የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

በህገ ወጥ መንገድ ተሠብሮ ከአገልግሎት ውጪ የነበረው የምዕራብ ወለጋ መንበረ ጵጵስና ጥገና ተደገርጎለት በሰባቱ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ተባርኮ ዳግም አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

October 10, 2024

መስከረም 29 ቀን 2016ዓ.ም.
+ + +

የጋምቤላ ፣ የቄለም ወለጋ፣ የአሶሳ፣ የምዕራብ ወለጋ ፣ የሆሮ ጉድሩ ፣ የምስራቅ ወለጋ እና የደቡብ ሱዳን አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ የጋምቤላ ክልል እና የቤኒ ሻንጉል ክልል የሰላምና የልማት አንባሳደር ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ከሐምሌ 2016ዓ.ም. ጀምሮ ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉዞ በስድስቱ አህጉረ ስብከት ታላላቅ መንፈሳዊ ጉዞዎችን አድርገዋል።

በጉዟቸው የተዘጉ አቢያተክርቲያናትን በማስከፈት ፣ ከህግ ውጪ የነበሩ ቡድኖችን በማስተማርና ወደህግ በማስገባት ፣ ፐርሰንት የማይከፍሉ አቢያተክርስቲያናትን እንዲከፍሉ በማድረግ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን በመሥራት ቆይታ አድርገዋል። በተለይም በአራቱ ወለጋዎች በህገ ወጥ ሹመት ምክንያት ተደረጅተው የነበሩ ቡድኖችን አንዲት ሃይማኖት ፣ አንድ ሲኖዶስና አንድ ፓትርያርክ ብለው እንዲያምኑ በማድረግና በምዕራብ ወለጋ በህገ ወጥ ተሿሚዎች ክህተነት ተሰጥቷቸው የነበሩ ከ100 በላይ የሚቆጠሩ ካህናትንና ዲያቆናትን ቀኖና በመስጠት በመጨረሻም በብፁዕነታቸው ክህነት ተሰጥቷቸው ወደ አገልግሎት እንደመለሱ ተደርጓል።

በምዕራብ ወለጋ የሚገኘው መንበረ ጵጵስና በህገ ወጥ ተሿሚዎች ቁልፉ ተሰብሮ፣ መስኮትና በሮቹ ተገንጥለው የነበረ ቢሆንም ብፁዕነታቸው ወደ ሀገረ ስብከቱ ከገቡ በኋላ እድሳት ተደርጎለት እና ተባርኮ ደግም አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። ብፁዕነታቸው ወደ ሀገረ ስብከቱ ሲገቡ ከጊንቢ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ የምትገቸው የዩብዶ ወረዳ ካህናትና ምዕመናን ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ብፁዕ አባታችንም “ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር” በሚል ርዕስ አባታዊ ምክርና ቃለ ምዕዳን ሰጥተዋል።

በመቀጠልም የምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሠራተኞችን በመሰብሰብ ከዚህ በኋላ በህገ ቤተክርስቲያን መሠረት ሥራቸውን እንዲቀጥሉ መመሪያ በመስጠትና እስከ አሁን ያልተከፈላቸውን ደመወዝ በመከፈል በአዲስ መልክ ሥራ እንዲጀምሩ አድርገዋል። የሀገረ ስብከቱ ሠራተኞችም የብፁዕነታቸውን አባታዊ መመሪያ በመቀበል ዳግም ወደ ሀገረ ስብከታችን ስለመጡልን እግዚአብሔርን እያመሰገንን ሥራችንን ጀምረናል ብለዋል።

በመጨረሻም የኦሮሚያ ቤተክህነት እናደረጃለን እያሉ በሀገረ ስብከቱ የሚነቀሳቀሱትን ልዩ ልዩ ቡድኖች ወደ ህግ እንዲቀርቡ በተረገላቸው ጥሪ መሠረት አብዛኞቹ ወደ ቤተክርስቲያን አንድነት የቀረቡ ሲሆን የማሰላሰያ ጊዜ የሚፈልጉ ጥቂት ግለሰቦችንም ወደ በረቱ እንዲመለሱ ጥሪ ቀርቦላቸዋል። እንደ ሀገረ ስብከቱ ሕዝብ ግንኙነት ገለጻ ከሆነ ብፁዕነታቸው ለጥቅም ሲኖዶስ ከመመለሳቸው በፊት ሁሉም ተጠቃለው እንደሚገቡ የሚታመን ነው ተብሏል።

ዘገባውን ያደረሰን የሀገረ ስብከቱ ሕዝብ ግንኙነት ነው።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ኮሚቴው የማጣራት ሥራው የደረሰበትን ደረጃ በተመለከተ ለጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ ሪፖርት አቀረበ። Link to: ኮሚቴው የማጣራት ሥራው የደረሰበትን ደረጃ በተመለከተ ለጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ ሪፖርት አቀረበ። ኮሚቴው የማጣራት ሥራው የደረሰበትን ደረጃ በተመለከተ... Link to: ለሦስት ወራት በ6 አህጉረ ስብከት ሲካሄድ የነበረው ሐዋርያዊ ጉዞ ለቤተክርስቲያን ዘርፈ ብዙ ትርፎችን በማትረፍ ተጠናቀቀ Link to: ለሦስት ወራት በ6 አህጉረ ስብከት ሲካሄድ የነበረው ሐዋርያዊ ጉዞ ለቤተክርስቲያን ዘርፈ ብዙ ትርፎችን በማትረፍ ተጠናቀቀ ለሦስት ወራት በ6 አህጉረ ስብከት ሲካሄድ የነበረው...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top