የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ለብፁዕ አቡነ ኤፍሬም በደምቢ ዶሎ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

June 16, 2026

ሰኔ 6/10/2018
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፣ የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኙት ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም፣በግንቦት 2018 ዓ በተካሔደው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የቄለም ወለጋን ሀገረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ መወሰኑ ይታወቃል።
በዚህም መሰረት ብፁዕነታቸው ይህንኑ ኃላፊነት ለመረከብ ሰኔ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ ደቢዶሎ ከተማ ሲያቀኑ፣በከተሣው ነዋሪዎች ምዕመናንና ምዕመናት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።
ብፁዕነታቸው ወደ ቄለም ወለጋ ሀገረ ስብከት በተጓዙበት ጊዜ
ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ (ዶ/ር)፦ የኢሉ አባቦርና የምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም የመቱ ፈለገ ሕይወት መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ፣ መላከ ምሕረት ቆሞስ አባ ገብረ እግዚአብሔር፦ የምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ።በኩረ ትጉህ ቀሲስ ምትኩ ከንቲባ፦ የጠቅላይ ቤተክህነት የቅርስ ጥበቃ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ ኃላፊ ሊቀ ልሳናት ቀሲስ በዳሳ ቶላ፦ የጠቅላይ ቤተክህነት የሊቃውንት ጉባኤና የኮዬ ፈጬ ክፍላተ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ላዕከ ወንጌል ኃይሉ አየለ፦ የጠቅላይ ቤተክህነት ሕዝብ ግንኙነት ምክትል መምሪያ ኃላፊ፣ መጋቤ ብሉይ ሣህለ ማርያም፦ የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ።
መላከ ሄዶም ቀሲስ ግርማ ኢማና፦ የደቢዶሎ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ተገኝተዋል ።
ብፁዕነታቸው ደቢዶሎ ደብረ ፀሐይ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን እንደደረሱ፤ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ የማህበራት ተወካዮች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት፣ የነገረ መለኮት ምሩቃን እና ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናት ደማቅ አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን በስነ-ስርዓቱ ላይም የደብረ ፀሐይ ደንቢዶሎ መድኃኔዓለም ሰንበት ተማሪዎችና የአዲስ አበባና የሸገር ሀገረ ስብከት ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ያሬዳዊ ዜማ አቅርበዋል።
በዚሁ መርሐ ግብር ላይ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ (ዶ/ር) ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት አንድነት ለቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ ልማት ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፤ በሁሉም ቋንቋ በቀረበው አገልግሎት መደሰታቸውንና ይህን የመሰለ ሁሉን አቀፍ አገልግሎት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልጸዋል።
በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ምስጋ አቅርበው ስለ ወለጋ ክልል ሰላም የሚነገረውና በተጨባጭ ያዩት እጅግ የተለየ መሆኑን በመጠቆም የሕዝቡ አንድነትና ፍቅር ልባቸውን እንደነካው ከገለጹ በኋላ ይህ መርሐ ግብር በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉት ሁሉ ምስጋናቸውን በማቅረብ ቃለ ምዕዳንና ቃለ በረከት አስተላልፈው የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል።
ዘጋቢ የላዕከ ወንጌል ኃይሉ አየለ ነው፤

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000014.jpg 299 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-06-16 15:34:202026-06-16 15:34:20ለብፁዕ አቡነ ኤፍሬም በደምቢ ዶሎ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳምን የሕንጻ ቤተክርስቲያን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸም ሂደትን ተዘዋውረው ተመለከቱ።
  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያንን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸምን ለመጎብኘት ወደ ድሬዳዋ ተጓዙ።
  • ለብፁዕ አቡነ ኤፍሬም በደምቢ ዶሎ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ። Link to: በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ። በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ... Link to: ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያንን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸምን ለመጎብኘት ወደ ድሬዳዋ ተጓዙ። Link to: ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያንን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸምን ለመጎብኘት ወደ ድሬዳዋ ተጓዙ። ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቁልቢ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top