የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

“ደን(ዕጽዋት )ለምድራችን የደም ሥርና ልብሷ ነው።ስለሆነም ምድራችን ስሯ ተቆርጦ ሕይወቷን እንዳታጣ የመጠቅና የመንከባከብ ኃላፊነት የሰው ልጆች በመሆኑ ደኖቻችንን በመንከባከብ ኃላፊነታችንን እንወጣ።”

November 10, 2023

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ባዘጋጀው የቤተክርስቲያን ደን ልማት ኮንፈረንስ ላይ ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰደ።

የቅዱስ ፓትርያርኩ መልዕክት ሙሉ ቃል
እንደሚከተለው ይነበባል፦

መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
•ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
•ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
•ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀጳጳስ፤
•ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ወኤጲስ ቆጶሳት፤
•የተከበራችሁ የኃይማኖት መሪዎች፤
•የተከበራችሁ የመንግስት ኃላፊዎች፤
•የተከበራችሁ አምባሳደሮች፤
•የተከበራችሁ የሲቪል ማህበራት አመራሮች፤
•የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች፤
•ክቡራንና ክቡራት፤
እንኳን ደህና መጣችሁ፤
“ወነሥአ እግዚአብሔር ለእጓለ እመሕያው ወሤሞ ውስተ ገነት ከመ ይትገበራ ወይዕቀባ፡-እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ወስዶ ያበጃትም፤ ይጠብቃትም ዘንድ በኤዶም ገነት አኖረው” (ዘፍ 2፡15)
ከዚህ ጥቅስ እንደምናስተውለው እግዚአብሔር አምላካችን በማይመረመር ጥበቡ ከምድር በላይ ከሰማይ በታች የሚገኙትን ፍጥረታት አስቀድሞ ፈጥሮ የሥነ ፍጥረት መደምደሚያ (ጉልላት) የሆነው ሰው ይገለገልባቸው ዘንድ ፈቃዱን ገልጦለታል፡፡ በተለይም ደግሞ በኤዶም ገነት የነበሩትን ዕፀዋት የመጠበቅና የመንከባከብ ሓላፊነትን ሰጥቶታል፡፡

ቅድስት ቤተክርስቲያንም ይህን አምላካዊ አደራ ተገንዝባ ለዘመናት በዙሪያዋ አገር በቀል ዕፅዋትን እየተከለች በመንገድ የደከሙ የሚያርፉበት ጥላ፤ ለተራቡት ምግበ ሥጋ፤ መኖሪያ የሌላቸው የሚያድሩበት መጠለያ ይሆኑ ዘንድ ጠብቃና አስጠብቃ ቆይታለች፡፡

ለአብነትም ያህልም በሀገራችን ረጅም ዘመናትን ያስቆጠሩና ለአካባቢ አየር ጥበቃ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸው አገር በቀል ደኖች የሚገኙት በቤተክርስቲያን ቅጽር ግቢ ውስጥ ነው፡፡
እነዚህ ደኖች ቅዱሳን ባሕታውያን የሚጸልዩባቸው ብቻ ሳይሆኑ በየዘራቸው፣ በየዓይነታቸው፣ በየወገናቸው፣ በየመልካቸው፣ እግዚአብሔር የፈጠራቸው ስፍር ቁጥር የሌላቸው እንስሳትና አራዊትም ደኑን ዓለማቸው አድርገው የሚኖሩበትና የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ የሚገለጽበት ነው ደን ማለት፡፡

ዓለመ ደን ጥቅሙ ለሰብአዊ ፍጡር ብቻ አይደለም ለፍጥረቱ ሁሉ ነው እንጂ፡፡

ከጥንት ጀምሮ ቤተክርስቲያን በረሃማነትን ለመቀነስ በደን ጥበቃ በኩል ያበረከተችው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ቢሆንም በአለንበት ዘመን ከሕዝብ ቁጥር መጨመር እና ከልዩ ልዩ ምክንያቶች ጋር ተያይዞ የደን መመናመን ይታያል፡፡

ስለሆነም እግዚአብሔር አምላክ ለሕይወታችን እንደሚያስፈልገን አውቆ አስቀድሞ ፈጥሮ አዘጋጅቶ የሰጠንን ሀብት እንዳናጣ መንከባከብና ባረጁት ዕፅዋትም ምትክ አዳዲስ ችግኞችን መትከል ይገባናል፡፡ ይህን ስናደርግ ምድራዊ ሕይወታችን የተስተካከለና የተደላደለ ይሆናል፡፡

በአንጻሩ ዕፅዋትን በአግባቡ ካልተንከባከብን አፈራችን በጎርፍ ተጠራርጎ፣ በአውሎ ነፋስ ተሸርሽሮ የምድሪቱን ልምላሜ የምናጣ ከመሆኑም ባሻገር ፀሐይና ድርቅ ይበረታል፤ የአካባቢያችን አየር ይለወጣል፤ ድርቅ እና ረሃብ ይበዛል፤ ሕያዋን ፍጥረታት በሙሉ ለከፋ ችግር ይጋለጣሉ፡፡

በመሆኑም እግዚአብሔር እንድንጠቀምባቸው የሰጠንን ዕፅዋት የመጠበቅና የመንከባከብ ሓላፊነታችንን በአግባቡ እንድንወጣ ለመወያየት እንዲሁም አለም አቀፋዊ ተሞክሮዎችን ለመቅሰም ይቻል ዘንድ ይህ መርሐ ግብር እንዲዘጋጅ ለደከሙ አካላት ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

በዚህ አጋጣሚ የዚህ ጉባኤ ተሳታፊዎች የሆናችሁ በሙሉ ሰላም የሰፈነባት፣ ልምላሜ የሞላበት፣ የጥይት ድምጽ የማይሰማባት፣ ሰው በሰውነቱ ብቻ ተከብሮ በነፃነት የሚኖርባት ሀገርን ለትውልድ የማስተላለፍ የታሪክ አደራ የሚጠብቃችሁ መሆኑን በማስታወስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን አስተባባሪነት የተዘጋጀው የቤተክርስቲያን ደን ልማት ኮንፈረንስ በዛሬው ዕለት በይፋ መከፈቱን በእግዚአብሔር ስም እናበስራለን፡፡

እግዚአብሔር የተባረከና የተቀደሰ ጉባኤ ያድርግልን!
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!

አባ ማትያስ
ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት
ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ
ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ጥቅምት 29 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ “ሐዋርያዊ ተልእኳችን ለዘመናችን “በሚል ርእስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣በሰሜን አሜሪካ የኒዎርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ከጠቅላዮ ቤተ ክህነት ጀምሮ እስከ ክፍላተ ከተማ ለተውጣጡ የወንጌል መምህራን የአንድ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጠ። Link to: በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ “ሐዋርያዊ ተልእኳችን ለዘመናችን “በሚል ርእስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣በሰሜን አሜሪካ የኒዎርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ከጠቅላዮ ቤተ ክህነት ጀምሮ እስከ ክፍላተ ከተማ ለተውጣጡ የወንጌል መምህራን የአንድ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጠ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን... Link to: ለሦስት ቀናት የቆየው የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት 22ኛው መደበኛ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በሰላም ተጠናቀቀ። Link to: ለሦስት ቀናት የቆየው የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት 22ኛው መደበኛ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በሰላም ተጠናቀቀ። ለሦስት ቀናት የቆየው የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top