የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የሲዳማ ሀገረ ስብከት ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ለብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የታቦር ፍኖተ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የእንኳን አደረሰዎ መርሐ ግብር አካሄደ።

September 17, 2024

መስከረም 5/2017 ዓ/ም
=======================
በመረሐ ግብሩ ላይ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ጥበባት ሞላልኝ መርጊያ፣የሀገረ ስብከቱ ም/ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ሃይማኖት ነጻነት አክለወግ፣የሀዋሳና ዙሪያ ወረዳ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ላዕከ ወንጌል ደግፌ ባንቡራ፣የሀገረ ስብከቱ የየመምሪያ ኃላፊዎችና ልዩ ልዩ ሠራተኞች፣የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣የገዳማትና የአድባራት ም/ሊቃነ መናብርትና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች የተገኙ ሲሆን መርሐ ግብሩ በብፁዕነታቸው ጸሎት ተጀምሯል።

– በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ያሬዳዊ ዜማና ቅኔ ቀርቧል።
– በመቀጠልም የሲዳማ ሀገረ ስብከት የአድባራትና የገዳማት አስተዳዳሪዎችና ተወካዮች የእንኳን አደረሰዎ መልእክታቸውን ለብፁዕነታቸው አስተላልፈዋል።
– የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ጥበባት ሞላልኝ መርጊያም ብፁዕነታቸውን እንኳን አደረሰዎ በማለት ያለፈው 2016 ዓ/ም እንደ ሀገረ ስብከት ስኬታማ ነን።

በብፁዕነታቸው መመሪያ ሰጭነትና አርቆ አሳቢነት በተለይ በስብከተ ወንጌል ሰፊ ሥራዎች ተሠርተዋል። ለአብነት ያህል ሀገረ ስብከት አቀፍ ጉባኤ ከርእሰ ከተማው እስከ ወረዳ ከተማዎች በማዘጋጀት የሲዳማ አፎ( ቋንቋ) ሰባክያንን በማሠማራት፣ በዚህ አዳዲስ አማንያን በብዛት መጠመቅ፣የብያተ ክርስቲያናት መስፋፋት፣አሁን ያረፍንበት መንበረ ጵጵስና በአጭር ጊዜ ተሠርቶ ብፁዓን አባቶች በተገኙበት ተመርቆ ሥራ ላይ መዋል፣በፍጥነት እየተገነባ ያለው ሎጎስ ሕንጻ እና የመሳሰሉት የተሠሩበት ዓመት በመሆኑ ስኬታማ ነን ማለት እንድንችል አድርጎናል። ለዚህም ትልቁ ድርሻ የብፁዕ አባታችን በመሆኑ በድጋሚ ብፁዕ አባታችንን እንኳን አደረስዎ ብላችሁ አመስግኑልኝ በማለት ሀሳባቸውን አጠቃልለዋል።

በመጨረሻም ብፁዕ አባታችን አቡነ ዮሴፍ በክቡር ሥራ አስኪያጁ እንደተገለጠው በ2016 ዓ/ም በእናንተ በጋራ ትብብር ብዙ ሥራዎች ተሠርተዋል። እንደምሳሌ ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ ዓመት እያከበርንበት ያለው መንበረ ጵጵስና ዛሬ እንሥራው ብንል አንችልም። ምክንያቱም ትናንት ዛሬ ስላልሆነ። ስለዚህ ዛሬም መሥራት ያለብንን ካልሠራን ነገ ሌላ ቀን ነው።ለነገ ዛሬ መሥራትን መልመድ አለብን።

ሌላው ከሀገረ ስብከት ጀምሮ እስከ አጥቢያ ያለ አገልጋይ ከሕዝቡ ጋር መግባባት ያስፈለጋል። ስህተትም ከተፈጠረ ዝም ብሎ ከማለፍ ይልቅ ማረም ያስፈልጋል። ነህምያን መሆን አለብን ነህምያ የፈረሰውን ለመገንባት ወገኖቹን ያበረታታ ነበር። ዛሬም በመካከላችን ብዙ የፈረሱ ነገሮች ስላሉ ተመልሰው እንዲገነቡ መሥራት ከካህናት ይጠበቃል።መሪዎች እንደመሆናችን እንደ ሰሎሞን አስተዋይ መሆን ያስፈልጋል። ካልሆነ ይህን ዓለም ቀድመን መምራት አንችልም።

በአጠቃላይ እግዚአብሔርን ካስቀደምን በጸሎት ከጸናን እግዚአብሔርም ከእኛ ጋር ከሆነ ይህን የመከራ ጊዜ ማለፍ እንችላለን ለዚህ ግን ማንበብ መጠየቅ ራስን ማብቃት መሠረታዊ ጉዳይ ነው። በጥቅሉ ዘመኑን የሰላም የፍቅር የበረከት ዘመን ያድርግላችሁ የሚል አባታዊ መልእክት አስተላልፈው በብፁዕነታቸው ጸሎትና ቡራኬ የፕሮግራሙ ፍጻሜ ሆኗል።

መረጃው የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት ነው

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ለቤተ ክርስቲያኗ ከፍተኛ መሪዎች «የእንኳን አደረሳችሁ» ስጦታ አበረከተ።
  • የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ተምሮ ማስተማር ሰንበት ትምህርት ቤት ላለፉት ሁለት ዓመታት ያሰተማራቸውን ደቀ መዛሙርት አስመረቀ !!!
  • ጳጉሜ የሚለው ስያሜ ‹‹ኤፓጉሜኔ›› ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ‹‹ጭማሪ›› ማለት ነው፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መዝገበ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገብ ቃላት፤ ገጽ ፱፻፭)
  • የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሠራተኞች ለተባባሪ ፕሮፌሰር ለብፁዕ አቡነ ፊልጶስ(ዶ/ር) የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በመመረቃቸው ልዩ የደስታና የምስጋና መርሐ ግብር አካሄዱ።
  • “መስከረም በአታ የሃያ ሺህ ሰዎች ምሥረታ” በሚል የታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም የአብነት ትምህርት ቤት ሕንጻ ግንባታ ድጋፍ ማስጀመሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ በተገኙበት ተሰጠ።

Archives

  • September 2026
  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት በብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የተመራ የመስቀልና ደመራን በዓል አስመልክቶ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመንበረ ጵጵስና አዳራሽ ስብሰባ ተካሄደ። Link to: በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት በብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የተመራ የመስቀልና ደመራን በዓል አስመልክቶ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመንበረ ጵጵስና አዳራሽ ስብሰባ ተካሄደ። በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት በብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ... Link to: የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ እያካሔደ ይገኛል። Link to: የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ እያካሔደ ይገኛል። የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት አጠቃላይ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top