የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በጠቅላይ ቤተክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ በተካሄደው የአቀባበል መርሐ ግብር ላይ ያስተላለፉት አባታዊ መልዕክት

June 3, 2025

ቅሩብ እግዚአብሔር ለየዋሃነ ልብ ወያድኀኖሙ ለትሑታነ መንፈስ እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል፡፡” መዝ 33፤ 18

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዘመነ ብሉይ የብሉይ ኪዳንን አስተምህሮ በሐዲስ ኪዳን ደግሞ በጃንደረባው አማካይነት ክርስትናን ከተቀበለች በኋላ የውስጥ እና የውጭ ችግሮች ቢኖሩም ዘመናትን በመሻገር ዶግማዋን እና ቀኖናዋን በመጠበቅ ለዛሬ ደርሳለች፡፡

ለዚህም የክርስትና እምነት ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚያሰጥ መንፈሳዊ ጉዞ በመሆኑ አባቶቻችን ሊቃውንት እና ብጹዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት አንድ ላይ በመሆን የሕዝቡ መንፈሳዊ ጉዞ ረዥም እንደሆነ በመገንዘብ እያንዳንዱ ሃይማኖታዊ ትሑፊት ለትውልዱ እንዲተላለፍ ለማድረግ ለቤተ ክርስቲያኒቷ በተሠራላት ሕግ መሠረት በየጊዜው የሚመሯትን አባቶች በመምረጥ ቤተ
ክርስቲያኒቷን እንዲመሩ የሚያደርጉ በመሆኑ በዚሁ መሠረት ባሳለፍነው የ2017 ዓ.ም የግንቦት ርክበ ካህናት ለቀጣይ ሦስት ዓመታት ቤተ ክርስቲያኒቷን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እንድንመራ አባቶች አደራ ሰጥተውናል፡፡

አደራው ግን እጅግ ከባድ እንደ መሆኑ መጠን አደራውን መወጣት እንድንችል የሁላችንም ኃላፊነት ከመቼውም ጊዜ በላይ ከባድ እና ጥብቅ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያኒቷን ለማገልገል የምናደርገው ጥረት በመንፈሳዊ መሠረት ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ያስፈልጋል ለዚሁም የአባቶቻችን ጸሎት እንደሚረዳን እናምናለን፡፡

አሁን በዚህ ዘመን ያለችቷ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ሁኔታዋ እናመንፈሳዊ አገልግሎቱ እንዲሁም ሁለንተናዊ የልማት ጉዞዋ እጅግ ውስብስብ እንደመሆኑ መጠን ይህን ለመወጣት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንደተጠቀሰው እኛም በትሑት ልብ ነህምያ የፈረሰችውን የኢየሩሳሌምን ቅጥር መልሶ ለመገንባት እኛ ልጆቹ ተነስተን እንሠራለን የሰማይ አባታችንም ያከናውንልናል በማለት የሥራው መጀመሪያ አደርጎ እንደተናገረው አሁንም ከዚህ ትምህርት በመውሰድ በጥልቅ እምነት በጸሎት በአስተዋይነት እና በቁርጠኝነት የሚቃወሙት እና እርሱ ቅጥሩን እንዳይሠራ የሚይፈልጉ ወገኖች ቢኖሩም እነርሱን ተሸግሮ የእግዚአብሔርን አጋዥነት ተስፋ በማድረግ የኢየሩሳሌምንቅጥር መልሶ እንደገነባ ሁሉ ዛሬም ያለብንን ችግር ፈትቶ ትውልዱ ከሚዘፈቅበት
ዓለማዊነት በማላቀቅ ቤተ ክርስቲያኒቷን ለትውልድ ለማሻገር እኔም ሆንኩኝ ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንደ ነህምያ መሥራት ይጠበቅብናል፡፡

ብጹዕ ወቅዱስ አባታችን
ብጹዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት

ነህምያ ከሁሉ በፊት ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ መንገዱን ለእግዚአብሔር በመስጠት ያሉ ችግሮችን በማጥናት የፈረሰውን ቅጥር በምሽት ዞሮ በማየት ቅጥሩ ለመፍረስ የቻለበትን ችግር ተረድቶ እንደገና እንዳይፈርስ ለማድረግ ለመገንባት እንደጀመረ ሁሉ ከእኛ ቀደም ብሎ በቦታው ላይ የነበሩት ኣባቶች ዘመናቸው በፈቀደላቸው መጠን እንደሠሩት እኛም ዛሬ ቤተ ክርስቲያን ወደ ፊት እንድትራመድ እንደ ቀድሞ ክብሯ እና ገናናነቷ እንዳትታይ ያደረጓትን ችግሮች በማጥናት እና በማየት በማቀድ መሥራት እንደሚገባን ይጠቁመናል፡፡

እርግጥ በነህምያ ዘመን የነበሩት አንዳንድ ወገኖቹ የእርሱን ሃሳብ እና የእግዚአብሔርን መንገድ ባለመረዳት ቅጥሩን መልሶ መገንባት እንደማያስፈልግ በጦቢያ እና በጌሼም የሚመሩ ተቃዋሚዎች ተነስተው በማስፈራራት እና በማፌዝ ሴራ ቢያሴሩበትም እርሱ ግን እጅ ባለመስጠት እኛ ልጆቹ ተነስተን
እንሠራለን የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል በማለት በጸሎት በንቃት እንደተቋቋማቸው ሁሉ እኛም በዙሪያችን የሚፈጠሩትን ችግሮች ለእግዚአብሔር በመስጠት ቤተ ክርስቲያናችንን በቁርጠኝነት መንፈሳዊ አስተዳደራዊ እና ማኀበራዊ ጉዳዮቿ በአንዳንድ ቢታዎች ላይ የሚታዩ አስተዳደራዊ ክፍተቶችን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚነሱ አለመግባባቶችን ፣ የንብረት አያያዝ ችግሮችን ፣በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ውስጥ የሚታዩ ክፍተቶችን በማከም በሁሉም አቅጣጫ የሚገኙት ምዕመናን ልጆቻችን ከቤተ ክርስቲያናቸው ጋር ያላቸውን መዳከም ፣ በተለያዩ ምክንያቶች እኛ የበለጠ ባለመሥራ
ታችን ከቤተ ክርስቲያኒቷ የሚርቁ እንዳይኖሩ ፈተናዎችን ለማሻገር ተግተን ልንሠራ ይጠበቅብናል ፡፡

ብጹዕ ወቅዱስ አባታችን
ብጹዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት

ቤተ ክርስቲያን አሁን ያለችበት ዘመን 21 ኛው ክፍለ ዘመን ላይ በመሆኑ እንደ ከዚህ ቀደሙ በዘልማድ ብቻ ልንጓዝ ስለማይቻል በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ እና ከቤተ ክርስቲያኒቱ ውጪ ያለውንም በመቃኘት ዕቅድ በማውጣት መንፈሳዊ አስተዳደራዊ ማኀበራዊ ክፍተቶችንም በመለየት ተጨባጭ የመፍትሔ ዕቅዶችን
በማውጣት በጥናት ላይ የተመሠረተ ውሳኔ ልትሠጥ ይገባታል፡፡

ቤተ ክርስቲያን በዚህ ዘመን በውስጥ ብቻ ሆነን ከምንሠራው በበለጠ ከውጭ ካሉትም ከተለያዩ አካላት ጋር ከመንግሥትም ጭምር በአስተዋይነት እና በጥበብ በመቅረብ ቤተ ክርስቲያኒቷ ተከብራ እንድትሻገር ካላደረግን የትውልድን ቅብብሎሽ ሊያደክምብን ይችላል፡፡ ስለሆነም ቤተ ክርስቲያን ከመንፈሳዊ አገልግሎቷ ጎን ለጎን አገልግሎት ለምትሰጣቸውም ሕዝብ በመራራት ልትደርስላቸው ስለሚገባት የቤተ ክርስቲያኗን የውስጥ ሰላም በማጠንከር በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ዜጎቿ ወደ ሰላም መንገድ እንዲመጡ መነጋገር እንዲችሉ የቤተ ክርስቲያን ድርሻዋ ከፍተኛ በመሆኑ እና ሊሠራ ስለሚገባ ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡

በመጨረሻም እግዚአብሔር ቢፈቅድ ባሉን ቀጣይ ሐዋሪያዊ የአገልግሎት ዘመናት በውስጥም ሆነ በውጭ ዓለማት የምትገኙ ሁሉ ለቤተ ክርስቲያን ዕድገት የሁላችን ድርሻ ትልቅ በመሆኑ ከፊትለፊታችን ያለውን የቤተ ክርስቲያን አንድነት ላይ ምላሽ ለመስጠት ሁላችሁም በተወከላችሁበት በተሰጣችሁ
ኃላፊነት ተግታችሁ እንድትሠሩ በአባታዊ ፍቅር አደራ እንላለን፡፡

ሰው በተሰጠው ኃላፊነት ላይ በትጋት በታማኝነት ፣ በቅንነት መሥራት የቤተ ክርስቲያኒቷን ሕልውና ከፍ ስለሚያደርግ በሥራ ቦታም ሆነ በግል ሕይወታችሁ ሰላምን እና መግባባትን ጠብቃችሁ እንድትሠሩ ግጭቶችን እና አለመግባባትን በሰላማዊ መንገድ መፍታት ወሳኝ እና ቤተ ክርሰቲያንም ከዚህ አትራፊ መሆንዋን ማሳሰብ እወዳለሁ፡፡

እግዚአብሔር ለልበ ቅኖች ቅርብ እንደመሆኑ መጠን ልባችንን ቅን በማድረግ ሕዝባችንን እና ቤተክርስቲያንን ለማገልገል በቅዱስ ሲኖዶስ የተጣለብንን አደራ መወጣት እንድንችል ከቅዱስ አባታችን መመሪያ በየጊዜው በመቀበል የምንሠራ ሲሆን ጸሎታቸውም ይርዳን እያልን በቤተ ክርስቲያንውስጥ ከአንድ ማዕድ እየተቋደስን በሃሰብ ልዩነቶች ውስጥ የሚገኙትን
በማቅረብ በሀገሪቷ ውስጥም በየቦታው በፖለቲካ ምክንያት የሚታዩትን አለመግባባት ተቀርፎ ሰላም እንዲመጣ ድርሻችንን በመወጣት ሕዝቡ ሰላማዊ አየር እንዲተነፍስ እንድናደርግ አምላከ ቅዱሳን እንዲረዳን በመጸለይ በሰላም በኢኮኖሚያዊ ማኀበራዊ የልማት ሥራዎች ከመንግሥት ጋርም ሆነ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር የቤተ ክርስቲያናችንን ዋና ተልዕኮ እና መብት በማስጠበቅ አብረን ለመሥራት ዝግጁ መሆናችንን እየገለጽን ፡፡

በዚህ በ2017 ዓ.ም የግንቦት ርክበ ካህናት ከእኔ ጋር የቤተ ክርስቲያኑን መንጋ እንድትጠብቁ የተሠየማችሁ የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊ ብጹዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ እና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን የተሸማችሁነትን ምልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ፡፡

የቅዱስነትዎ ጸሎት እና በረከት በሥራችን ስኬታማ እንድንሆን ይርዳን ፡፡

አመሰግናለሁ።
ግንቦት 25/09/2017 ዓ.ም

አባ ሳዊሮስ
የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብምዕራብ
ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/photo_2025-01-07_16-23-06-300x300-1.png 300 300 tc https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg tc2025-06-03 09:21:142025-06-03 09:21:14ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በጠቅላይ ቤተክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ በተካሄደው የአቀባበል መርሐ ግብር ላይ ያስተላለፉት አባታዊ መልዕክት
Search Search

Recent Posts

  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች
  • ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በሀገረ ስብከቱ ለካህናት የሚሰጠውን ሥልጠና በጸሎትና በቡራኬ አስጀመሩ።
  • ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ተገኝተው የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዐን አባቶችን መደበ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን የልዑካን ቡድን ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዛሬው ዕለት በተደረገው የአቀባበል ሥነሥርዓት ላይ ያስተላለፉት አባታዊ መልዕክት Link to: ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዛሬው ዕለት በተደረገው የአቀባበል ሥነሥርዓት ላይ ያስተላለፉት አባታዊ መልዕክት ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና... Link to: በብፁዕ አቡነ ኤልያስ የተመሠረተው “ዝክረ ነዳያን ዘአበዊነ” የበጎ አድራጎት ድርጅት ለዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ የ700,000 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ Link to: በብፁዕ አቡነ ኤልያስ የተመሠረተው “ዝክረ ነዳያን ዘአበዊነ” የበጎ አድራጎት ድርጅት ለዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ የ700,000 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ በብፁዕ አቡነ ኤልያስ የተመሠረተው “ዝክረ ነዳያን...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top