የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የዘመን መለወጫን በዓል አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ።

September 10, 2024

ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የዘመን መለወጫን በዓል አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ።

የብፁዕነታቸውን ሙሉ መልእክት እነሆ!!!
* * * * *

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

“ምድር ሠናይት እንተ ዘልፈ ይሔውጻ እግዚአብሔር አምላክከ ፤ ወአዕይንቲሁ ለእግዚአብሔር አምላክከ ላዕሌሃ እምርእሰ ዓመት እስከ ማኅለቅተ ዓመት ”

“አምላክህ እግዚአብሔር የሚጎበኛት አገር ናት ፤ ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ የእግዚአብሔር ዓይን ሁልጊዜ በርሷ ላይ ነው”ዘዳ ፲፩ ÷ ፲፪

የተወደዳችሁ እና የተከበራችሁ በቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያ በመላው ዓለምም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ የዘመናት ባለቤት እግዚአብሔር 2016 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን በሰላም እና በጤና አስፈጽሞ እንኳን ለ2017 ዓም ዘመነ ማቴዎስ በሰላም እና በጤና አደረሰን! አደረሳችሁ!!!

የዘመናት ባለቤት እግዚአብሔር ዘመንን በዘመን እየለወጠ ዓለም ከተፈጠረ ዘመን ከተቆጠረ 5500 ዓመተ ኲነኔ 2017 ዓመተ ምሕረት በአጠቃላይ 7517 ዘመን ይሆናል ።

እስራኤል ዘሥጋ በግብፅ ባርነት በነበሩበት ዘመን ተወልዶ በፈርኦን ቤት የፈርኦን ልጅ መባልን በእምነት እንቢ በማለት ያደገው ክቡደ መዝራዕት ሙሴ ከ4 መቶ 30 የግብፅ ባርነት ዘመን በኋላ እስራኤላውያንን ነጻ ለማውጣት በግብፅ እና በግብፃውያን ላይ ዘጠኝ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አሥረኛ ሞተ በኲርን አሥራ አደኛ ስጥመትን ፈጽሞ በርሱ መሪነት በመልአኩ ተራዳኢነት በእግዚአብሔር አሻጋሪነት ቀይ ባሕር ተከፍሎላቸው በደረቅ አልፈው ከሞት ወደሕይወት ከባርነት ወደነጻነት ከውርደት ወደ ክብር ተሸጋግረዋል ።

በመሆኑም የእግዚአብሔር ሰው ሙሴ በጸናች የእግዚአብሔር እጅ እስራኤል ዘሥጋን ከግብፅ የባርነት ሕይወት ነጻ አውጥቶ ሊወርሷት ወደአለችው የአባቶቻቸው ርስት የተስፋይቱ ምድር ከነአን ለመግባት በሞአብ ሜዳ ላይ በጉዞ ለነበሩት ለእስራል አዲሱ ትውልድ የምትወርሷት የበረከት ምድር ከነዓን ዝናብ እንደማይዘንብባት እንደ ግብፅ ምድር አይደለችም።

የቃል ኪዳን ምድር ከነዓን የዘሩባትን የምታበቅል የተከሉባትን የምታጸድቅ እግዚአብሔር የሚጎበኛት የእግዚአብሔር ዓይን በረድኤት የማይለያት መሆኑን በመግለጽ በውስጧ በሰላም ለመኖር የባርነት ቀንበራቸውን ሰብሮ መና ከሰማይ አውርዶ እየመገበ ውኃ ከዓለት ላይ አፍልቆ እያጠጣ ያሻገራቸውን የእግዚአብሔርን ሕግ እና ሥርዓት ጠብቀው እንዲኖሩ በአጽንኦት ሲመክራቸው እናስተውላለን።

የተወደዳችሁና የተከበራችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን አባቶቻችን በአጥንታቸው እና በደማቸው አጽንተው ያስረከቡን ቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያ ስሟ በመጽሐፍ ቅዱስ ተደጋግሞ የተወሳ ልክ እንደተስፋይቱ ምድር ከነዓን 3 መቶ 65 ቀናት ስመ እግዚአብሔር የሚጠራባት ሥርዓተ አምልኮ የሚፈጸምባት እግዚአብሔር ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ በምሕረት ሀገረ እግዚአብሔር በምሕረት ዓይኑ የሚመለከታት ፣ መዝበ ታሪክ ዓይኑ የሚመለከታት ሀገረ እግዚአብሔር ፣ መዝገበ ታሪክ ፣ የቅርስ ማዕከል እና የሰው ዘር መገኛ መሆኗን እናስታወሳለን።

ይሁን እንጂ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተለየ ሁኔታ ከውስጥና ከውጪ እየደረሰ ባለው ፈርጀብዙ የተፈጥሮ እና የሰው ሠራሽ ችግር ምክንያት በአራቱም ማዕዘን በጦርነት ድምፅ እየተናጠች የፈተናና የመከራ ማዕበል እያንገላታት ትገኛለች።

በዚሁ ችግር ምክንያት የተነሳ በርካታ ወገኖቻችን መተኪያ የሌላት ውድ ሕይወታቸውን እያጡ ሲሆን ለዘመናት የደከሙበት ሀብት ንብረታቸው እየጠፋ ይገኛል።

ከቤት ቀያቸው ተፈናቅለው ለቀን ሀሩር ለሌሊት ቁር ተጋልጠዋል ፤ ሕፃናት ከትምህርት ገበታ ተለይተው የለጋነት እድሜያቸውን በከንቱ እያሳለፉት ይገኛሉ ፤ በአጠቃላይ በሀገራችን እየሆነ ያለውን ነገር ስንመለከት ችግሩ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን እንገነዘባለን።

በመሆኑም ከዘመነ ዮሐንስ ወደዘመነ ማቴዎስ ስንሸጋገር እስራኤል ዘሥጋ ከግብፅ ወደከነዓን ሲሻገሩ የግብፅን ትብት በግብፅ ቀብረው ከሞት ወደሕይወት ከባርነት ወደነጻነት እንደተሻገሩ እኛም እስራኤል ዘነፍስ ያረጀውን ሰውነት ገፍተን አዲሱን ሰውነት በመልበስ አሮጌውን የኃጢኣት ርሾ አስወግደን አዲስን የጽድቅ ርሾ ገንዘብ በማድረግ ጥላቻን አውልቀን ፍቅርን በመልበስ መለያየትን ተጸይፈን አንድነትን በመጎናጸፍ የክርስቶስ መልክ መገለጫ የሆነውን የሰውን ልጅ በሰውነቱ ብቻ በማክበር በአዲስ ልብ በአዲስ አስተሳሰብ በአዲስ መንፈስ ልንሻገር የሚገባ መሆኑን በአጽንኦት ማሳሰብ እንፈልጋለን ።

ዘመነ ክረምት አልፎ አዲሱ ዓመት ሲገባ መስከረም ሲጠባ የወንዝ ውኃዎች ይጠራሉ አበባዎች ይፈካሉ የእኛም ሕይወት በንስሓ ውኃ ሊጠራ በበጎ ነገር ሁሉ ሊፈካ በአዲሱ ዓመት አዲስ ማንነት ሊኖረን ያስፈልጋል።

በመጨረሻም የዘመን መለወጥ ለሰው ልጅ ሕይወት ትርጉሙ ከፍ ያለ በመሆኑ በሕይወታችን ተለውጠን ስለ ሀገራችን እና ስለሕዝባችን በሰላም ወጥቶ በሰላም መግባት በመጸለይ የሰላም ሰው ሆነን ለሰላም የልባችንን በር በመክፈት እጃችንን ለፍቅርና ለአንድነት በመዘርጋት በማረሚያ ቤት ፣ በሆስፒታል እና በተለያየ ችግር ውስጥ ያሉ ወገኖቻችንን በመጠየቅ ፣ ያለንን ለሌላቸው ወገኖቻችን በማካፈል በይቅርታ ልብ መጪውን አዲሱን ዓመት እንድንቀበለው በማለት መልእክታችንን እናስተላልፋለን ።

መጪው አዲሱ ዘመን ዘመነ ማቴዎስ ሞት እና ጦርነት የሚቆምበት የጥይት ጩኸት የማንሰማበት የሀገራችን ችግር የሚፈታበት የሰላም የፍቅር እና የበረከት ዘመን እንዲሆንልን መልካም ምኞታችንን በመጸለይ ጭምር እንገልጽላችኋለን ።

ቅዱስ እግዚአብሔር ሀገራችን ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!!!

አባ ቀሌምንጦስ
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/በመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ!!!

ጳጒሜን ፭ ቀን ፲፫ ወር ፳፻ ፲፮ ዓም
ሺዋ ደብረ ብርሃን ኢትዮጵያ!!!

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/abune-kelemnetos-cover.jpg 408 400 tc https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg tc2024-09-10 19:53:212024-09-10 19:53:21ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የዘመን መለወጫን በዓል አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ።
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: “ይህ ዓመት ለሕዝባችን፣ ለሀገራችንና ለዓለማችን ሰላም፣ ደስታና መንፈሳዊ እድገት እንዲያመጣ የዘወትር ምኞቴና ጸሎቴ ነው” ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ ሊቀ ጳጳስ Link to: “ይህ ዓመት ለሕዝባችን፣ ለሀገራችንና ለዓለማችን ሰላም፣ ደስታና መንፈሳዊ እድገት እንዲያመጣ የዘወትር ምኞቴና ጸሎቴ ነው” ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ ሊቀ ጳጳስ “ይህ ዓመት ለሕዝባችን፣ ለሀገራችንና ለዓለማችን... Link to: ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የደቡብ ምዕራብ ሽዋ፣ የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ኃላፊ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ! Link to: ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የደቡብ ምዕራብ ሽዋ፣ የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ኃላፊ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ! ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የደቡብ ምዕራብ ሽዋ፣ የሸገር...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top