ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ከቤተክርስቲያናችን የኮሪደር ልማት ዐቢይ ኮሚቴ አባላት ጋር ተወያዩ።

ሰኔ ፪ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
****
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
=============
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የኮሪደር ልማት ዐቢይ ኮሚቴ አባላት ጋር ትውውቅና ውይይት አደረጉ።

የኮሪደር ልማት ዐቢይ ኮሚቴው በዚህ የትውውቅ መርሐ ግብር ላይ እስከ ዛሬ ድረስ ያከናወናቸውን ዋናዋና ተግባራትና በቀጣይ ሊያከናውናቸው በዕቅድ በያዛቸው ሥራዎች ዙሪያ ገለጻ ያደረገ ሲሆን በቀረበው ገለጻ ዙሪያም ውይይት ተደርጎበታል።

ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በዚሁ ጊዜ እስከ አሁን ለተከናወኑት ውጤታማ ሥራዎች አመስግነው ወደፊት ዐቢይ ኮሚቴው በሚከናወኑ ሥራዎች ዙሪያም ምክክርና ውይይት እየተደረገ የቤተክርስቲያንን ጥቅም በሚያስከብር አግባብ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር እንደሚሰራ እንደሚደረግ በመግለጽ የሥራ መመሪያ ተሰጥተዋል ።