ልማት በቤተ ክርስቲያን

ልዮ ዕትም መጽሔት

ይህ ”ልማት በቤተክርስቲያን“ የተሰኘ ልዮ ዕትም መጽሔት ጽርሐ ምኒሊክ ወይም በተለምዶ መሐሙድ ሕንጻ በመባል የሚታወቀው ሕንጻ ፈርሶና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሙሉ ወጪ ተገንብቶ ለምርቃት መብቃቱን በማስመልከት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ተዘጋጀ።

ዜናዎች እና ወቅታዊ ክንውኖች

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የአክትስ ቸርች ኦፍ ሱዲን የሥራ ኀላፊዎችን   በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

የካቲት 1 ቀን 2017.ዓ.ም.

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኀበር ባካሔደው የነዳያን ምገባ መርሐ ግብር ላይ ተገኝተው ነዳያንን ከመገቡ በኋላ ቃለ በረከትና ቃለ ቡራኬ ሰጡ።

ጥር 29 ቀን 2016 ዓ.ም

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የ2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ መግለጫ ሙሉ መልእክት የሚከተለው ነው፡፡

ጥር ፳፱ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የግብፅ  ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ልዑካንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

ጥር 24 ቀን 2017 ዓ.ም

የ”ዝክረ ኒቅያ ዓለም አቀፍ ጉባኤ” ከሚያዚያ 20-24 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚካሔድ ሊቃውንት ጉባኤ አስታወቀ።

ጥር 23 ቀን 2017 ዓ.ም

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ልዑካንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

ጥር 20 ቀን 2017.ዓ.ም.

የጥምቀት በዓል ብፁዕ አቡነ አብርሃም በተገኙበት በባሕር ዳር በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ።

ጥር ፲፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም

መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ

ጥር ፲፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የእድሳት ሥራ ተጠናቆ በቅዱስ ፓትርያርኩ እየተመረቀ ነው።

ጥር ፮ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም

የ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም የጥምቀት በዓል ዝግጅት ዐቢይ ኮሚቴ በጃን ሜዳ እስከ አሁን የተከናወኑትን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ተዘዋውሮ ተመለከተ።

ጥር ፮ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም

በፌስቡክ ያግኙን

የኅትመትና ሚዲያ ዋና ክፍል

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ

የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ

የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የደቡብና የደቡብ ምሥራቅ ትግራይና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ልማት በቤተ ክርስቲያን

ይህ ልዩ ዕትም መጽሔት ጽርሐ ምኒሊክ ወይም በተለምዶ መሐሙድ ሕንጻ በመባል የሚታወቀው ሕንጻ ፈርሶና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሙሉ ወጪ ተገንብቶ ለምርቃት መብቃቱን በማስመልከት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ተዘጋጀ።

ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

ርእይ

ሁለንተናዊ ስብእናው የተጠበቀ፣ በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የደመቀ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ መንፈሳዊና ሥጋዊ ጣዕመ ሕይወትን የተላበሰ፣ ለእግዚአብሔር መንግሥት ዝግጁ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀጣይነት በዝቶ ማየት

ተልእኮ

  • የእግዚአብሔርን ቃል ለሰው ልጆች ሁሉ ማስተማርና ማዳረስ

  • ሰውን በሁለንተናዊ ሰብእናው ማገልገልና ማዳን

  • ሰውን ሁሉ በነገረ መለኮትና በነገረ ጥበብ ትምህርት በማልማት በመንፈሳዊም ሆነ በሥጋዊ ሕይወቱ የተሻለ ኑሮ እንዲኖረው ማድረግ

  • ጥራትና ብቃት፣ ፍትሐዊነትና እኩል ተደራሽነት ያለው መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ለሰው ሁሉ ማበርከት

  • የተለያዩ የልማት መርሀ ግብሮችን በመንደፍ ቤተ ክርስቲያንን በኢኮኖሚ ማበልጸግ

  • በቴክኖሎጂ ስልት የሚመራና አዋጭነቱ አስተማማኝ የሆነ የጠቅላላ ሀብት አስተዳደርና አጠቃቀም እንዲረጋገጥ ማድረግ

  • የሰው ልጆች ሁሉ እኩልነት፣ ሰላምና ፍትሕ፣ ፍቅርና ስምምነት እንዲጠበቅ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ

  • የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አሰራር ግልጽ፣ ለሁሉም ተደራሽና ችግር ፈቺ እንዲሆን ማድረግ

ዕሴቶች

  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኅሊናን የሚረታ፣ አእምሮን የሚመሥጥ፣ ከጥንተ ፍጥረት ተነሥቶ በዘመነ አበው በሕገ ልቡና፣ በዘመነ ብሉይ በሕግ ኦሪት፣ ተራምዶ መዳረሻውን ሕገ ወንጌል ያደረገ ጥንታዊ ክርስቶሳዊና ሐዋርያዊ ትምህርተ ሃይማኖት፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን፣ በያሬዳዊ ጣዕመ ዜማ የታጀበ ሥርዐተ አምልኮ፣ በጽሑፍና በትውልድ ቅብብሎሽ የተወረሰ የረጅም ጊዜ ትውፊት ባህልና ታሪክ

  • በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የበለጸገ፣ እግዚአብሔርን የሚወድና የሚፈራ ለእግዚአብሔር የሚታዘዝና ምክረ ካህን የሚቀበል ከስልሳ ሚልዮን በላይ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ

  • ለምጣኔ ሃብት ዕድገት እጅግ የምትጠቅም በውብ ሥነ ተፈጥሮና በሥነ ጽሑፍ፣ በሥነ ጥበብና በኪነ ጥበብ፣ በታሪክና በቅርስ ሃብት የበለጸገች እንዲሁም በሃይማኖት፣ በነጻነትና በአንድነት የደመቀች ሃገር

  • የእግዚአብሔርን ቃል ከሃገር ውስጥ ባሻገር ለመላው ዓለም ማዳረስ የሚችሉ ከግማሽ ሚልዮን ያላነሱ ሊቃውንት፣ ቀሳውስት፣ ዲያቆናት፣ ሰባክያነ ወንጌል እንዲሁም ከሁለት ሺሕ ያላነሱ ገዳማት

  • መላውን ዓለም እያዳረሰና እየሰፋ የሚገኝ ከአጥቢያ ጀምሮ እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ የተዋቀረ ጠንካራ መዋቅር ያላት መሆኗ

ያግኙን

+251 111 55 0098 P.O.Box 1283 A.A. 5 KILLO, ADDIS ABABA, ETHIOPIA በፌስቡክ ያግኙን የዩትዩብ ቻነል የቴሌግራም ቻነል