የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሽገር ከተማ ሀገረ ስብከት በቡራዩ ገፈርሳ ጉዴ መልካ ኖኖ ክፍላተ ከተማ ስር ያሉት የቤተክርስቲያን አገልጋዮች የ2017 ዓ.ም የጥምቀት በዓል አከባበርን አስመልክቶ ወይይት አደረጉ።

December 26, 2024

ታሕሳስ 13 ቀን 2017ዓ.ም.
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሽገር ከተማ ሀገረ ስብከት በቡራዩ ገፈርሳ ጉጄ መልካ ኖኖ ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሥር የሚገኙት የአምስቱ አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች፣የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት የስብከተ ወንጌል ኃላፊዎች እና የማህበራት አመራሮች የ2017 ዓ.ም የጥምቀት በዓል አከባበር እንዴት መከበር እንዳለበት ከወዲው ሊከናወኑ በሚገቡ ጉዳዮች ዙርያ በዛሬው እለት ውይይት አድርጓል።

በኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ወቅትን ጠብቀው ከሚከበሩ ሃይማኖታዊ በዓላት አንዱ የጥምቀት በዓል ነው፡፡ እንደ ሊቃውትን ትርጉሜ ጥምቀት ማለት መነከር መዘቅ ፣መታጠብ ፣ መረጨት ማለት ነው፡፡በዓሉን የተለየ የሚያደርገው በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ታቦታት ጥር 10 ቀን ከሰዓት በኋላ ወደ ወንዝ ወርደው ለማረፊያ በተዘጋጀላቸው ቦታ ያድራሉ፡፡ ህዝበ ክርስቲያኑ በነቂስ ወጥቶ ታቦታቱን በማጀብ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ በመሄድ ያከብራሉ፡፡ ካህናት ሌሊቱን በማህሌት ስብሐተ እግዚአብሄር ሲያደርሱ ቆይተው የቅዳሴው ስነ ሥርዓት በመንፈቀ ሌሊት ተጀምሮ ይፈጸማል፡፡ ይሁን እንጂ ለበርካታ ዓመታት ይህንኑን ታሪካዊ በዓል ለማክበር ወደ አዲስ አበባ ገዳመ ኢየሱስ ሲወጡ የነበሩት ታቦታት በእግዚአብሔር አጋዥነት በድንግል ማርያም አማላጅነት በብፁዕ አባታችን አቡነ ሳዊሮስ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ የቅዱስ ሲኖዶስ ያላለሰለሰ ጥረት አዲስ የጥምቀት ማክበርያ ቦታ አግኝተን በመንግስት በኩል ከፍተኛ እገዛ እየተደረገልን በፍጹም ደስታ እያከበርን እንገኛለን። ከዚህው ጋር ተያይዞ ይህንን የ2017 ዓ.ም የጥምቀት በዓል አከባበር ከአምናው በተሻለ መልኩ ተዉቦ እና ደምቆ እንዲከበር ከወዲው ዝግጅት ስለ ሚያስፈልግ በዛሬው እለት ከአምስቱ አብያተ ክርስቲያናት ማለትም
1ኛ ከወይበላ ማኅደረ መለኮት ቅድስት ማርያምእና ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል
2ኛ ከፊሊ ዶሮ አቡነ ተክለ ሃይማኖትቤተክርስቲያን
3ኛ ከደብረ በረከት ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን
4ኛ ከአሸዋ ሜዳ ቅድስት ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን
5ኛ ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ቤተ ክርስቲያን የተወጣተጡ
የአድባራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች የስብከተ ወንጌል አገልጋዮች፣ የሰንበት ትምህርት ተወካዮች እና የማህበራት አመራሮች በቦታው ተገኝተው ቦታውን ከማጽዳት ጀምሮ እንዴት መከናወን እንዳለበት መክሮዋል።

የዚህ ውይይት ዋና አላማው የጥምቀት በዓል ሲመጣ የተለለያዩ ሀገራት ቱሪስቶች ፣ዲፕሎማቶች፣ አምባሳደሮች እና ባለስልጣናት በዓሉን ከእኛ ጋር ለማክበር ወደ ተቀደሰችው አገራችን ኢትዮጵያ እንደ ሚመጡ እዉን ነው ስለዚህ በዩኒስኮ ከተመዘገቡት የማይዳሰሱ ቅርሶች ጥምቀት አንዱ ቢሆንም በባለቤትነት ደረጃ ግን የምትመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስለ ሆነች ከወዲው መዘጋጀት እና የሚመጡትን እንግዶች ፍጹም በሆነ ክርስቲያናዊ መልክ ልንቀበላቸው ስለሚገባ ይህንንም ለማሳሰብ ጭምር ነው ተብሎአል። በዚህ እና መሰል ጉዳዮች ዙርያም ከቤቱ ሐሳብ አስተያየት የሰጡት ታላላቅ የገዳማት እና አድባራት አስተዳዳሪዎች የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት የማህበር ተወካዮች እና የሀገር ሽማግሌዎች ሲሆኑ በሰጡት አስተያየታቸውም ለሀገራችን ኢትዮጵያዉያን አንድነትና ተቻችሎ የመኖር ተምሳሌት ጥምቀት አንዱ ማሳያነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ወጣትም ከወዲው ለሰላም እና አንድነት ዘብ ሊቆም ይገባል፡፡ ከወዲው ከልጆቻችንን ጋር ሁነን የከተራና ጥምቀት በዓል በየአመቱ ሲመጣ ታቦታት ወደ ማረፊያቸው የሚሄዱበትንና የሚያርፉበትን ጎዳናዎች ለማጽዳት እና ለማስተካከል በተባበረ ክንድ ከመቼውም ጊዜ በላይ እንሰራለን ብለዋል። አክለውም ምዕመናኑ ፤ባህላቸውን፣ ሃይማኖታቸውን ሥርዓታቸውን እና ትውፊታቸውን ጠብቀው ከቀደምት አባቶቻቸው የተረከቡትን በረከት ለልጆቻቸውም ማስረከብ አለባቸው ብለዋል። የዛሬው የጥምቀት በዓል አከባበርን በተመለከት በታቦቱ ማክበርያ ቦታ የተደረገው ውይይት በፀሎት ተጀምሮ በስኬት ተጠናቋል ።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች
  • ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በሀገረ ስብከቱ ለካህናት የሚሰጠውን ሥልጠና በጸሎትና በቡራኬ አስጀመሩ።
  • ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ተገኝተው የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዐን አባቶችን መደበ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን የልዑካን ቡድን ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ለቤተክርስቲያኗ መሪ እቅድ ስኬት አገልጋይ ካህናትና ምእመናን የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተጠቆመ። Link to: ለቤተክርስቲያኗ መሪ እቅድ ስኬት አገልጋይ ካህናትና ምእመናን የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተጠቆመ። ለቤተክርስቲያኗ መሪ እቅድ ስኬት አገልጋይ ካህናትና... Link to: የአባታችን የጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በእዣ ወረዳ ቤተክህነት በገጨ ምዕራፈ ቅዱሳን ቅዱስ አቡነ ሳሙኤል ወቅዱስ ዕሩፋኤል ገዳም በድምቀት ተከብሮ ዋለ። Link to: የአባታችን የጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በእዣ ወረዳ ቤተክህነት በገጨ ምዕራፈ ቅዱሳን ቅዱስ አቡነ ሳሙኤል ወቅዱስ ዕሩፋኤል ገዳም በድምቀት ተከብሮ ዋለ። የአባታችን የጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ዓመታዊ ክብረ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top