የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ቅዱስ ሲኖዶስ በልማትና ዘመናዊ አሠራር ላይ ያተኮሩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ለ6 ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን የ2018 ዓ.ም የርክበ ካህናት ጉባኤውን አጠናቀቀ

May 13, 2026

ግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ለስድስት ተከታታይ ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን መደበኛ የምልኣተ ጉባኤ ስብሰባውን በ22 አጀንዳዎች ላይ በመወያየትና ለቤተክርስቲያናችን ቀጣይ ጉዞ ወሳኝ የሆኑ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ማጠናቀቁን የቅዱስ ሲኖዶስ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ፣ ረዳት ፕሮፌሰር ቀሲስ ዳንኤል ሰይፈ-ሚካኤል ለEOTCTV በሰጡት ዕለታዊ መግለጫ አስታውዋል።
ኃላፊው በሰጡት ማብራርያ፣ ጉባኤው በተለይም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት እየተከናወኑ ያሉትን የልማት፣ የዘመናዊ አሠራር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ሥራዎች በዝርዝር ከገመገመ በኋላ ከፍተኛ አድናቆቱን መግለጹን ተናግረዋል።
በጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሆኑት በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ አመራር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት በምስል እና ድምፅ የተደገፈ ሰፊ ሪፖርት ለምልአተ ጉባኤው መቅረቡን የጠቀሱት ረዳት ፕሮፌሰር ቀሲስ ዳንኤል፣ ሪፖርቱ “ቤተክርስቲያናችን ለዘመናት ያላትን ታሪካዊ አስተዋጽኦ እያስጠበቀች፣ ከዘመኑ ጋር የሚራመድ አሠራርን ለመገንባት እየተደረገ ያለውን ርብርብ በጉልህ አሳይቷል” ሲሉ ገልጸዋል።
በሪፖርቱ ከቀረቡት ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል በመንበረ ፓትርያርክ ግቢ እና “በኮሪደር ልማት” በተገኙ መሬቶች ላይ የተጀመሩ የግንባታ ፕሮጀክቶች እንዲሁም ግቢውን የማስዋብና ምቹ የማድረግ ሥራዎች እንደሚገኙበት የገለጹ ሲሆን ረዳት ፕሮፌሰር ቀሲስ ዳንኤል እንዳብራሩት፣ “ምልአተ ጉባኤው በአጭር ጊዜ ውስጥ የተገኙትን እነዚህን ተጨባጭ ውጤቶች በማየት ሥራዎቹን በከፍተኛ አድናቆት ምልዓተ ጉባኤው ተቀብሏቸዋል።” ብለዋል።
ከዚህም በተጨማሪ፣ ለዘመናት ተቀምጠው የነበሩ ታሪካዊ የሰነድ መዛግብትን በዲጂታል ቴክኖሎጂ የማስቀመጥ ሥራ መጀመሩና
አስተዳደራዊ መዋቅሩን በማዘመን የአገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑ ተብራርቷል።
ለረጅም ጊዜ በመጋዘን የቆዩ ቅዱሳት መጻሕፍትን በማሳተም ለምዕመናን ተደራሽ የማድረግ ሥራም በስፋት መከናወኑን ኃላፊው አክለው ገልጸዋል።
ብፁዓን አባቶች በቀረበው ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ፣ “የተጀመሩት ስራዎች የቤተክርስቲያኒቱን ክብርና ልዕልና
የሚያስጠብቁ፣ ተቋማዊ ህልውናዋን የሚያጠናክሩና ለምዕመናን የሚሰጠውን አገልግሎት የሚያዘምኑ ናቸው” በማለት ሙሉ ድጋፋቸውን መግለጻቸውን ረዳት ፕሮፌሰር ቀሲስ ዳንኤል አስረድተዋል።
በዚህም መሠረት ምልኣተ ጉባኤው የተጀመሩት የልማትና የማዘመን ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ከመወሰኑም በላይ፣ ሌሎች አባቶችም በየአህጉረ ስብከታቸው ተመሳሳይ ማሻሻያዎችን እንዲተገብሩ ጥሪ ማቅረቡን ገልጸዋል።
ጉባኤው ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጀመሩትን ሥራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ሙሉ ድጋፍ እንደሚሰጥም አረጋግጧል ተብለዋል ።
ጉባኤው በሌሎች አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ ከመከረ በኋላም፣ በቀጣዮቹ ስድስት ወራት በቋሚ ሲኖዶስ ውስጥ የሚያገለግሉ ብፁዓን አባቶችን ምርጫ ማካሄዱን የኮሙኒኬሽን ኃላፊው ተናግረዋል።
በመጨረሻም፣ “ለቀናት በተለያዩ አገራዊና ሃይማኖታዊ አጀንዳዎች ላይ ሲመክር የቆየው የቅዱስ ሲኖዶሱ ምልኣተ ጉባኤ፣ በነገው
ዕለት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሚሰጡት ቃለ ምዕዳንና አባታዊ ቡራኬ በይፋ ይጠናቀቃል” ሲሉ ረዳት ፕሮፌሰር ቀሲስ ዳንኤል ሰይፈ-ሚካኤል ማብራርያቸውን አጠቃለዋል።©EOTc tv

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/00025.jpg 252 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-05-13 18:46:462026-05-13 19:07:00ቅዱስ ሲኖዶስ በልማትና ዘመናዊ አሠራር ላይ ያተኮሩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ለ6 ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን የ2018 ዓ.ም የርክበ ካህናት ጉባኤውን አጠናቀቀ
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅጣጫ ሰጪነት እየታደሰ የሚገኘውን ዕድሜ ጠገቡን የወንጪ ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም ጎበኙ
  • ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ እየተገነባ ያለውን ዓለም አቀፍ የሥብሰባ አዳራሽ ጎበኙ
  • በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ተጀምሮ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ትጋት ለፍጻሜ የበቃው ባለ 480 ካሬ ሜትር ሁለገብ ሕንጻ ተመረቀ
  • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
  • ቅዱስ ሲኖዶስ በልማትና ዘመናዊ አሠራር ላይ ያተኮሩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ለ6 ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን የ2018 ዓ.ም የርክበ ካህናት ጉባኤውን አጠናቀቀ

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና የኢትዮጵያ ፈደራል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ “ጠንካራ ትብብር ለሀገር ሰላም! ሰላም የወል ሀብታችን ነው!” በሚል መሪቃል ስለሰላም በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የጋራ ስምምነት ተፈራረመ Link to: የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና የኢትዮጵያ ፈደራል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ “ጠንካራ ትብብር ለሀገር ሰላም! ሰላም የወል ሀብታችን ነው!” በሚል መሪቃል ስለሰላም በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የጋራ ስምምነት ተፈራረመ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና የኢትዮጵያ... Link to: ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ Link to: ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top