የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ (ዶ/ር) ፲፬ኛ ዓመት በዓለ ዕረፍት መታሰቢያ

August 15, 2026
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፭ኛ ፓትርያርክ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ (ዶ/ር) ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፲፬ኛ ዓመት በዓለ ዕረፍት መታሰቢያ በዓል እሑድ ነሐሴ ፲ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በጸሎት ታስቦ ይውላል።
​​ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዚዳንት እና የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዚዳንት ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት ነሐሴ ፲ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም ነበር። እነሆ ፲፬ ዓመታት ተቆጠሩ።
ቅዱስነታቸው በጥቂቱ ሲታወሱ፡-
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ (ዶ/ር) ወንጌልን በማስፋፋት የቤተክርስቲያንን አስተዳደር ለማጠናከርና የቤተክርስቲያኒቱን ዓለም አቀፍ ግንኙነት ለማስፋት ያላሰለሰ ጥረትን አድርገዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከውጭው ክፍለ ዓለም ጋር በመገናኘት ከኦርየንታልና ከምሥራቅ ኦርቶዶክስ ጋር ያላት ግንኙነት እንዲጠነክር አድርገዋል፡፡ በዚህም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ያላት ተሰሚነትና ተቀባይነት አንዲያድግ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በመላው ዓለም እንድትስፋፋ ያደረጉ ታላቅ ዓለም አቀፋዊ አባት ነበሩ፡፡
ቤተክርስቲያናችን በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ (ዶ/ር) ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘመነ ክህነት የሀገርና የዓለም አቀፍ ይዘቷን እያጠናከረችና እያሰፋች በመጣችበት ወቅት፤የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ፣ የሰዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኰሌጅ፣ የፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኰሌጅ እንዲከፈቱ አድርገዋል፤ በደርግ መንግሥት ተወርሰው የነበሩትን የቤተክርስቲያን ሕንፃዎችንና ንብረቶችን አስመልሰዋል፡፡በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር አዳዲስ አብያተ ክርስቲያናትን እንዲታነጽ አድርገዋል፡፡ ወደ የአህጉረ ስብከቱ ሐዋርያዊ ጉዞ በማድረግ በየገዳማቱና አድባራቱ እንዲሁም በገጠር በየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በመገኘት ከቤተ መቅደሱ ክህነታዊ አገልግሎት ጀምሮ በሚሰጡት ቀኖናዊ መመሪያ፤ አባታዊ ቡራኬ፣ ቃለ ምዕዳንና ትምህርተ ወንጌል፤ካህናት በቤተክርስቲያን አገልግሎታቸው፤ምእመናንም በእምነታቸውና በአንድነታቸው ጸንተው እንዲኖሩ አድርገዋል፡፡
ቅዱስነታቸው ሰብሳቢ ያጡ ዕጓለ ማውታ ሕፃናት፣ በአንድነት ተሰባስበው እየተማሩ እንዲያድጉ በማድረግ፤ የተጎዱ አብያተ ክርስቲያናት እንዲታደስ፣ በተለያዩ ቦታዎች አዳዲስም አብያተ ክርስቲያናት እንዲሠሩ ማድረግ የቅዱስነታቸው የዘወትር ተግባር ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ጠንካራ ሥራ ከሀገር፣ ከአህጉርና ከወገን አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና አግኝቶ ከተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን የናንሰን ሜዳይ ተሸልመዋል፡፡
​​በአጠቃላይ ቅዱስነታቸው በፕትርክና ዘመናቸው የቤተክርስቲያንን ሉዓላዊነት ያስከበሩ፣ የቋንቋ ባለቤትና የባለ ምጡቅ አእምሮ ባለቤት ሲሆኑ፤ በመስቀል ደመራና በጃንሜዳ ባሕረ ጥምቀት በሚያስተምሯቸው ትምህርቶችና በሚያስተላልፏቸው ዓለማቀፋዊ መልእክቶች የብዙ ቱሪስቶችን ቀልብ የሳቡ ነበሩ፡፡ የጥምቀት በዓል በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባሕል ድርጅት United Nations Educational, Scientific and Cultural Organization( UNESCO) በማይዳሰስ ቅርስነት እንዲመዘገብ ያደረጉና በብዙ ኢትዮጵያውያን ልብ ሲታወሱ የሚኖሩ አባት ናቸው፡፡
በዓለ ዕረፍት
እሑድ ነሐሴ ፲ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም የቅዱስነታቸው ክቡር ሥጋቸው ባረፈበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ ካህናት፣ ምእመናንን የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች፣ያሳደጓቸው የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው፣ በተገኙበት ከጧቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ ጸሎተ ፍትሐት ይደረጋል፡፡
የብፁዕ ወቅዱስ አባታችን በረከታቸው ይድረሰን፡፡ አሜን!!!
@የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000066.jpeg 336 336 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-08-15 11:45:542026-08-15 11:45:54የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ (ዶ/ር) ፲፬ኛ ዓመት በዓለ ዕረፍት መታሰቢያ
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለ272 አገልጋዮች ሥልጣነ ክህነት ሰጡ።
  • የደብረ ታቦር በዓል በምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከበረ።
  • ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ በባሕታዊ አባ ተስፋ ማርያም ሕልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ኅዘን በመግለጽ አባታዊ መልዕክት አስተላልፈዋል፤ የብፁዕነታቸው አባታዊ መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይነበባል::
  • ብፁዕ ጠቅላዬ ሥራ አስኪያጂና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ቤተክርስቲያን የምታከናውናቸውን የልማት ሥራዎች አፈጻጸምን ተዘዋውረው ተመለከቱ።
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት 14ኛ ዓመት መታሰቢያ በዓል ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድሥት ሥላሴ ካቴድራል በመከበር ላይ ይገኛል።

Archives

  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: 14ኛ ዓመት ዕረፍት መታሰቢያ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ Link to: 14ኛ ዓመት ዕረፍት መታሰቢያ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ 14ኛ ዓመት ዕረፍት መታሰቢያ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ... Link to: የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ለተመደቡት ለመልአከ ብርሃን መምህር ሰሎሞን በቀለ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። Link to: የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ለተመደቡት ለመልአከ ብርሃን መምህር ሰሎሞን በቀለ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top