የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

“የአበው ሥርዓት ለቤተ ክርስቲያን አንድነት” በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የቆየውን የገዳማት አበምኔቶችና እመምኔቶች አገር አቀፍ ጉባኤ ተጠናቀቀ

May 1, 2026

ሚያዚያ ፳፫ ቀን ፳፻፲ወ፰ዓ.ም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የገዳማት አስተዳደር መምሪያ ባዘጋጀው መርሐ ግብር፤ ከመላው ኢትዮጵያ የአንድነት ገዳማት ለተውጣጡ አበምኔቶች እና እመምኔቶች “የአበው ሥርዓት ለቤተ ክርስቲያን አንድነት” በሚል ርዕስ ሲሰጥ የነበረው የሥልጠና እና የምክክር ጉባኤ ፍጻሜውን አግኝቷል።
ከሚያዝያ ፳፪ እስከ ሚያዚያ ፳፫ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
ድረስ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በተካሄደው በዚህ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ፤ የገዳማቱን አስተዳደራዊ እና መንፈሳዊ አቅም የሚያጎለብቱ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል። ከዚህም ባለፈ ተሳታፊዎቹ አባቶች እና እናቶች እርስ በርስ የልምድ ልውውጥና ጥልቅ ምክክር ያደረጉ ሲሆን፣ ከብፁዓን አባቶችም አባታዊ ቃለ ምዕዳን ተሰጥቷቸዋል።
በጉባኤው ላይ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የደቡብ ምዕራብና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ፣
የመንበረ ፓትርያርክ የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የባሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም ብፁዕ አቡነ ቶማስ የምሥራቅ ጎጃም፣ የመተከል እና አዊ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተገኝተዋል። በተጨማሪም
የገዳማት መምሪያ ዋና ኃላፊ መጋቤ ካህናት አባ ሀብተ ጊዮርጊስ ዓሥራትን ጨምሮ ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የመጡ የገዳማት
አበምኔቶች (አባቶች) እና እመምኔቶች (እናቶች) የጉባኤው ተካፋይ ነበሩ።
በመዝጊያው መርሐ ግብር ላይ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ሰፋ ያለ አባታዊ መልእክትና መመሪያ አስተላልፈዋል። ብፁዕነታቸው በንግግራቸው “ገዳማት የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የጽናት መሠረቶች ናቸው” በማለት አጽንዖት ሰጥተው፣ አባቶችና እናቶች በአንድነት መሰባሰባቸውና መወያየታቸው ትልቅ ውጤት ያመጣ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም “ለገጠሙን ችግሮች በጋራ ባደረግነው ውይይት መፍትሔ አግኝተናል፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ አሁን ካለችበት ሁኔታ አኳያ በመንፈሳዊ ሕይወታቸው የጸኑ ጠንካራ
መነኮሳት በእጅጉ ያስፈልጓታል። ስለዚህም ወደ ቀደመው እና ወደ ጥንታዊው የአበው መንፈሳዊ ሕይወት መመለስ ግድ ይለናል”
ብለዋል።
ከተሳታፊዎች ለተነሳው የማረፊያ ቦታ ጥያቄ በተመለከተም፣ ጉዳዩን አጥንተው ለቅዱስ ሲኖዶስ እንደሚያቀርቡ ብፁዕነታቸው ቃል ገብተዋል።
በመጨረሻም ገዳማውያኑ የቅዱስ ሲኖዶስ የጸሎት መሠረት መሆናቸውን በማስታወስ፣ “ጾምና ጸሎት ትልልቅ
መንፈሳዊ የጦር መሣሪያዎች በመሆናቸው ለሀገር እና ለቤተ ክርስቲያን ሰላም በትጋት ጸልዩ” ሲሉ አደራ ብለዋል።
ለሁለት ቀናት በስኬት ሲካሄድ የቆየው ይህ የምክክር እና የሥልጠና ጉባኤም፣ በአረጋዊው አባት በብፁዕ አቡነ ዮሴፍ
አባታዊ ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ ተጠናቋል።©EOTC t.v.

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/007.jpg 336 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-05-01 08:36:182026-05-05 08:39:13“የአበው ሥርዓት ለቤተ ክርስቲያን አንድነት” በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የቆየውን የገዳማት አበምኔቶችና እመምኔቶች አገር አቀፍ ጉባኤ ተጠናቀቀ
Search Search

Recent Posts

  • የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ትርጓሜ ምስክር ት/ቤት በባሕር ዳር ከተማ ለሚያስገነባው “የሕክምና መንደር” የመሠረት ድንጋይ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተቀመጠ።
  • የላሊበላ ቅርሶችን ለመጠበቅ የሚያስችል ውይይት ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ።
  • በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) እና የዲጂታል ሽግግር አማካሪ ኮሚቴ ለአስተዳደር ጉባኤው በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየሠራ ያለውን የተለያዩ የጥናት ሰነዶች አቀረበ፡፡
  • የቤቶችና ሕንጻዎች ልማት ድርጅት ሠራተኞቹን አመሰገነ።
  • “ተመራቂዎች በየተሰማሩበት የስምሪት መስክ ሁሉ እንደ መብራት ሊያበሩ ይገባል” ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: EOTC TV | የቤቶችና ሕንጻዎች ድርጅት የልማት ግሥጋሤ Link to: EOTC TV | የቤቶችና ሕንጻዎች ድርጅት የልማት ግሥጋሤ EOTC TV | የቤቶችና ሕንጻዎች ድርጅት የልማት ግሥ... Link to: በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በሰበታ ገላን ጉዳና ፉሪ የዓለም ገና ደብረ ቀርሜሎስ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ ተባረከ Link to: በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በሰበታ ገላን ጉዳና ፉሪ የዓለም ገና ደብረ ቀርሜሎስ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ ተባረከ በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በሰበታ ገላን ጉዳና...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top