የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የመልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል በዓለ ንግሥ በዲላ ዋለሜ ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን በድምቀት ተከበረ

September 8, 2024

ጳጉሜ 3/2016 ዓ.ም

“ሩፋኤል ግሩም በመንፈስ ቅዱስ ኅቱም
መዓዛ ቅዳሴከ ጥዑም ከመ ጽጌ ገዳም
ነዓ ነዓ ማዕከሌነ ቁም
በበዓልከ ባርከነ ዮም።

ዚቅ ዘበዓለ ሩፋኤል ዘወርሐ ጳጉሜን

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በመንበረ ጵጵስና ወናጎ ወረዳ ቤተክህነት ሥር በምትገኘው በዲላ ዋለሜ ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን የመልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል በዓለ ንግሥ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራአስኪያጅ መልአከ ሕይወት ቀሲስ ብርሃኑ ክፍሌ የሀገረ ስብከቱ የሥራ ክፍል ኃላፊዎች የወረዳ ቤተክህነት ዋና ሥራአስኪያጅ ሊቀጠበብት መሠረት ይልማ የአድባራት አስተዳዳሪዎች የዲላ ምዕመናን በተገኘበት በታላቅ ድምቀት ተከብሯል።

የሀገረ ስብከቱ ዋና ሕዝብ ግንኙነት ክፍል እንደገለጹት መርሐ ግብሩን መልአከ ኃይል ቀሲስ ጌታሁን ገሠሠ የሀገረ ስብከቱ የቁጥጥር፣ የእቅድና ልማት ክፍል ኃላፊ የመሩት ሲሆን የደብሩ ሰንበት ት/ቤት ያሬዳዊ ወረብ አቅርበዋል ብለዋል። የዕለቱን የወንጌል ትምህርት ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ሀብታሙ አበበ የሀገረ ስብከቱ ስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ ‹‹ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ›› (ጦቢት ፲፪፥፲፭)፡፡ በሚል ርዕስ ስለ ቅዱስ ሩፋኤል ክብር ጥበቃና አማላጅነት ከቅዱሳት መጻሕፍት በመጥቀስ በሰፊው አስተምረዋል።

የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራአስኪያጅ መልአከ ሕይወት ቀሲስ ብርሃኑ ክፍሌ ቅዳሴውን በመቀደስ እና ቃለ ምዕዳን ያስተላለፉ ሲሆን የእግዚአብሔር መላእክት ያለቸውን ክብር በመዝ 33:7 ያለውን በመግለጽ ምዕመናን ችግራቸውን ሁሉ ለቅዱስ ሩፋኤል ቢነግሩ መፍትሔ የሚገኙ መሆኑን ገልጸዋል። እንዲሁም አዲሱን ዓመት ለመቀበል ሁሉም ክፋትን ምቀኝነት መጥፎ ሁሉን ነገር ማሻገር እንደሌለበት ንሰሐ መግባት እንደሚያስፈልግ አስተምረዋል። በመጨረሻም ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ተሰጥቶ የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል ብለዋል ።

መረጃው የሀገረ ስብከቱ ህዝብ ግንኙነት ነው።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • የድሬዳዋ ሳባ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ያስገኘባው ባለ ሦስት ወለል ሁለገብ ሕንጻ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጸሎተ ቡራኬ በዛሬው ዕለት ተመረቋል።
  • የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን ዕድሳት ተጠናቆ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ተባረከ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ ወደ ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ተጓዘ።
  • አሐዱ ባንክ ላደረገው ሁለተናዊ እገዛ በቋሚ ሲኖዶስ የእውቅናና የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበረከተለት።
  • የመቱ ፈለገ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ የመጀመሪያውን ዙር እጩ መምህራን በደማቅ ሥነ ሥርዓት አስመረቀ

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: በሲዳማ ሀገረ ስብከት በሀዋሳ ከተማና ዙሪያ ወረዳ በሀዋሳ ከተማ በደብረ ታቦር ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሩፋኤል በዓለ ንግሥ በታላቅ ድምቀት ተከበረ። Link to: በሲዳማ ሀገረ ስብከት በሀዋሳ ከተማና ዙሪያ ወረዳ በሀዋሳ ከተማ በደብረ ታቦር ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሩፋኤል በዓለ ንግሥ በታላቅ ድምቀት ተከበረ። በሲዳማ ሀገረ ስብከት በሀዋሳ ከተማና ዙሪያ ወረዳ... Link to: ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት መካከል አንዱ የሆነው ቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት በርዕሰ አድባራት ወገዳማት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል በድምቀት ተከበረ። Link to: ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት መካከል አንዱ የሆነው ቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት በርዕሰ አድባራት ወገዳማት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል በድምቀት ተከበረ። ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት መካከል አንዱ የሆነው ቅዱስ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top