የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የደቡብ ምዕራብ ሽዋ፣ የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ኃላፊ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት !

September 10, 2024

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የደቡብ ምዕራብ ሽዋ፣ የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ኃላፊ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት !

ወትባርክ አክሊለ አመተ ምሕረትከ፤በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ (መዝሙር 65-11)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት ካህናት ዲያቆናት የመንፈስቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት እንዲሁም መላው ኢትዮጵያውያን

እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወንጌላዊ ወደዘመነ ማቴዎስ ወንጌላዊ በሰላም እና በጤና አሸጋገራችሁ
እንኳን አደረሳችሁ

ቀን እና ሌሊትን
ሳምንታትን እና ወራትን
አመታትን እና አዝማናትን እያፈራረቀ በዕድሜያችን ላይ ዕድሜን ጨምሮ ለአዲሱ ዘመን ያደረሰን ከዘመናት በፊት የነበረ ዘመናትንም አሳልፎ የሚኖር ለህላዌው ዘመን የማይቆጠርለት ቸሩ አምላካችን መድኃኔዓለም ስለማይነገር ስጦታው እስከዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን

የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያን
እግዚአብሔር ለፍጥረታት ልዩ ልዩ ጸጋዎችን አድሏል

እግዚአብሔር ለምድር እስከዚህ ድረስ ተብሎ ሊቆጠሩ የማይችሉ አዝማናትን ሲሰጣት ለሰው ልጆች ደግሞ በአዝማናት ውስጥ የሚቆጠሩ ዕድሜያትን ይሰጣል

በእግዚአብሔር ቸርነት ምድር ዘመንን ስትቀይር የምታገኛቸው ልዩ ልዩ ጸጋዎች አሏት
በሚቀየረው ዘመን ውስጥ የምድር ገጽታ ይለዋወጣል
የደረቀው መሬት በዝናም ይርሳል
በዝናም የራሰው መሬት ቡቃያን ይይዛል
ቡቃያው ያፈራል
ቀላያት ሞልተው ይፈሳሉ
ተራሮች በአረንጓዴ ይሞላሉ
ከጊዜ በኋላ የለመለመው ሁሉ ረግፎ ምድር ወደ ባዶነት ትቀየራለች

የሰው ልጆች ዑደትም ይህን ይመስላል
እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ዕድሜን ሲሰጥ
ሰዎች በተሰጣቸው ዕድሜ በኃጢአት የደረቀ ሕይወታቸውን በቅድስና እንዲያለመልሙ
በኃጢአት ያደፈ ማንነታቸውን በንስሓ እንዲቀድሱ
ከጥላቻ ሕይወት ወጥተው በፍቅር እንዲኖሩ
ከጦርነት ወደ ሰላም እንዲመለሱ
በአጠቃላይ ህገ እግዚአብሔርን ጠብቀው የእግዚአብሔርን መንግስት እንዲወርሱ ነው

እግዚአብሔር ዘመንና ዕድሜን ለሰው ልጆች ሲሰጥ ባለፉት ዘመናት የሰራናቸውን ክፉ ሥራዎች ይቅር ብሎ ከነዚያ ክፉ ሥራዎቻችን እንድንርቅ እና በንስሐ ወደ እርሱ እንመለስ ዘንድ ነው
ለዚሁም ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በመጀመርያው መልእክቱ ምዕራፍ 4-3 ላይ
“የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል።”
ብሎ ባለፈው ዘመን ከኖርንበት የኃጢአት መንገድ እንድንመለስ ያስተምረናል

የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት
ዘመን አልፎ ዘመን ሲመጣ በደመና የጠቆረው ሰማይ ብርሃንን ይጎናጽፋል
ተራሮች ይለመልማሉ
ቆሻሻው በጎርፍ ታጥቦ ከምድር ይሠወራል
የደፈረሰው ውሀ ይጠራል
ምድር ፍሬን ትሰጣለች

የሰው ልጅ ግን ፊቱ በወንድሙ ላይ እንደጠቆረ ነው
ሰውነቱ በጽድቅ ከመለምለም ይልቅ በኃጢአት ደርቋል
ሰላምን ከመስበክ ይልቅ የጦርነት ዜና ማስተጋባትን መርጧል
ለወንድሙ መድኃኒት ከመሆን ይልቅ የወንድሙ ገዳይ ሆኗል

በእንደዚህ አይነት ሕይወት ውስጥ ሆኖ አዲስ ዘመንን መቀበል የእግዚአብሔርን ስጦታ ማቃለል ነው
ካለፈው መጥፎ ሕይወት ሳይመለሱ የዕድሜ ባለቤት መሆን በዕዳ ላይ ዕዳን መጨመር ነው

ስለዚህ ሁላችን ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያት ከሚያልፈው አሮጌ ዘመን ጋር አሮጌ አስተሳሰባችንን በመጣል አዲሱን ዘመን እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ መልካም አስተሳሰብ ልንቀበለው ይገባል

ይህን ካደረግን አምላካችን እግዚአብሔር ዘመናችንን ይባርክልናል
ምድራችን የሰላም ምድር ትሆናለች
በሰዎች መካከል ጥላቻ ጠፍቶ ፍቅር ይነግሳል
ከሁሉም በላይ በሚያልፈው ዘመንና በምታልፈው ምድር የምንሰራው መልካም ሥራ የማያልፈውን የእግዚአብሔር መንግሥት እንድንወርስ ይረዳናል

ዘመኑ የሰላም የፍቅር የአንድነት የዕርቅ የበረከት ዘመን ይሁንልን

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
መልካም አዲስ ዓመት

አባ ሳዊሮስ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የደቡብ ምዕራብ ሽዋ የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ኃላፊ

 

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/abune-sawiros-cover-1.jpg 432 400 tc https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg tc2024-09-10 19:58:152024-09-10 19:59:02ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የደቡብ ምዕራብ ሽዋ፣ የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ኃላፊ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት !
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የዘመን መለወጫን በዓል አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ። Link to: ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የዘመን መለወጫን በዓል አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ። ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ... Link to: “ካለፈው ዓመት ስህተት ወደ አዲሱ ዓመት እንዳይሸጋገር ማድረግ እና ለሁለንተናዊ ለውጥ ራስን ማዘጋጀት ይኖርብናል”። ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ Link to: “ካለፈው ዓመት ስህተት ወደ አዲሱ ዓመት እንዳይሸጋገር ማድረግ እና ለሁለንተናዊ ለውጥ ራስን ማዘጋጀት ይኖርብናል”። ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ “ካለፈው ዓመት ስህተት ወደ አዲሱ ዓመት እንዳይሸጋገር...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top