የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የወልቂጤ ቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሁለተኛውን ዙር የነገረ መለኮት ደቀ መዛሙርት በታላቅ ድምቀት አስመረቀ።

June 27, 2026
ሰኔ ፳ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ሣልሳይ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የተመሠረተው የወልቂጤ ቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ፣ ለሦስት ተከታታይ ዓመታት በነገረ መለኮት ትምህርት ዘርፍ ሲያስተምራቸው የነበሩ የሁለተኛ ዙር ደቀ መዛሙርት በዛሬው ዕለት በታላቅ ድምቀት አስመርቋል።
የሀገርና የቅድስት ቤተክርስቲያን ተተኪ አገልጋዮችንና ምሁራንን በማፍራት ላይ የሚገኘው የዚህ ኮሌጅ ታሪካዊ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት በከፍተኛ መንፈሳዊ ድምቀትና ሥርዓት የተከናወነ ሲሆን፤ በበዓሉ ላይ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ሣልሳይ (የኮሌጁ መሥራችና የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ)፣ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ (የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የታቦር ፍኖተ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ) እና ብፁዕ አቡነ መቃሪዎስ (የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ) ተገኝተዋል። በተጨማሪም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ከፍተኛ ልዑካን እና የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አመራር አካላት፣ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግስት አካላት በክብር እንግድነት በመገኘት የሥነ-ሥርዓቱ ተካፋይ ሆነዋል።
በዛሬው የምረቃ መርሐ ግብር ላይ መደበኛ የነገረ መለኮት ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ 19 ደቀ መዛሙርት እንዲሁም ለአንድ ወር ተከታታይ የአጭር ጊዜ የአቅም ማጠናከሪያ ሥልጠና ሲከታተሉ የነበሩ 30 ካህናትና አገልጋዮች በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እጅ የዲፕሎማና የሰርተፍኬት የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል። ይህ የምረቃ በዓል ኮሌጁ በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ዘርፍ እያበረከተ ያለውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያሳይ ሲሆን፤ ተመራቂዎቹም ላለፉት ሦስት ዓመታት የቀሰሙትን ዕውቀት መሠረት በማድረግ ኦርቶዶክሳዊነትን ለማስፋፋትና ቅድስት ቤተክርስቲያንን በዕውቀት ለማገልገል የሚሰማሩበት ልዩ ምዕራፍ መሆኑ ተገልጿል።
ኮሌጁ በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ዘርፍ እያበረከተ ያለው ይህ ከፍተኛ አስተዋጽኦ፣ በሀገረ ስብከቱም ሆነ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የሚታየውን የአገልጋይ እጥረት ለመቅረፍ ትልቅ ተስፋ የሰነቀ መሆኑም በዕለቱ ተነግሯል።
በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ሰፋ ያለና ጥልቅ ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል።
ለአጠቃላዩ ተመራቂዎች መንፈሳዊ መመሪያና አባታዊ መልዕክት ያስተላለፉት ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ሣልሳይ፤ መነሻቸውን “ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ኑሩ” (ፊል 1፥27) በሚለው የቅዱስ መጽሐፍ ቃል ላይ በማድረግ ይህ ዕለት የትምህርታቸው ማብቂያ ሳይሆን የአገልግሎታቸው ጅማሬ መሆኑን ተመራቂዎቹ አውቀው ሊያስቡበት እንደሚገባ አሳስበዋል።
በጉባኤው ውስጥ የተማሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምዕመናንን የሚጠብቁበት ክንድ በመሆኑ፣ የተቀሰመው ዕውቀት ከአገልግሎት የተለየ እንዳይሆንና በትምህርት ደረጃ ብቻ ሳይቀረጽ በተግባር ላይ ሊውል እንደሚገባም መመሪያ ሰጥተዋል። ተመራቂዎቹ ለምዕመናን ምሳሌ በመሆን መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን በሓላፊነት ስሜትና በትጋት ሊወጡ እንደሚገባ የገለጹት ብፁዕነታቸው፣ የክህነት አገልግሎት ልዩ ክብር ያለው ቢሆንም ከሁሉ በላይ የመስዋዕትነትና የኃላፊነት ዋጋ መሆኑን፣ ያላችሁበት ዘመንም በብዙ ፈተናዎች የተከበበ መሆኑን በተለየ ሁኔታ መገንዘብና ማወቅ እንደሚገባ በጥብቅ አሳስበዋል። ታሪካዊው የምረቃ ሥነ-ሥርዓት በብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ቃለ ምዕዳንና አባታዊ ቡራኬ ተጠናቋል። © ሣሌም የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000019.jpeg 299 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-06-27 17:57:492026-06-27 17:57:49የወልቂጤ ቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሁለተኛውን ዙር የነገረ መለኮት ደቀ መዛሙርት በታላቅ ድምቀት አስመረቀ።
Search Search

Recent Posts

  • የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ትርጓሜ ምስክር ት/ቤት በባሕር ዳር ከተማ ለሚያስገነባው “የሕክምና መንደር” የመሠረት ድንጋይ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተቀመጠ።
  • የላሊበላ ቅርሶችን ለመጠበቅ የሚያስችል ውይይት ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ።
  • በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) እና የዲጂታል ሽግግር አማካሪ ኮሚቴ ለአስተዳደር ጉባኤው በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየሠራ ያለውን የተለያዩ የጥናት ሰነዶች አቀረበ፡፡
  • የቤቶችና ሕንጻዎች ልማት ድርጅት ሠራተኞቹን አመሰገነ።
  • “ተመራቂዎች በየተሰማሩበት የስምሪት መስክ ሁሉ እንደ መብራት ሊያበሩ ይገባል” ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት፤ የቤተ ክርስቲያኒቱን መንፈሳዊ ፍርድ ቤቶች እንደገና ለማቋቋም፣ ለማደራጀት እና ለማጠናከር ያዘጋጀውን አዲስ ረቂቅ አዋጅ ለውይይት አቀረበ። Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት፤ የቤተ ክርስቲያኒቱን መንፈሳዊ ፍርድ ቤቶች እንደገና ለማቋቋም፣ ለማደራጀት እና ለማጠናከር ያዘጋጀውን አዲስ ረቂቅ አዋጅ ለውይይት አቀረበ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን... Link to: “ተመራቂዎች በየተሰማሩበት የስምሪት መስክ ሁሉ እንደ መብራት ሊያበሩ ይገባል” ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ Link to: “ተመራቂዎች በየተሰማሩበት የስምሪት መስክ ሁሉ እንደ መብራት ሊያበሩ ይገባል” ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ “ተመራቂዎች በየተሰማሩበት የስምሪት መስክ ሁሉ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top