የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የአዳማ ሰቀቀሎ ደብረ ገነት ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤቱ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከበረ

May 10, 2026

ግንቦት ፪ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም አዳማ — በአዳማ ከተማ በውብ የኪነ-ሕንጻ ጥበብ የታነጸው የአዳማ ሰቀቀሎ ደብረ ገነት ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ ቤተ መቅደስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የሀገረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎችና በሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናን በተገኙበት በዛሬው ዕለት ቅዳሴ ቤቱ በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት ተከብሯል።
ትላንት ግንቦት ፩ ቀን በብፁዕ አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ (የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ቋሚ አባልና የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ተቋማት የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሰብሳቢ) እንዲሁም በብፁዕ አቡነ ጢሞቲዎስ (የዳውሮ፣ ኮንታ እና የከንባታ ሀላባ ጠንባሮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ ቋሚ አባል) ቡራኬ ተባርኮ የተመረቀው ይህ ቤተ መቅደስ በዛሬው ዕለት ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል።
በክብረ በዓሉ ላይ በመገኘት ቡራኬና ትምህርት የሰጡት ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ፣ ምእመናን የእግዚአብሔርን ቤት በመሥራታቸው ያለቸውን ደስታ ገልጸው የሚከተለውን መልእክት አስተላልፈዋል፦
“ዛሬ አሳንጻችሁ የወልደ እግዚአብሔርን ሥጋውን የምንበላበት፣ ደሙን የምንጠጣበት የእግዚአብሔርን ቤት ሠርታችኋል። በዚህ ቤተ መቅደስ እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያም ፣ ቅዱሳን መላእክትን፣ ጻድቃንና ሰማዕታትን እናገኝባቸዋለን። ይህ ሥፍራ ያዘነ የሚጽናናበት፣ የደከመ የሚበረታበት፣ ያጣ የሚያገኝበትና የተቸገረ ከችግሩ የሚላቀቅበት ዘላለማዊ ቤት ነው” ብለዋል።
ብፁዕነታቸው አክለውም፣ እግዚአብሔር ከምእመናን የሚፈልገው በዋናነት ራሳቸውን እንደሆነ ገልጸው፤ ምእመናን በንስሓ ሕይወት በመመላለስ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን መቀበል እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ በበኩላቸው፣ በሀገረ ስብከታቸው እየተከናወኑ ያሉ የቤተ ክርስቲያን የልማት ሥራዎችን በማድነቅ ጥልቅ የሆነ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክትና ቃለ ምዕዳን አስተላልፈዋል።
“ለሁሉም ነገር መሠረቱ ሕዝብ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝበ ክርስቲያን በሰላም፣ በአንድነትና በመቻቻል ተሳስሮ የኖረ ድንቅ ሕዝብ ነው። ይህ ሕዝብ ቤተ ክርስቲያኑን ሠርቶ በማስፈጸም ረገድ ያለውን ጥንካሬ የምናደንቀው ቢሆንም፤ ከምንም በላይ ግን ይህንን ለዘመናት የቆየ ሰላሙን፣ አንድነቱንና መቻቻሉን ጠብቆ ማስቀጠል አለበት” ብለዋል።
አክለውም አዳማ ከተማ የፍቅርና የአንድነት ከተማ መሆኗን ጠቅሰው፣ ከልጅ እስከ አዋቂ በገንዘባቸውና በጉልበታቸው ለደከሙ ሁሉ “እንኳን ደስ አላችሁ” በማለት በአባታዊ ቡራኬና ቃለ ምዕዳን ሰጥተዋል።
በዕለቱ የሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል ኃላፊ መጋቤ ሐዲስ ቆሞስ አባ ኃይለ ገብርኤል ተስፋ፣ በብፁዕነታቸው መልካም ፈቃድ “የማትፈርስ መቅደስ” በሚል ርዕስ ጥልቅ የሆነ የወንጌል ትምህርት አስተምረዋል። መርሐ ግብሩን ደግሞ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሣሕል ቀሲስ ነጋሽ ሀብተ ወልድ በብቃት መርተውታል።
በመጨረሻም ሕንጻ ቤተ መቅደሱ ከጅምሩ እስከ ፍጻሜው እንዲደርስ በእውቀታቸው፣ በጉልበታቸውና በገንዘባቸው ከፍተኛ ድጋፍ ላደረጉ ምእመናንና ባለሙያዎች ዕውቅናና ምስጋና ተሰጥቷል።
የሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ ማጠቃለያ ዕይታ ፤ ይህ ውብ ሕንጻ ቤተ መቅደስ ከ108 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበት ለፍጻሜ መብቃቱ፣ ከመንፈሳዊ ጥንካሬ ባለፈ የታላቅ አመራርና የተናበበ ሥራ ውጤት መሆኑን ነው።
​በተለይም የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ገነት ቀሲስ ታፈሰ ተስፋዬ፣ ግንባታው ከመሠረት ድንጋይ ጀምሮ እዚህ ደረጃ ላይ እስኪደርስ ድረስ የነበራቸው ሚና የሚደነቅ ነው። አስተዳዳሪው ከዲቁና የክህነት ማዕረግ ጀምሮ በዚህ ደብር ውስጥ በማገልገልና አሁን ላይም በኃላፊነት በመምራት፣ የአዳማ ከተማን ምእመናን በአንድነት በማስተባበር ያሳዩት ቁርጠኝነት ለቤተ መቅደሱ ግንባታ መሳካት ዋነኛ ምሰሶ ሆኖ ተገኝቷል።
​ይህ ክስተት የሚያሳየው፣ አንጋፋ አባቶች ከሕዝበ ክርስቲያኑ ጋር በፍቅርና በትሕትና ሲሰለፉ፣ እንደዚህ ያሉ ታላላቅ የልማት ሥራዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ማከናወን እንደሚቻል ነው። ሚዲያችን እንደተመለከተው፤ የአስተዳዳሪው የረጅም ዘመን አገልግሎትና ከምእመናን ጋር የገነቡት ጥንካሬ፣ ዛሬ ለታየው ታላቅ መንፈሳዊ ድልና ለቤተ ክርስቲያኒቱ ክብር መጎናጸፊያ ሆኗል። ይህም ለሌሎች አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎችም ትልቅ ትምህርትና አርአያ የሚሆን ተግባር መሆኑን ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ ባደረገው ዳሰሳ አረጋግጧል።©ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/00021.jpg 427 640 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-05-10 16:40:242026-05-10 16:41:26የአዳማ ሰቀቀሎ ደብረ ገነት ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤቱ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከበረ
Search Search

Recent Posts

  • የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ትርጓሜ ምስክር ት/ቤት በባሕር ዳር ከተማ ለሚያስገነባው “የሕክምና መንደር” የመሠረት ድንጋይ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተቀመጠ።
  • የላሊበላ ቅርሶችን ለመጠበቅ የሚያስችል ውይይት ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ።
  • በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) እና የዲጂታል ሽግግር አማካሪ ኮሚቴ ለአስተዳደር ጉባኤው በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየሠራ ያለውን የተለያዩ የጥናት ሰነዶች አቀረበ፡፡
  • የቤቶችና ሕንጻዎች ልማት ድርጅት ሠራተኞቹን አመሰገነ።
  • “ተመራቂዎች በየተሰማሩበት የስምሪት መስክ ሁሉ እንደ መብራት ሊያበሩ ይገባል” ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በቃሊቲ አካባቢ ለበጎ አድራጎት ሥራ ከ23 ዓመት በፊት ያስገነቡትን Gተ1 የመኖሪያ ሕንጻ ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማኅበር በስጦታ አበረከቱ Link to: ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በቃሊቲ አካባቢ ለበጎ አድራጎት ሥራ ከ23 ዓመት በፊት ያስገነቡትን Gተ1 የመኖሪያ ሕንጻ ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማኅበር በስጦታ አበረከቱ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በቃሊቲ አካባቢ ለበጎ አድራጎት... Link to: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሳዑዲ ዓረቢያ የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው በአስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን በማስመልከት ለኢትዮጵያና ለሳዑዲ መንግሥታት፣ ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አባታዊ መልእክት አስተላለፉ። Link to: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሳዑዲ ዓረቢያ የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው በአስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን በማስመልከት ለኢትዮጵያና ለሳዑዲ መንግሥታት፣ ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አባታዊ መልእክት አስተላለፉ። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top