የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡

May 30, 2026

ግንቦት ፳፪ ቀን ፳፻፲ወ፰ ዓም
የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቡራኬ ተመረቀ፡፡ ቤተክርስቲያኑን ለማጠናቀቅ ዐሥራ ሁለት ዓመት የፈጀ ሲሆን፤ በወቅቱ የመሠረት ድጋዩ የተጣለው በ፳፻፮ ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ሲሆን፤ ለምርቃት የበቃውም በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ዕለት በዕለት ክትትልና አመራር ሰጪነት መሆኑን የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ምሕረት ቀሲስ ያሬድ ሺፈራው ያስረዳሉ፡፡ የደብሩ አስተዳዳሪ አያይዘውም አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ተመርቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ እንዳስደሰታቸው ጠቁመው፤ በቤተክርስቲያን ሕሙማንን የሚፈውስ ታሪካዊ፣ በርካታ ገቢረ ተአምራት የሚፈጸምበት ጠበል የሚገኝ በመሆኑ ምእመናን ወደ ሥፍራው መጥተው እንዲጠመቁ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ እንደተናገሩት “ ግሩም የሆነ፣ በጣም ያማረ ሕንጻ ቤተክርስቱያን አንጻችኋል፡፡ በድካማችኁ፣ በገንዘባችኁ ዘመን ተሸጋሪ፣ ለቀጣዩ ትውልድ የሚተላለፍ ታካዊ ቤተክርስቲያን እግዚአብሔር ፈቅዶላችሁ፣ እናንተ የምትገለገሉበት፣ እግዚአብሔር የሚመሰገንበት ሠርታችሁ በማጠናቀቃችሁ እንኳ ደስ አላችሁ” ብለዋል፡፡ ብፁዕነታቸው አያይዘውም ቤተክርስቲያኑን በፍቅር፣ በሰላም በአንድነት እንድታመሰገኑ ሲሉ አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የሕንጻ አሠሪ ኮሚቴ ጸሐፊ አቶ ዐቢይ አበበ እንደተናገሩት ይህን ቤተክርስቲያን ስንሠራ ብዙ ነገር አሳልፈናል፤ እግዚአብሔር ለዛሬዋ ለምርቃት ቀን ስላበቃን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን ብሏል፡፡
ሊቀ ብርሃናት መምህር ተክለ ብርሃን “እናንተ እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆናችሁ ቤተክርስቲያን ሠርታችኋል፤ በቅዱስ መጽሐፍ እንደተገለጸው ቤተመቅደስ ሥሩልኝ እኔም በውስጡ እድራለሁ ያለውን ቃል ተግባራዊ ያደረጋችሁ በመሆናችሁ፤ ዕድለኞች ናችሁ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም ለሕንጻ ቤተክርስቲያኑ ግንባታ በዕውቀታቸው፣ በጉልበታቸውና በገንዘባቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ምእመናን፣ በጎ አድራጊዎችና በሕንጻ አሠሪ ኮሚቴ ሲያገለግሉ የነበሩ ከብፁዕነታቸው እጅ ሽልማትና የምስጋና ምስክር ወረቀት ተቀብለዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ መልአከ ኃይል አባ አፈወርቅ ዮሐንስ የለገጣፎ ለገዳዲ እና ኩራ ጂዳ፣ የመልካ ኖኖ፣ የጉጂ ገፈርሳ ክፍላተ ከተማ እንዲሁም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ሊቀ ልሣናት በዳሳ ቶላ የኮዬ ፈጬና ገላን ክፍላተ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና በርካታ የአካባቢው ምእመናን ተገኝተዋል፡፡©EOTC_TV

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr00005.jpg 336 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-05-30 15:03:512026-05-30 15:03:51ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ። Link to: የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ። የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top