የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የአመራር ብቃትን ለማሳደግና ዘመኑን የዋጀ የአሰራር ሥርዓትን ለመዘርጋት የሚያስችል የምክክር ጉባኤ በጠቅላይ ቤተክህነት በመካሔድ ላይ ነው።

March 19, 2024

መጋቢት ፲ቀን፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
“”””””””””””””””””””””””””””
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
=============

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ መዋቅራዊ አደረጃጀቶችን ተከትሎ የአመራር ብቃትን ለማሳደግና ዘመኑን የዋጀ የአሠራር ሥርአትን በመገምባት በሁሉም ዘርፍ የተገነባች ቤተ ክርስቲያንን ለትውልድ ማስተላለፍን ዓላማው ያደረገ የሁለት ቀናት የምክክር ጉባኤ በመካሔድ ላይ ነው።

በምክክር ጉባኤው ላይ የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች፣የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ ፣የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ፣የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ ዋና ክፍል ኃላፊዎች፣የጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያውና የየድርጅቶቹ ኃላፊዎች፣ምክትል ኃላፊዎችና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰባቱ ክፍላተ ከተሞች ሥራ አስኪያጆች ይሳተፋሉ።

በዚሁ ጊዜ ሕግን ጠብቆ አለመስራት የሚያስከትለው ተጠያቂነት በሚል ርዕስ፣የዐሥር ዓመቱ ዕቅድ አተገባበር በሚል ርዕስ፣የዕቅድ አዘገጃጀትና አቀራረብ በሚል ርዕስ፣የሪፖርት አቀራረብ በሚል ርዕስ፣ስለ መረጃ አደረጃጀትና አያያዝ በሚል ርዕስ፣የስብከተ ወንጌል አገልግሎት አሰጣጥና ተደራሽነት በሚል ርዕስ፣ስለ ፐርሰንት አከፋፈል ከቃለ ዐዋዲው መመሪያ አኳያ በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሑፎች የሚቀርቡ ሲሆን ጸሑፎቹም በዘርፉ ከፍተኛ እውቀትና የትምህርት ዝግጅት ባላቸው ባለሙያዎች የሚሰጥ ይሆናል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሥልጠናው መክፈቻ መርሐ ግብር ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት የቤተክርስቲያንን ሁለንተናዊ የሥራ ሒደትን በማዘመን ቀልጣፋ ሥራ መስራት ይቻል ዘንድ በዚህ የምክክር መድረክ ላይ የተገኛችሁ ሁሉ እንኳን በሰላም መጣችሁ ካሉ በኋላ የምክክር ጉባኤው የተሳካና ውጤታማ መሆን እንዲችል ጸሎታችን ነው ብለዋል።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የባህርዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዚሁ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር የምክክር ጉባኤውን አስፈላጊነት በተመለከተ ሠፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።በዚህ ማብራሪያም ቀደምት አባቶችን ዘመኑ በፈቀደላቸው ሁኔታ በርካታ መሰናክሎችን አልፈው ለቤተክርስቲያን ሁሉን አቀፍ እድገት መንፈሳዊና አስተዳደራዊ ተጋድሎን በሚገባ ተጋድለው ለዚህ ትውልድ አስረክበዋታል። ብለዋል።

አያይዘውም ይህ ትውልድ ከቀደምት አባቶቹ የተረከባትን ቤተክርስቲያን በሚገባ ጠብቆ፣አስጠብቆና አስከብሯታል ወይስ ቤተክርስቲያንን ከመሪነት ሚናዋ አዋርዶ ወደ ታች ጥሏታል? ያሉት ብፁዕነታቸው ቤተክርስቲያናችን አሁን ካለችበት ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር በመመዘንም አሰራራችንን በማዘመንና ዘመኑን የሚዋጅ በማድረግ የቤተክርስቲያንን ተልዕኮ ለማሳካት መስራት ይኖርብናል ብለዋል።

ቤተክርስቲያን በርካታ ፈተናዎች ገጥመዋታል ፈተናዎቹ ግን አላንበረከኳትም ካሉ በኋላ ለፈተና የማይንበረከክ፣ለተፈጠሩ ችግሮች መፍትሔ የሚሰጥና የቤተክርስቲያንን አሰራር በማዘመን ለውጥ የሚያመጣ አመራር ስለሚያስፈልግ ይህ የምክክር ጉባኤ ሊዘጋጅ ችሏል በማለት የጉባኤውን መከፈት አብስረዋል።

ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ እና ከብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ቀደም ብሎም ሊቀ መዘምራን ሀረገወይን ጫኔ የምክክር ጉባኤውን አስፈላጊነት፣ለምክክር ጉባኤው መዘጋጀት ምክንያት የሆኑ መነሻ ሀሳቦችን በመጥቀስ መልዕክት አስተላልፈዋል።የምክክር ጉባኤው ለሦስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በቀረቡ ጥናታዊ ጽሑፎች ዙሪያ ውይይት ይደረግባቸዋል።በመጨረሻም ጉባኤው የአቋም መግለጫ በማውጣት የምክክር መድረኩ ማጠቃለያ ይሆናል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ቅድስት ቤተክርስቲያናችን በብሔራዊ ምክክር መድረክ ተሳታፊ እንድትሆንና በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ውስጥ ተገቢው ክብርና እውቅና እንዲሰጣት በቋሚ ሲኖዶስ በኩል ጥረት እንዲደረግ የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ አሳሰበ። Link to: ቅድስት ቤተክርስቲያናችን በብሔራዊ ምክክር መድረክ ተሳታፊ እንድትሆንና በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ውስጥ ተገቢው ክብርና እውቅና እንዲሰጣት በቋሚ ሲኖዶስ በኩል ጥረት እንዲደረግ የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ አሳሰበ። ቅድስት ቤተክርስቲያናችን በብሔራዊ ምክክር መድረክ... Link to: ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በአሮጌው ቄራና በጠቅላይ ቤተክህነት  በግንባታ ላይ የሚገኙትን ሕንጻዎች የሥራ አፈጻጸም ተዘዋውረው ተመለከቱ። Link to: ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በአሮጌው ቄራና በጠቅላይ ቤተክህነት  በግንባታ ላይ የሚገኙትን ሕንጻዎች የሥራ አፈጻጸም ተዘዋውረው ተመለከቱ። ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በአሮጌው ቄራና በጠቅላይ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top