የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት የቢሮ ዕድሳት ሥራ ያለበትን ደረጃ ተመለከቱ

March 29, 2026

መጋቢት 20ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣
የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት የሚያከናውነውን የቢሮ ዕድሳት ሥራ አፈጻጸምን ከጠቅላይ ቤተክህነት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን ዛሬ ረፋዱ ላይ ተዘዋውረው ተመለከቱ።
ብፅዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ድርጁቱ የሚያከናውነው የቢሮ ዕድሳት ሥራ የደንበኛችን ምቹ አገልግሎት የማግኘት ዕድልን የሚያሰፋውንና ለቴክኖሎጂ ሽግግር ምቹ ሁኔታን የፈጠረ መሆኑን ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክትና በሰጡት የሥራ መሠሪያ ገልጸዋል። አያይዘውም የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት አሰራሩን ለማዘመንና ተደራሽነቱን በማስፋት አሰራሩን ከደንበኛ ተኮር የአገልግሎት ዐይነት ጋር በማቀናጀት ለመፈጸም የሚያደርገውን ጥረት አድንቀው ይህንን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግም ከቤተክርስቲያን ምንም አይነት ወጪ ሳይጠይቅ በጎ አድራጊ ምዕመናንን በማስተባበር ቢሮውን በዘመናዊ መልኩ ማደስና ማደራጀት መጀመሩ የሚደነቅና የሚያስመሰግን ተግባር ነው ብለዋል።
ድርጅቱ በፍጥነት በመለወጥና በማደግ ላይ እንደሚገኝ የገለጹት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ይህንን በመምራትና በማስተባበር በግንባር ቀደምነት የሚጠቀሱት የድሮጅቱ ዋና ሦራ አስኪያጅ ሊቀ ሥዩማን እስክንድር ገብረክርስቶስ ምስጋናና አድናቆት ይገባቸዋል። ካሉ በኋላ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የቢሮ ዕድሳት ሥራ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ከእድሳት ሥራ አፈጻጸሙ መቀላጠፍ የተረዱ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በተመሳሳይ ዜና ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በጠቅላይ ቤተክህነት አካባቢ የሚኖሩ ወገኖች በአካባቢው የተጋረጠውን የእሳት አደጋ የመፈጠርን ዕድል ተከትሎ በአስቸኳይ እንዲነሱ
የሚደረጉ ነዋሪዎች በጊዜየያዊነት የሚያርፉበት ቦታ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት አማካኝነት በልደታ አካባቢ እየተሰራ መሆኑን ተከትሎ የጊዜያዊ ማረፊያ ቤት የግንባታ ሂደትን በትላንትናው ዕለት የተመለከቱ ሲሆን ድርጅቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይህን የመሰለ ማረፊያ ቤት በመስራት ዝግጁ በማድረጉ ሊመሰገን ይገባዋል ብለዋል።
በመጨረሻም የተጀመረውን የጊዚያዊ ማረፊያ ቤቶችን ግንባታ
በአስቸኳይና በጥራት በማጠናቀቅ ነዋረመዎችን የማዘዋወሩን ሥራ በፍጥነት ማከናወን እንደሚገባ ገልጸው ነዋሪዎቹ በሚያርፉበት ቦታ ላይ መብራት፣ውኃ፣መጸዳጃና ማብሰያ ቦታውች በአስቸኳይ ተሟልተው እንዲጠናቀቅ መመሪያ ሰጥተዋል።በአሁኑ ጊዜ በልደታ አካባቢ የሚከናወነው የግንባታ ሥራ ከሰማኒያ በመቶ በላይ የተጠናቀቀ ሲሆን በሦስት ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ አልቆ ነዋሪዎችን የማዘዋወሩ ሥራ እንደሚጀመርና በፒያሳ አካባቢም በተመሳሳይ መልኩ በአጭር ጊዜ ውስጥ ቤቶቹ ተሰርተው ነዋሪዎችን የማዘዋወሩ ሥራ እንደሚከናወን የድርጅቱ የዕቅድና ልማት ክፍል ኃላፊ መምህር ታዲዮስ ሽፈራሁ ገልጸዋል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/0031.jpg 427 640 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-03-29 10:23:372026-05-05 10:25:30ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት የቢሮ ዕድሳት ሥራ ያለበትን ደረጃ ተመለከቱ
Search Search

Recent Posts

  • የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ትርጓሜ ምስክር ት/ቤት በባሕር ዳር ከተማ ለሚያስገነባው “የሕክምና መንደር” የመሠረት ድንጋይ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተቀመጠ።
  • የላሊበላ ቅርሶችን ለመጠበቅ የሚያስችል ውይይት ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ።
  • በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) እና የዲጂታል ሽግግር አማካሪ ኮሚቴ ለአስተዳደር ጉባኤው በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየሠራ ያለውን የተለያዩ የጥናት ሰነዶች አቀረበ፡፡
  • የቤቶችና ሕንጻዎች ልማት ድርጅት ሠራተኞቹን አመሰገነ።
  • “ተመራቂዎች በየተሰማሩበት የስምሪት መስክ ሁሉ እንደ መብራት ሊያበሩ ይገባል” ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ሳዊሮስ ሥልጠና በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ከትናት በተሻለ መልኩ ለመሥራት በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን ገለጹ Link to: ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ሳዊሮስ ሥልጠና በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ከትናት በተሻለ መልኩ ለመሥራት በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን ገለጹ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ሳዊሮስ ሥልጠና... Link to: የጌታችን የአምላካችን የመድኃኔዓለም ጥንተ ስቅለት በዓል በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በከታ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል በታላቅ ድምቀት ተከበረ፡ Link to: የጌታችን የአምላካችን የመድኃኔዓለም ጥንተ ስቅለት በዓል በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በከታ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል በታላቅ ድምቀት ተከበረ፡ የጌታችን የአምላካችን የመድኃኔዓለም ጥንተ ስቅለት...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top