የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መሪ እቅድ ትግበራ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ።

June 30, 2023

ሰኔ ፳፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም
“”””””””””””””””””””””
አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ
==============

በግንቦት ፳፻፲፭ ዓ/ም ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የጸደቀውንና ለቤተክርስቲያናችን መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት መሳለጥ ተጨባጭ ለውጥ ያመጣል ተብሎ የታመነበትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መሪ እቅድ በሠፊው የሚተነትንና የሚያስረዳ የአንድ ቀን ሥልጠና የመንበረ ፖትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት አስፈፃሚ አካላት ለሆኑት ለጠቅላይ ጽ/ቤቱ የመምሪያና ድርጅት ኃላፊዎችና ለምክትል ኃላፊዎች ተሰጠ።

በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽርሐ-ተዋሕዶ አዳራሽ የተሰጠው ሥልጠና በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፖትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ጸሎት እና አባታዊ መመሪያ የተከፈተ ሲሆን ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የኒው ዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በቅዱስ ሲኖዶስ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መሪ እቅድ ዓቢይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን የመንበረ ፖትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ምክትል ሥራ አሥኪያጅ በመክፈቻው መርሐ ግብር ላይ ታድመዋል።

ቅዱስነታቸው በመክፈቻው ሥነሥርዓት ላይ ባስተላለፉት አባታዊ መልእክት “ይህ መሪ እቅድ ቤተክርስቲያናችንን የሚጠቅም የቤተክርስቲያናችንን መንፈሳዊ አገልግሎት የሚያሳድግ ነው። ይህ መሪ እቅድ ተግባራዊ ከሆም ሥራዎች በአግባቡ ስለሚሠሩ የሚያማና የሚታማ ስለማይኖር ሁሉም አገልጋይ ለተግባራዊነቱ በቅንነትና በታማኝነት መረባረብ ይኖርበታል” ብለዋል።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም በበኩላቸው ባደረጉት የመግቢያ ንግግር የመሪ ዕቅድ ዝግጅቱ ከ፰ ዓመታት በላይ መውሰዱንና ዛሬ ለመምሪያና ለድርጅት ኃላፊዎችና ምክትል ኃላፊዎች ግንዛቤ በመሥጠት የተጀመረው የገለጻ መርሐ ግብር እስከ ወርኃ ጥቅምት ቀጥሎ እስከ አህጉረ ስብከት ላሉ የሥራ ኃላፊዎች እንደሚቀጥልና ከጥቅምት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በኋላ ወደ ሥራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናው በመሪ እቅዱ ላይ የተያዙ ሦስት (መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ) ዓበይት ዘርፎች ላይ አትኩሮት አድርጎ ተሰጥቷል።
የመጀመሪያውና የመንፈሳዊ ልማት ዘርፍ ላይ ያተኮረው ሥልጠና የመሪ ዕቅድ ትግበራ ዓቢይ ኮሚቴ አባል በሆኑት በዶ/ር በለጠ ብርሀኑ የተሰጠ ሲሆን ልማትና ኢኮኖሚ ላይ ያተኮሩት የመሪ ዕቅዱ ክፍል ደግሞ በዶ/ር ሰሎሞን ፀሐዬ ቀርቧል።

መርሐ ግብሩን ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ በመንበረ ፖትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የመሪ እቅድ ትግበራ መምሪያ ዋና ኃላፊ የመሩት ሲሆን የሥልጠናውን ሂደት በማሳለጥና ውይይቶችን በመምራት ረገድ የኮሚቴው አባል ሊቀ ትጉሃን በድሉ አሰፋ ሰፊ አገልግሎት ተሰጥተዋል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • የድሬዳዋ ሳባ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ያስገኘባው ባለ ሦስት ወለል ሁለገብ ሕንጻ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጸሎተ ቡራኬ በዛሬው ዕለት ተመረቋል።
  • የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን ዕድሳት ተጠናቆ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ተባረከ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ ወደ ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ተጓዘ።
  • አሐዱ ባንክ ላደረገው ሁለተናዊ እገዛ በቋሚ ሲኖዶስ የእውቅናና የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበረከተለት።
  • የመቱ ፈለገ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ የመጀመሪያውን ዙር እጩ መምህራን በደማቅ ሥነ ሥርዓት አስመረቀ

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የሰኔ ማርያም በዓለ ንግሥ ቅዱስ ፓትርያርክ በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በታላቅ ድምቀት ተከበረ። Link to: የሰኔ ማርያም በዓለ ንግሥ ቅዱስ ፓትርያርክ በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በታላቅ ድምቀት ተከበረ። የሰኔ ማርያም በዓለ ንግሥ ቅዱስ ፓትርያርክ በተገኙበት... Link to: በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ የልዑካን ቡድን ሐምሌ ፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም ወደትግራይ ርዕሰ ከተማ መቐለ ይጓዛል። Link to: በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ የልዑካን ቡድን ሐምሌ ፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም ወደትግራይ ርዕሰ ከተማ መቐለ ይጓዛል። በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ የልዑካን ቡድን...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top