የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አዘጋጅነት ‹‹ኦርቶዶክሳዊ ብዙኃን መገናኛ ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን›› በሚል መሪ ቃል በተደረገው የሥልጠና፣ ውይይትና የምክክር መርሐ-ግብር በተሳተፍን የቤተ ክርስቲያን ልጆች የቀረበ የአቋም መግለጫ፤

April 16, 2024

* በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት
* ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ ባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
* ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት
እኛ በማኅበራዊ ሚዲያ በተለያየ መንገድ አሳባችንን በመግለጽና አዎንታዊ መረጃዎችን በመስጠት የእናታችን የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መንፈሳዊ አገልግሎት ለማገዝ የምንሠራ የቤተክርስቲያናችን ልጆች ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ያቀረበችልንን ጥሪ በመቀበልና ሚያዝያ 5 እና 6 ቀን 2016 ዓ/ም ‹‹ኦርቶዶክሳውያን ብዙኀን መገናኛ ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን›› በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀችልንን የሥልጠና፣ የምክክርና የውይይት መርሐ-ግብር በመሳተፋችን እጅግ ታላቅ ደስታ ተሰምቶናል፡፡

በሥልጠናው ላይ የጥናት ጽሑፎችን በማቅረብ ግንዛቤን የሰጡን የቤተ ክርስቲናችን ምሁራንም ያቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ ማኅበራዊ ሚዲያን በተመለከተ በቂ ግንዛቤን የሰጠን ከመሆኑም በላይ ቤተ ክርስቲያናችን እንዲህ ያሉ ምሁራን ያሏት መሆኑን አስገንዝቦናል፡፡

ያለንበት ወቅት ቤተ ክርስቲያናችን በተለያዩ ውስጣዊም ሆነ ውጪያዊ ፈተናዎች የተወጠረችበት ከመሆኑም ባሻገር እነዚህ ፈተናዎች ግዘፍ ከሚነሱባቸው መስኮች አንዱ የማኅበራዊ ሚዲያው ዘርፍ መሆኑን ተረድተናል፡፡

እናት ቤተክርስቲያናችን በዚህ መንገድ እየተፈተነች መሆኑን የተገነዘበው የቤተክርስቲያናችን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ‹‹የሀገሩን ሰርዶ በሀገሩ በሬ›› እንደሚባለው በማኅበራዊ ሚዲያ በኩል የሚከሰቱ ፈተናዎችን መከላከል የሚቻለው በዘርፉ ባሉ የቤተክርስቲያን ልጆች መሆኑን ተገንዝቦ ከቤተክርስቲያናችን ጎን ቆመን ፈተናዎችን በጋራ መከላከል እንድንችል የተደረገልንን የልጅነት ጥሪ በደስታ ተቀብለናል፡፡

ስለሆነም ለሁለት ቀናት የተሰጠንን ሥልጠና መነሻ በማድረግ ባከናወንነው የቡድን ውይይት የሚከተሉትን የአክብሮት የልጅነት ጥያቄ የቤተክርስቲያናችን ርእሰ አበው በሆኑት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት እና በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፊት በማቅረብ የቤተክርስቲያናችንን መንፈሳዊ፣ አስተዳደራዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ለማገዝ በልጅነት የሚቻለንን ሁሉ ለማድረግ እንደሚከተለው ቃል እንገባለን፡፡

እኛ በማኅበራዊ ሚዲያ የቤተክርስቲያንን መልካም ገጽታ ለመገንባትና ጎጂ ተግባራት የሚወገዱበትን መረጃ ለማኅበረሰብ የምናደርስ የቤተክርስቲያን ልጆች፡-
1- በተደረገው የሥልጠና፣ የውይይትና የምክክር መርሐ-ግብር ደስተኞች በመሆናችን የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር ጠብቀን ከቤተ ክርስቲያናችን የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ጋር በጋራ ለመሥራት የምንችልበት አስፈላጊው መደላድል እንዲፈጠርልን በልጅነት እንጠይቃለን፡፡
2- ቤተ ክርስቲያናችን ለማኅበረሰብም ሆነ ለምእመናን አስፈላጊውን መረጃ በወቅቱ ማድረስ የምትችልበትን አሠራር እንድታጠናክር እንጠይቃለን፡፡

3- በቤተ ክርስቲያን ስም የሚወጡ የሐሰት ዜናዎችን እየተከታተለ የሚያጋልጥ አሠራር እንዲዘረጋ እንጠይቃለን፡፡

4- የቤተ ክርስቲያን ልጆች በሚዲያ አምባሳደርነት ተካተው ቤተ ክርስቲያናችንን በማኅበራዊ ሚዲያው ዘርፍ እንዲያግዙ የሚያደርግ አሠራር እንዲዘረጋ እንጠይቃለን፡፡

5- የቤተ ክርስቲያን ልጆች እንደሆኑ በሚገልጹ የማኅበራዊ ሚዲያ አንቂዎች የሐሰት አስተምህሮ እንዲሁም በተለያዩ ክብረ በዓላት ላይ የቀጥታ ሥርጭት የሚያስተላልፉ አካላት ከቤተ ክርስቲያናችን ቀኖና እና ነባር ባሕለ-ሃይማኖት ጋር የሚጋጩ ተግባራትን እየፈጸሙ በመሆናቸው ምክንያት የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አጠባበቅ ላይ ከፍተኛ ክፍተቶች እየተፈጠሩ በመሆኑ ሚዲያን የተመለከተ ጠንካራ ሕግ እንዲወጣ እንጠይቃለን፡፡

6- በማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማችን ላይ ክፍተቶች እየተፈጠረ ያለው ከግንዛቤ ማነስ በመሆኑ እንዲህ ያሉ የሥልጠና፣ የውይይትና የምክክር መድረኮች ተደጋግመው ይዘጋጁልን ዘንድ እንጠይቃለን፡፡ ወደፊት በሚዘጋጁ ተመሳሳይ መርሐ-ግብሮች ላይም ከእኛ ጋር በንቃት የሚሳተፉ የቤተ ክርስቲያን ልጆችን ለእናት ቤተ ክርስቲያናችን ድምጽ ይሆኑ ዘንድ ወደ መርሐ-ግብሩ ለመጋበዝ ቃል እንገባለን፡፡

7- ከግል ዝንባሌ፣ ከወገንተኝነት፣ ከጥቅመኝነት፣ ከዘርና ከዝምድና አስተሳሰብ ነጻ በሆነ መንገድ ቤተ ክርስቲያናችንን በዘርፉ ለማገልገል ቃል እንገባለን፡፡

8- የሚዲያ የሥነ-ምግባር ሕግጋትንና ክብረ ክህነትን ባከበረ መንገድ መረጃዎቻችንን ለማስተላለፍ ቃል እንገባለን፡፡

9- የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች መሆናችንን የሚገልጹ አርአያዎችን በመያዝና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን በመረጃ ምንጭነት በመጠቀም መረጃዎቻችንን ለማስተላለፍ ቃል እንገባለን፡፡

10- የቤተ ክርስቲያናችንን አበው፣ ሊቃውንትና ንዋየ ቅድሳት በምንጠራበት ወቅት ቤተ ክርስቲያናችን የምትጠቀምባቸውን ቀኖናዊ ሥያሜዎች ብቻ በመጠቀም ለመጥራት ቃል እንገባለን፡፡

ይህንንም የገባነውን ቃል ለመጠበቅ እንድንችል የብፁዕ ወቅዱስ አባታችን እና የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት አባቶቻችን ጸሎት ትርዳን፡፡
ሚያዝያ 7 ቀን 2016 ዓ/ም
አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ኦርቶዶክሳውያን ብዙኃን መገናኛ ተቋማትና ማኅበራዊ ሚዲያዎች ሐሰተኛ ወሬ ባለመቀበል እና ባለማስተላለፍ ኃላፊነታቸውን ሊውጡ እንደሚገባ ብፁዕ አቡነ አብርሃም አሳሰቡ። Link to: ኦርቶዶክሳውያን ብዙኃን መገናኛ ተቋማትና ማኅበራዊ ሚዲያዎች ሐሰተኛ ወሬ ባለመቀበል እና ባለማስተላለፍ ኃላፊነታቸውን ሊውጡ እንደሚገባ ብፁዕ አቡነ አብርሃም አሳሰቡ። ኦርቶዶክሳውያን ብዙኃን መገናኛ ተቋማትና ማኅበራዊ... Link to: “ንጹሕ ምንጭ ኢትዮጵያ ልዩ ታሪካዊ ዐውደ ርእይ” በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፣ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያዊ ጉብኝትና ቡራኬ ተጠናቀቀ። Link to: “ንጹሕ ምንጭ ኢትዮጵያ ልዩ ታሪካዊ ዐውደ ርእይ” በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፣ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያዊ ጉብኝትና ቡራኬ ተጠናቀቀ። “ንጹሕ ምንጭ ኢትዮጵያ ልዩ ታሪካዊ ዐውደ ርእይ”...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top