ሥራዋን ያደረገችው የሀገሪቱን ንጉሥና ቅዱስ ፓትርያርኩ የበላይ ጠባቂነት የሚመራ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ያሳተፈ የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ምክር ቤት ማቋቋም ሲሆን ምክር ቤቱ ከንጉሡ እና ከፓትርያርክ ጀምሮ ሁሉም ተስፋ የሚጥሉበት ስለነበረ ለአፈጻጸም የማይቸገር መሆኑን
ሊቃውንት ይገልጻሉ።
👉 የንጉሡ ዘመን ካለፈ በኋላም ሶሻሊዝምን አራማጁ የደርግ መንግሥት ለስብከተ ወንጌል ፈተና ቢሆንበትም ቅሉ ባለ ራዕዩ እና ልባሙ ቅዱስ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ አማካኝነት ሰበካ ጉባኤንና
ሰንበት ትምህርት ቤት ወልዶ ራሱን በመዋቅር በ1972ዓ.ም አዲስና ለእንቅስቃሴው በር ከፋች ስርዓት በመፍጠር ሲሰራ እንደነበረ የዓይን እማኞች ይናገራሉ።
👉 ከለውጡ ማግሥት በ1984 እና በ1988 ዓ.ም. ደግሞ በሌላኛው ፓትርያርክ ልዩ መተዳደሪያ ደንብ ተሠርቶለት ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋቱ ረገድ አንቱ የተባለ ሥራ የተሠራ ሲሆን በ1992 ዓ.ም. ደግሞ ዓለም ዓቀፋዊ በሆኑት ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅደስ አቡነ ጳውሎስ መመሪያ ሰጭነት በብፁዕ አቡነ ቄርሎስ የወቅቱ ሥራ አስኪያጅ አስፈፃሚነት የተቋቋመው የ120 ቤተሰብ የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ኮሚቴ ደግሞ ሌላኛው የስብከተ ወንጌል ገፅታ ነው።
👉 በዚህ ልክ ራሱን እያሳደገ የመጣው የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ዛሬም የምዕመናን ደጀንነቱንና የቤተክርስቲያን ብቸኛ ተስፋ መሆኑን በሚገልጽ መልኩ በየጊዜው ስልጠናዎችንና ውይይቶችን እየደረገ ነው።
👉 በዛሬው እለትም ይህንኑ ስልጠናና ውይይት በወንጌል ሕይወታች ሆነልን በሚል ርዕስ ያካሄደ ሲሆን በስልጠናው ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብጰት ሊቀ ጳጳስ፤
ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ ፣ የሐድያና ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣
ክቡር ንቡረዕድ ኤልያስ አብርሃ የጠቅላይ ቤተክህነት የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ፤
ክቡር ረዳት ፕሮፌሰር ግርማ ባቱ የጠቅላይ ቤተክህነት ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ፤
ክቡር ሊቀ ኅሩያን ይልማ ጌታሁን የኢትዮጵያ የመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ጠቅላይ ጸሐፊ
ክቡራን የጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎችና የየድርጅቶች ሥራ አስኪያጆች፤
ክቡራን የአህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጆችና የስብከተ ወንጌል ክፍል ኀላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
👉 መርሐግብሩ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሸገር ከተማና የደቡብ ምዕራብ ሸዋ አህጉረ ስብከት ሲሆንሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኀኔዓለም ገዳም የበላይ ኀላፊ መሪነት የመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ካልናት ጸሎተ ወንጌል አድራሽነት ተጀምሮ የስብከተ ወንጌል ተግዳሮቶችና መፍትሔዎቻቸው በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቦ በርሱም ላይ ወይይት ተደርጎ ከምሳ ሰዓት በፊት ያለው መርሐግብር ተጠናቋል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/0010.jpg 427 640 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-04-27 08:45:322026-05-05 08:50:55ለዘመናት የቤተክርስቲያንን ተልእኮ በማሳለጥ የሚታወቀው የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ በበጀት ዓመቱ ለሦስተኛ ጊዜ ዐቢይ ጉባኤ አካሄደ
Search Search

Recent Posts

  • የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ትርጓሜ ምስክር ት/ቤት በባሕር ዳር ከተማ ለሚያስገነባው “የሕክምና መንደር” የመሠረት ድንጋይ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተቀመጠ።
  • የላሊበላ ቅርሶችን ለመጠበቅ የሚያስችል ውይይት ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ።
  • በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) እና የዲጂታል ሽግግር አማካሪ ኮሚቴ ለአስተዳደር ጉባኤው በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየሠራ ያለውን የተለያዩ የጥናት ሰነዶች አቀረበ፡፡
  • የቤቶችና ሕንጻዎች ልማት ድርጅት ሠራተኞቹን አመሰገነ።
  • “ተመራቂዎች በየተሰማሩበት የስምሪት መስክ ሁሉ እንደ መብራት ሊያበሩ ይገባል” ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: በበርካቶች ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ድረ-ገጽ አገልግሎት ጀመረ Link to: በበርካቶች ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ድረ-ገጽ አገልግሎት ጀመረ በበርካቶች ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የቤቶችና... Link to: EOTC TV | የቤቶችና ሕንጻዎች ድርጅት የልማት ግሥጋሤ Link to: EOTC TV | የቤቶችና ሕንጻዎች ድርጅት የልማት ግሥጋሤ EOTC TV | የቤቶችና ሕንጻዎች ድርጅት የልማት ግሥ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top