የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

“ዝክረ ወንጌል ወዝክረ ሊቃውንት”በሚል መሪ ቃል በስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ከትምህርትና ማሰልጠኛ መምሪያዎች ጋር በመሆን የሁለት ቀናት የምክክር ጉባኤ አዘጋጀ።

July 2, 2025

ሰኔ ፳፬ ቀን ፳፻፲ወ፯ ዓ.ም
“”””””””””””””””””””””””””””””””””
አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ
+++++++++++++
በመንበረ ፖትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽርሐ ተዋህዶ አዳራሽ “ዝክረ ወንጌል ወዝክረ ሊቃውንት”በሚል መሪ ቃል በስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ከትምህርትና ማሰልጠኛ መምሪያዎች ጋር በመቀናጀት የምክክር ጉባኤ አዘጋጀ።

ሰኔ ፳፬ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም በተዘጋጀው በዚህ ጉባኤ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት እና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተገኝተዋል።

መርሐ ግብሩም በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጸሎተ ቡራኬ የተከፈተ ሲሆን ቅዱስነታቸውም የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክትም አስተላልፈዋል።

ቅዱስነታቸው በመልዕክታቸው ቤተ ክርስቲያን የምትጠበቀው በካህናትና በምዕመናን ነው ያሉ ሲሆን ለዚህም ቤተ ክርስቲያንን እና ሃይማኖታችንን ለመጠበቅ እየተሰበሰቡ መመካከር አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ወቅታዊውን የበሀገራችንን ሁኔታንም በማስታወስ አሳሳቢነቱን የጠቀሱት ቅዱስነታቸው ለዚህም ቤተክርስቲያንን ጠንክረን መጠበቅ አለብንም ሲሉ መክረዋል።

ይህችን ቤተ ክርክቲያን የሚቃረኗት ብዙ መሆናቸውንም ጠቅሰው ለዚህም ሁላችሁም ኃላፊነታችሁን ለመወጣት መሰል ጉባኤያት አስፈላጊም ኃላፊነትም ነው ሲሉ ቤተ ክርስቲያንን ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ ነቅቶ መጠበቅ እንደሚያሻ አባታዊ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዕለቱ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስም የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም ሐዋርያትን በዓለም ዞረው ወንጌልን መስበካቸውን ጠቅሰው የሐዋርያትን ፈለግ የተከተለችው ቤተ ክርስቲያን በየዘመኑ ከመናፍቃን ጋር ያደረገችውን ተጋድሎም አንስተዋል።ለዚህም በዋቢነት በዓለም አቀፍ ደረጃ የተደረጉ ጉባኤያትን አንስተው አርዮስን፣መቅዶንዮስ እና ንስጥሮስን አውግዛ መለየትዋን ገልጸዋል።

ዛሬም ቤተ ክርስቲያን ተልዕኮዋ ወንጌልን ተደራሽ ማድረግ እና ተልዕኮዋን እንዳትወጣ የሚያደርጓትን ችግሮችን መቅረፍ እና አውግዞ መለየት ነውም ሲሉ አክለዋል።

“ዝክረ ወንጌል ወዝክረ ሊቃውንት”በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው ይህ ጉባኤ የስብከተ ወንጌልን እና የአብነት ትምህርትን ለማስፋፋት ያለመ መሆኑን የጠቀሱት ደግሞ የትምህርትና ማሰልጠኛ መምሪያ ዋና ኃላፊ መጋቤ ሐዲስ ኃይለ እግዚ አሰፋ ሲሆኑ በበኩላቸው በሰጡት ማብራሪያ መርሐ ግብሩ በጥምረት መዘጋጀቱ ያለውን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አንስተዋል።

ሁለቱም መምሪያዎች ቀደምት መሆናቸውንም ጠቅሰው ምንም እንኳ የተለያየ የሥራ ዘርፍ ቢኖራቸውም በስብከተ ወንጌል ረገድ ያላቸውን አንድነትም አብራርተዋል።

በመሆኑም ከወርሐ መጋቢት ጀምረው በጥምረት መስራት መጀመራቸውን ገልፀው ሊሰሩ ያሰቧቸውንም ዘርፈ ብዙ የሥራ መስኮችም በዝርዝርና በቁጥር አቅርበዋል።

መላከ ሰላም ቆሞስ አባ ቃለ ፅድቅ ሙሉጌታ (ዶ/ር) የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያም በበኩላቸው ጉባኤው ውጪያዊውን ችግሮች ለመፍታት የተዘጋጀ ሳይሆን ውስጣዊ ችግሮችን ለማየት እና ለመፈተሽ የተዘጋጀ ጉባኤ መሆኑን ገልጸዋል።

መላከ ሰላም “መንፈሳዊነት ለሁለንተናዊ አገልግሎት” በሚል ርዕስም ጥናታዊ ጽሑፍ ያቀረቡ ሲሆን በጥናታዊ ጽሑፋቸውም የመንፈሳዊነትን ምንነት ዳሰዋል።

ቤተ ክርስቲያን የምትሰጠው ትምህርት ትውፊታዊ መሆኑንም የጠቀሱ ሲሆን ያ ወንጌል ቀለም ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊነትንም የያዘ እና እኛም የወረስነው ነው ሲሉ መንፈሳዊነትን በተለያየ መልክ አብራርተዋል።

በመጨረሻም በቀረቡ ጥናታዊ ጽሑፍ ዙሪያ ሰፊ ሀሳብ እና አስተያየት የተሰጠ ሲሆን በዋናነት በመምህራን ረገድ ያለው የእውቀት ክፍተት እና የመንፈሳዊነት ዝለት ተነስቷል።

መርሐ ግብሩ በቀጣይም በየዓመቱ የሚዘጋጅ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በከሰዓቱም ውሎም የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎች የሚቀርቡበት ሲሆን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ቤተ መጽሐፍትና ወመዘክር ጉብኝት የሚቋጭ መሆኑ ታውቋል።
በዕለቱም ብፁዓን አበው ላቃነ ጳጳሳት፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች፤የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች እንዲሁም የሚዲያ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

መርሐ ግብሩ ለሁለት ቀናት የተዘጋጀ ሲሆን በነገው ዕለትም ቀጥሎ ይውላል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያስገነባውን ባለ ሰባት ወለል ሁለገብ ምትክ ሕንጻ ለቅድስት ቤተክርስቲያን አስረከበ። Link to: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያስገነባውን ባለ ሰባት ወለል ሁለገብ ምትክ ሕንጻ ለቅድስት ቤተክርስቲያን አስረከበ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያስገነባውን ባለ... Link to: “ዝክረ ወንጌል ወዝክረ ሊቃውንት”በሚል መሪ ቃል በስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ከትምህርትና ማሰልጠኛ መምሪያ ጋር በመሆን ያዘጋጀው የሁለት ቀናት የምክክር ጉባኤ የአቋም መግለጫ አውጥቷል የአቋም መግለጫው ሙሉ ቃል Link to: “ዝክረ ወንጌል ወዝክረ ሊቃውንት”በሚል መሪ ቃል በስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ከትምህርትና ማሰልጠኛ መምሪያ ጋር በመሆን ያዘጋጀው የሁለት ቀናት የምክክር ጉባኤ የአቋም መግለጫ አውጥቷል የአቋም መግለጫው ሙሉ ቃል “ዝክረ ወንጌል ወዝክረ ሊቃውንት”በሚል መሪ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top