የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በቃሊቲ አካባቢ ለበጎ አድራጎት ሥራ ከ23 ዓመት በፊት ያስገነቡትን Gተ1 የመኖሪያ ሕንጻ ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማኅበር በስጦታ አበረከቱ

May 10, 2026

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የዋሽንግተን እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሰጡት የስጦታ መርሐ ግብር ላይ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተገኝተዋል።
ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ለበጎ አድራጎተት እንዲውል የሕንጻ ቁጥሩ 982 የሆነውንና በግል ገንዘባቸው በ544 ካሬ ሜትር ቦታ ያረፈ ሕንጻ በመገንባት ለዚሁ ዓላማ እንዲውል አድርገዋል።
ሕንጻው ያረፈበት ቦታ 240 ካሬ ሜትር ሲሆን በግንባታ ወቅት የወጣበት ወጪ ከ3ሚሊዮን በላይ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ባለው የገበያ ዋጋ ከ120 ሚሊዮን በላይ ይገመታል።ሕንጻው ከተገነባ 23 ዓመታትን ማስቆጠሩ ተገልጿል።
በመርሐ ግብሩ አቶ አምሓ ይልማ ባቀረቡት መልእክት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ሕንጻውን በገነቡበት ወቅት ያስተላለፉትን በሕግ ፊት የሚጸና ተብሎ የተመዘገበውን የኑዛዜ ሰነድ በጽሑፍ አቅርበውታል።
ቤቱን ለመቄዶንያ አረጋውያንና አእምሮ መርጃ ማዕከል ለማስተላለፍ ከቤተ ሰብ ጭምር ኮሚቴ (ቦርድ) ተቋቁሟል ተብሏል።
በመቀጠልም በስጦታ አድራጊ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤልና በስጦታ ተቀባይ መቄዶንያ የውል ስምምነት ሰነድ እና ካርታ ርክክብ ተፈጽሟል።
ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በስጦታ መርሐ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልእክት እግዚአብሔር የሰጠኝን ቤት ለእግዚአብሔር አስረክቤያለሁ ብለዋል። ብፁዕነታቸው ጨምረው እንደገለጹት 19 ዓመት የቤቱ ኪራይ ለበጎ አገልግሎት ውሏል ብለዋል።
መስጠት የማይፈልጉ ኃይሎች የእኔን ስጦታ ሲተቹ ሰምቻለሁ።
ይህ ግን አግባብነት የለውም ብለዋል። ብፁዕነታቸው እኔ የሚቆጠር ንብረት የለኝም ያሉ ሲሆን በመጨረሻም ካርታውንና የቤቱን ቁልፍ የመቄዶንያ መሥራች ብኒያም በለጠ ተረክበው የምስጋና መልእክት አስተላልፈዋል።
ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል 18 ዓመታቸው ስለመነኮሱ እግዚአብሔር የመቄዶንያ መሥራች ብንያም በለጠ የጠራቸው አባት መሆናቸውን እናምናለን። ስጦታቸውን የሚያጣጥሉ ኃይሎች መፈጠራቸው አሳዝኖናል ብለዋል።
ቀድሞም የቤት ኪራዩን ሜቄዶንያ ሲጠቀምበት የቆየ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ቤቱ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል 58ኛ መቄዶንያ ቅርንጫፍ እንዲባል ጠይቀዋል።
በመቄዶንያ ታሪክ ትልቁ ስጦታ ይህ ነው በማለት የመቄዶንያ መሥራቹ ብኒያም በለጠ ተናግረዋል።
በመቀጠልም የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች ስለስጦታው አርአያነት ያለው ነው በማለት አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
የመቄዶንያ አረጋውያንና አእምሮ ሕሙማን ማዕከል ተረጅዎችም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ አባታዊ ትምህርት የሰጡ ሲሆን ብፁዕነታቸው በሰጡት ትምህርት የትንሣኤው በኩር የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ከእኔ ተማሩ በማለት ያስተማረውን ትምህርት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በተግባር አውለውታል ብለዋል።
ብፁዕነታቸው ራሳቸውን በመስጠት ትልቁን መሰናከል አልፈዋል ብለዋል። ዛሬ ያጣነው የሚሠራ እንጂ የሚያወራ አይደለም ሲሉ መልዕታቸውን አጠቃለዋል።
በመጨረሻም በብፁዕ አቡነ ኤልያስ የኖርዲክ ሀገራት እና የግሪክ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ የመጨረሻ ትምህርትና ጸሎት መርሐ ግብሩ ተጠናቋል።©Eotc tv.

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/00022.jpg 448 330 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-05-10 16:38:522026-05-10 16:38:52ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በቃሊቲ አካባቢ ለበጎ አድራጎት ሥራ ከ23 ዓመት በፊት ያስገነቡትን Gተ1 የመኖሪያ ሕንጻ ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማኅበር በስጦታ አበረከቱ
Search Search

Recent Posts

  • የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ትርጓሜ ምስክር ት/ቤት በባሕር ዳር ከተማ ለሚያስገነባው “የሕክምና መንደር” የመሠረት ድንጋይ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተቀመጠ።
  • የላሊበላ ቅርሶችን ለመጠበቅ የሚያስችል ውይይት ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ።
  • በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) እና የዲጂታል ሽግግር አማካሪ ኮሚቴ ለአስተዳደር ጉባኤው በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየሠራ ያለውን የተለያዩ የጥናት ሰነዶች አቀረበ፡፡
  • የቤቶችና ሕንጻዎች ልማት ድርጅት ሠራተኞቹን አመሰገነ።
  • “ተመራቂዎች በየተሰማሩበት የስምሪት መስክ ሁሉ እንደ መብራት ሊያበሩ ይገባል” ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ Link to: መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ Link to: የአዳማ ሰቀቀሎ ደብረ ገነት ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤቱ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከበረ Link to: የአዳማ ሰቀቀሎ ደብረ ገነት ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤቱ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከበረ የአዳማ ሰቀቀሎ ደብረ ገነት ቅዱስ በዓለ ወልድ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top