የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ አዲሱን ዓመት አስመልክቶ ለመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው ያስተላለፉት አባታዊ መልእክት።

September 10, 2024

ጳጉሜን 4/2016 ዓ/ም
===============
እንኳን ከዘመነ ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ቅዱስ ማቴዎስ በሰላምና በጤና አሻገረን አሻገራችሁ። “ወይቤሎ ኅድጋ እግዚኦ ሐሪፈኒ’ “በዚች ዓመት ደግሞ ተዋት” ሉቃ 13፥8

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምሳሌ ባስተማረው በዚህ ትምህርት ውስጥ የአትክልቱ ባለቤት፡ በወይኑ አትክልት ቦታ የተተከለች በለስና የአትክልቱ ሠራተኛ ይገኛሉ። የበለሷ ባለቤት በለስ መትከሉና የሚንከባከብ ሠራተኛ የመቅጠሩ መሠረታዊ ዓላማ ከበለሷ ፍሬ ለማግኘት ነው። ነገር ግን የአትክልቱ ባለቤት በለሷ ፍሬ መስጠት በሚገባት ወቅት ጠብቆ ቢመጣም ፍሬ ማግኘት አልቻለም። የአትክልት ሠራተኛውን እነሆ ከዚች በለስ ፍሬ ልፈልግ ሦስት ዓመት እየመጣሁ ምንም አላገኘሁም ቁረጣት፣ ስለምን ደግሞ መሬቱን ታጎሳቁላለች? አለው። ጠባቂዋም ‘ጌታ ሆይ ፍሬ እንድታፈራ አስፈላጊውን እስካደርግላት ድረስ በዚች ዓመት ደግሞ ተዋት በማለት ልመናን አቀረበ።

የበለሷ ባለቤት በለስ ተክሎ ፍሬ እንደፈለገ ሁሉ እኛንም ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር ሲፈጥረን ፍሬ እንድናፈራ እንጂ ፍሬ አልባ በለሶች እንድንሆን አይደለም። ፍሬ ማፍራት ካልቻልን ደግሞ እጣ ፋንታችን መቆረጥ ይሆናል፡፡ ስለዚህ የንስሓ፣ የፍቅር፡ የይቅርታ የበጎ ምግባር ፍሬ እንድናፈራ ይፈልጋል። የአትክልቱ ሠራተኞች በዚች ዓመት ተዋት ብለው እንደለመኑ ዛሬም እኛ ከዓመት ወደ ዓመት መሻገራችን በጎ ፍሬ ስለ ተገኘብን ሳይሆን ፍሬ እንድናፈራ አቤቱ የዘንድሮን ተዋት በማለት በሚማልዱልን በቅዱሳን መላእክት ምክንያት መሆኑን ማስተዋል ይገባናል። ፍሬ ሳታፈራ ለምን ምድርን ታጎሳቁላለች እንደ ተባለችው በለስ እኛም እንንከባከባት ዘንድ የተሰጠችንን ምድር በክፋት፡ በጥላቻ፡ ፍቅርን ትተን ጠብን በመዝራት እርስ በርእስ በመጠፋፋት ለሰው ልጆች የመከራና የሰቆቃ ስፍራ አድርገናታል፡፡ ክቡር የሰው ልጅ ደም በራሱ በሰው ልጅ ጭካኔ በከንቱ እየፈሰሰ ይገኛል፡፡ ፍሬ ባያገኝብንም እግዚአብሔር ቸር በመሆኑ በቅዱሳን ጸሎት ከዘመነ ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ቅዱስ ማቴዎስ እንድንሻገር ፈቀደልን። በመሆኑም ይህ ዘመን የተጨመረልን ለንስሐ የሚገባ ፍሬን እናፈራ ዘንድ መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ከዘመን ወደ ዘመን መሻገር በሰዎች ጥበብ የማይገኝ ከእግዚአብሔር ብቻ የሚሆን ትልቅ ስጦታ ነው። እግዚአብሔር ደግሞ በጊዜ ላይ ጊዜ በእድሜ ላይ እድሜ የጨመረልን ካለፈው ዘመን ተምረን የሚቀጥለውን በማረም ፍሬአማ ሕይወትን መኖር እንድንችል ነው፡፡ በአዲሱ ዘመን ሰላምና ፍቅርን በሀገራችን ለማጽናት የበኩላችንን ማበርከት ከእያንዳንዳችን ይጠበቃል፡፡ ስለዚህ በ2017 ዓመተ ምሕረት በዘመነ ቅዱስ ማቴዎስ ጥላቻን አርቀን ፍቅርን፣ ክፋትን ትተን ደግነትን፡ መገፋፋትን አስወግደን መረዳዳትን፡ ከኃጢአት ርቀን ጽድቅን የምንሠራበት፣ ጦርነት ከሀገራችን ተወግዶ በሰላም ወጥተን በሰላም የምንገባበት፡ መለያየታችን ወደ አንድነት የሚመጣበት ዘመን እንዲሆን በጸሎት ትተጉ ዘንድ አደራ ጭምር አሳስባችኋለሁ፡፡

የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ዘመነ ቅዱስ ማቴዎስን የሰላምና የበረከት ያድርግልን፡፡ አሜን

መልእክተ ሕይወት ኢየሱስ ክርስቶስ ሀገራችንንና ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን!!!
አባ ዮሴፍ
የሲዳማ ሀገረ ስብከት እና የሀዋሳ ታቦር ፍኖተ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/abune-yosef-cover.jpg 412 400 tc https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg tc2024-09-10 19:20:372024-09-10 19:22:23ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ አዲሱን ዓመት አስመልክቶ ለመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው ያስተላለፉት አባታዊ መልእክት።
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት እንዲሁም በመላው ዓለም የምትገኙ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምዕመናን ወምዕመናት እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም አደረሳችሁ አሸጋገራችሁ Link to: በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት እንዲሁም በመላው ዓለም የምትገኙ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምዕመናን ወምዕመናት እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም አደረሳችሁ አሸጋገራችሁ በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት እንዲሁም በመላው... Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተዳደር ጉባኤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰጠውን መግለጫ መነነሻ በማድረግ በጉዳዩ ላይ ተወያይቶ ልዩልዩ ውሳኔዎችን አስተላለፈ Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተዳደር ጉባኤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰጠውን መግለጫ መነነሻ በማድረግ በጉዳዩ ላይ ተወያይቶ ልዩልዩ ውሳኔዎችን አስተላለፈ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top