የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

May 26, 2026

ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም
የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምሥራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከዚህ በፊት በቅዱስ ሲኖዶስ በተወሰነው መሠረት ሀገረ ስብከቱን እንዲመሩ መድቧቸዋል።
በዚሁም መሠረት ብፁዕነታቸው በም0ሥራቅ አርሲ አሰላ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።
በአቀባበሉ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ፣ የደቡብ ምስራቅ ትግራይና ራያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ እና የድርጅት ኃላፊዎች ፣ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ፣የሀገረ ስብከቱ የልዩ ልዩ የክፍል ኃላፊዎች ፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን አባ ገዳዎችና በጣም በርካታ ምዕመናን ተገኝተዋል።
ብፁዕነታቸውና ብፁዓን አበው ሊቀነ ጳጳሳት በቤተ ክርስቲያኑ ሲደርሱም ጸሎተ ወንጌልና ኪዳን ከተደረሰ በኋላ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት ለብፁዕነታቸው የተዘጋጀ ደብዳቤ በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦምና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ከተነበበ በኋላ ሕዝበ ክርስቲያኑ በእልልታና በደስታ ብፁዕነታቸውን ተቀብሏል።
የደብሩ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንም የቅዱስ ያሬድ ዜማ ያቀረቡ ሲሆን በመቀጠልም ቅኔያት በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ቀርበዋል፡፡
የመታሰቢያ ስጦታዎችም ለብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ ለብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ፣ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም ለብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ተሰጥተዋል።
በመቀጠልም ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦምና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅድስት ሥላሴ ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት የዕለቱን ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል።
በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ፣ የደቡብ ምሥራቅ የራያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አባታዊ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ሥራንና ሠራተኛን ማገናኘት የሚችሉና ጠንካራ አባት በመሆናቸው ቅዱስ ሲኖዶስ በሀገረ ስብከቱ የነበረውን ችግር በማየት ሀገረ ስብከቱን እንዲያሳድጉ መመደባቸውን ገልጸዋል።
ብፁዕነታቸው አክለውም በእምነታችን ከጸናን ሁሉም ስለሚያልፍ መጸለይ አለብን ፣ ቤተ ክርስቲያናችንን መጠበቅ አለበን በማለት አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል።
በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቃለ ምዕዳንና አባታዊ ቡራኬ የሰጡ ሲሆን ሀገረ ስብከቱ እንደ ቀደምትነቱ ብዙ ያልተሠራበት በመሆኑ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ እንደሚሰሩ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።
ሕዝቡ በቋንቋው መማር እንዳለበትና ሀገሩ እንዲለማ አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ብፁዕነታቸው አክለውም ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ከታች ጀምሮ የተሰጣቸውን ሥራ ሁሉ በመሥራት የሚታወቁ በመሆናቸው አብሮ መሥራት ያሰጥተዋል።
በብፁዕነታቸው አባታዊ ቡራኬና ጸሎት መርሐ ግብሩ የተጠናቀቀ ሲሆን ለመንበረ ጵጵስናው ለሚሠራ ሕንጻ ፣ በጥምቀተ ባህር ግቢ ውስጥ G+6 ሁለ ገብ የሕንጻ የገበያ ማዕከል እንዲሁም ለተለያዩ የልማት ሥራዎች በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ መሠረተ ድንጋይ ተቀምጠዋል ።
በተጨማሪም የምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት የአገልግሎት ጥራትን ለማሳደግና የፋይናንስ አቅም ለማጠናከር ታስቦ የተገነባ ሁለገብ ሕንጻ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳተ ቡራኬ ተመርቋል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr00001.jpg 299 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-05-26 10:30:002026-05-26 10:30:00ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ከግንቦት እስከ ግንቦት ክፍል ሦስት Link to: ከግንቦት እስከ ግንቦት ክፍል ሦስት ከግንቦት እስከ ግንቦት ክፍል ሦስት Link to: በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ። Link to: በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ። በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top