ዜናዎች እና ወቅታዊ ክንውኖች

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት እንዲሁም በመላው ዓለም የምትገኙ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምዕመናን ወምዕመናት እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም አደረሳችሁ አሸጋገራችሁ

“ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ ወይጸግቡ ጠላተ ገዳም –  በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል” መዝ ፡ ፷፬ ( ፷፭ ) ፥ ፲፩

“አስመ የአክለክሙ ዘኀለፈ መዋዕል ዘገበርክሙቦቱ ፈቃዶሙ ለአህዛብ”“የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና” /1ኛ ጴጥ. 4፥3/፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
አባ ሕርያቆስ የሀድያ ስልጤ የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ዐሠርቱ ወሰብዓቱ ዓመተ ምሕረት

አዲሱ ዘመን በሃይማኖት መንፈስ ግጭትን በውይይት፤ መለያየትን በአንድነት፤ አለመግባባትን በዕርቅ ፈትተን በመታደስ ማማ ላይ የቆመ ማኅበረ ሰብን ለመገንባት ሁላችንም ጥረት እንድናደርግ በእግዚአብሔር ስም መልእክታችንን እናስተላልፋለን፡፡

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የበጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ውይይት አደረገ።

ሀገረ ስብከቱ የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም ጥቅል የሥራ አፈጻጸም ውይይት በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የበላይ ሐላፊ በብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ መሪነት መከናወኑ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በዛሬው ዕለት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡ የመልዕክቱ ሙሉ ቃል ከዚህ እንደሚከተለው ይነበባል፡፡

“ለቤተክርስቲያን አይደለም ጥቅማጥቅማችንን አንገታችን እንሰጣለን” ብፀዕ አቡነ አብርሃም

ጷጉሜን ፬ ቀን ፪፻፲፮ ዓ.ም.

ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት መካከል አንዱ የሆነው ቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት በርዕሰ አድባራት ወገዳማት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል በድምቀት ተከበረ።

ጷጉሜን ፫ቀን ፳፻፲ወ፮ ዓ.ም

የመልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል በዓለ ንግሥ በዲላ ዋለሜ ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን በድምቀት ተከበረ

ጳጉሜ 3/2016 ዓ.ም

በሲዳማ ሀገረ ስብከት በሀዋሳ ከተማና ዙሪያ ወረዳ በሀዋሳ ከተማ በደብረ ታቦር ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሩፋኤል በዓለ ንግሥ በታላቅ ድምቀት ተከበረ።

ጳጉሜን 3/2016 ዓ/ም

በምሥራቅ ሐረርጌ ሀ/ስብከት በሐረር ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ቅ/ሚካኤል ወቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን የሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል በዓለ ሢመት የንሥስ በዓል

ጷጉሜን ፫  ፳፻፲፮ ዓ/ም

በፌስቡክ ያግኙን

የኅትመትና ሚዲያ ዋና ክፍል

ብፁዕ አቡነ አብርሃም

የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ

በሰሜን አሜሪካ የኒውዮርክ እና አከባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ

ለውስጥ አገልግሎት

የኢሜይል አገልግሎት

ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

ርእይ

ሁለንተናዊ ስብእናው የተጠበቀ፣ በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የደመቀ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ መንፈሳዊና ሥጋዊ ጣዕመ ሕይወትን የተላበሰ፣ ለእግዚአብሔር መንግሥት ዝግጁ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀጣይነት በዝቶ ማየት

ተልእኮ

  • የእግዚአብሔርን ቃል ለሰው ልጆች ሁሉ ማስተማርና ማዳረስ

  • ሰውን በሁለንተናዊ ሰብእናው ማገልገልና ማዳን

  • ሰውን ሁሉ በነገረ መለኮትና በነገረ ጥበብ ትምህርት በማልማት በመንፈሳዊም ሆነ በሥጋዊ ሕይወቱ የተሻለ ኑሮ እንዲኖረው ማድረግ

  • ጥራትና ብቃት፣ ፍትሐዊነትና እኩል ተደራሽነት ያለው መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ለሰው ሁሉ ማበርከት

  • የተለያዩ የልማት መርሀ ግብሮችን በመንደፍ ቤተ ክርስቲያንን በኢኮኖሚ ማበልጸግ

  • በቴክኖሎጂ ስልት የሚመራና አዋጭነቱ አስተማማኝ የሆነ የጠቅላላ ሀብት አስተዳደርና አጠቃቀም እንዲረጋገጥ ማድረግ

  • የሰው ልጆች ሁሉ እኩልነት፣ ሰላምና ፍትሕ፣ ፍቅርና ስምምነት እንዲጠበቅ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ

  • የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አሰራር ግልጽ፣ ለሁሉም ተደራሽና ችግር ፈቺ እንዲሆን ማድረግ

ዕሴቶች

  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኅሊናን የሚረታ፣ አእምሮን የሚመሥጥ፣ ከጥንተ ፍጥረት ተነሥቶ በዘመነ አበው በሕገ ልቡና፣ በዘመነ ብሉይ በሕግ ኦሪት፣ ተራምዶ መዳረሻውን ሕገ ወንጌል ያደረገ ጥንታዊ ክርስቶሳዊና ሐዋርያዊ ትምህርተ ሃይማኖት፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን፣ በያሬዳዊ ጣዕመ ዜማ የታጀበ ሥርዐተ አምልኮ፣ በጽሑፍና በትውልድ ቅብብሎሽ የተወረሰ የረጅም ጊዜ ትውፊት ባህልና ታሪክ

  • በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የበለጸገ፣ እግዚአብሔርን የሚወድና የሚፈራ ለእግዚአብሔር የሚታዘዝና ምክረ ካህን የሚቀበል ከስልሳ ሚልዮን በላይ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ

  • ለምጣኔ ሃብት ዕድገት እጅግ የምትጠቅም በውብ ሥነ ተፈጥሮና በሥነ ጽሑፍ፣ በሥነ ጥበብና በኪነ ጥበብ፣ በታሪክና በቅርስ ሃብት የበለጸገች እንዲሁም በሃይማኖት፣ በነጻነትና በአንድነት የደመቀች ሃገር

  • የእግዚአብሔርን ቃል ከሃገር ውስጥ ባሻገር ለመላው ዓለም ማዳረስ የሚችሉ ከግማሽ ሚልዮን ያላነሱ ሊቃውንት፣ ቀሳውስት፣ ዲያቆናት፣ ሰባክያነ ወንጌል እንዲሁም ከሁለት ሺሕ ያላነሱ ገዳማት

  • መላውን ዓለም እያዳረሰና እየሰፋ የሚገኝ ከአጥቢያ ጀምሮ እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ የተዋቀረ ጠንካራ መዋቅር ያላት መሆኗ

ያግኙን

+251 111 55 0098 P.O.Box 1283 A.A. 5 KILLO, ADDIS ABABA, ETHIOPIA በፌስቡክ ያግኙን የዩትዩብ ቻነል