የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም የትንሣኤ በዓልን ምክንያት የእንኳን አደረሰዎ መርሐ ግብር ተካሔደ።

April 17, 2023

ሚያዚያ ፲ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
*******
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
“”””””””””””””””””””

በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ክቡር ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያና የየድርጅቶቹ የሥራ ኃላፊዎች ክቡር ሊቀ አእላፍ በላይ ጸጋዬ የአዲስአበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ፣የአድባራትና ገዳማት ከስተዳዳሪዎች እና የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።

በዓሉን በማስመልከት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራትና ገዳማትን በመወከል መልዕክት የቀረበ ሲሆን ቅኔዎችም በሊቃውን ቀርቧል።

ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁም በአሉን በማስመልከት የእንኳን አደረሰዎ መልዕክት አስተላልፈዋል። በመልዕክታቸው ቤተክርስቲያን በውስጥና በውጪ የገጠማትን ፈተና ለመቋቋም ቅዱስነትዎ የሰጡት ትዕግስትና ብልሀት የተሞላበት አመራር የሚደነቅ ነው።
ብለዋል ። አያይዘውም አሁን ያለነወ አባቶች አንዲት ቤተክርስቲያን ፣አንድ ሲኖዶስ፣አንድ ፓትርያሪክ የሚለውን ክስስቲያናዊ መርህን ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ እንችል ዘንድ የሚጠበቅብንን ሁሉ እንድንወጣ አደራ እላለሁ ብለዋል።

በዚሁ መርሐ ግብር ላይም ሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅትም በዕለተቱ ለቅዱስነታቸው ሥጦታ ያበረከተ ሲሆን ድርጅቱ “ንግባእኬ ኀበ ጥንተ ነገር” በሚል መሪ ቃል፦
እንደአባቶቻችን ብራና ዳምጦ፣ብዕር ቀርጾ፣ ቀለም በጥብጦ፣የተለያዩ ማዕድናት አቅልጦ፣ ትውፌታቸውን የጠበቁ የብራና መጻሕፍቶችን ፣የብራና አና የገበቴ(የእንጨት) ቅዱሳት ስዕላትን፣የተለያዩ ንዋያተ ቅድሳቶችን ጥራታቸውን በጠበቀ መንገድ ያመርታል።

ድርጅቱ እስካሁን በመቶዎች የሚቆጠሩ የብራና መጻሕፍቶችን እና ቅዱሳት ስዕላቶችን በማምረት ለገዳማት፣ ለአድባራት፤ለአብያተ ጉባኤያት ና ለምዕመናን ከማቅረባቸውም ባሻገር ይህን የቀደምት ኢትዮጰያውያን አባቶቻችን ጥበብ ለትውልዱ እንዲተላለፍ የተለያዩ የስልጠና ማዕቀፎችን በማዘጋጀት ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

ዛሬም ይህንን በተቋማቸው የተዘጋጀውን በውስጡ ፭ ስዕላት፣፭ ሐረጋት ያካተተ የ ፬ቱ ወንጌላውያን የብራና ወርቅ ወንጌል የትንሣኤ በዓልን በማስመልከት ለብዑዕ ወቅዱስ አቡነ ምትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት አበርክተዋል።በመጨረሻም ቅዱስነታቸው ቃለ በረከትና ቃለ ቡራኬ በመስጠት የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: በቂም፣ በበቀል፣ በጥላቻ ወድቀን ትንሣኤውን እናከብራለን ማለት ትክክል እንዳልሆነ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ተናገሩ። Link to: በቂም፣ በበቀል፣ በጥላቻ ወድቀን ትንሣኤውን እናከብራለን ማለት ትክክል እንዳልሆነ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ተናገሩ። በቂም፣ በበቀል፣ በጥላቻ ወድቀን ትንሣኤውን እናከብራለን... Link to: ከወደቅንበት የራስን ጥቅም የማሳደድ አዚም ወጥተን የቤተ ክርስቲያንን ህልውና ሊያጸና የሚችለውን ሥራ እያስቀደምን ማገልገል የሁላችንም ውሳኔ መሆን እንዳለበት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ አሳሰቡ። Link to: ከወደቅንበት የራስን ጥቅም የማሳደድ አዚም ወጥተን የቤተ ክርስቲያንን ህልውና ሊያጸና የሚችለውን ሥራ እያስቀደምን ማገልገል የሁላችንም ውሳኔ መሆን እንዳለበት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ አሳሰቡ። ከወደቅንበት የራስን ጥቅም የማሳደድ አዚም ወጥተን...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top