የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

በ18 ወራት ውስጥ ተሠርቶ ለፍጻሜ የበቃው የሔንቤቾ ደብረ ፀሐይ ብዙኃን ማርያም አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የወላይታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ተባርኮ በዛሬው ዕለት ከፍተኛ የመንግሥት ባለ ሥልጣናት በተገኙበት ቅዳሴ ቤቱ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ።

February 10, 2026

የካቲት ፩/፳፻፲፰ ዓ/ም
እጨጌ የወላይታ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
+++++++++++++++++++++++++
በወላይታ ሀገረ ስብከት በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ቤተ ክህነት በሊቀ ኄራን ተክለ ወልድ አጥፉ አስተባባሪነት የተገነባው የሔንቤቾ ደብረ ፀሐይ ብዙኃን ማርያም አዲሱ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የወላይታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ጸሎት በትናንትናው ዕለት (በዋዜማው) የተባረከ ሲሆን በዛሬው ዕለት የቅዳሴ ቤቱ ክብረ በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል።

በቅዳሴ ቤቱ ክብረ በዓሉም ላይ ሊቀ ኄራን ተክለወልድ አጥናፉ የጠቅላይ ሚንስትሩ የፋይናንስ አማካሪ ሚኒስተር፣ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ፣ አቶ ገብረ መስቀል ጫላ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ክብርት ወ/ሮ እታገኝ ኃ/ማርያም የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ፣ አቶ ዳጋቶ ኩንቤ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮምሽን ዋና ኃላፊ እንዲሁም የፌደራል፣ የክልል፣ የዞን እና የከተማ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የገዳማት እና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ መምህራን፣ ካህናት፣ ዲያቆናት፣ የሰንበት ት/ቤት አገልጋይ ዘማርያን እና በርካታ ምዕመናን ተገኝተዋል።

በበዓሉም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እና የሶዶ ኦቶና ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ፈለገ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ያሬዳዊ ዝማሬ ያቀረቡ ሲሆን በተጋባዥ መምህራን ዕለቱን እና በዓሉን የተመለከተ ትምህርት ወንጌል በሰፊው ተሰጥቷል።

በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የወላይታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ክቡር ዲያቆን ተክለወልድ አጥናፉ የአባታቸውን ሊቀ መዘምራን አጥናፉን አደራ ተቀብለው ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመመካከር ርስታቸውን ከመስጠት ጀምሮ 18 ወራትን ብቻ የፈጀ የዚህ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ግንባታ ሥራ ላይ ቁልፍ ሚና በመጫወታቸው ከዛሬ ከየካቲት 01/2018 ዓ/ም ጀምሮ “ሊቀ ኄራን” ተክለወልድ አጥናፉ ተብለው እንዲጠሩ ሰይመዋል። በዚህ ሕንጻ ቤተ ክርስስቲያን የግንባታ ሥራ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ ያበረከቱትን ሁሉ አመስግነው ትምህርት፣ ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ ሰጥተው የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅጣጫ ሰጪነት እየታደሰ የሚገኘውን ዕድሜ ጠገቡን የወንጪ ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም ጎበኙ
  • ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ እየተገነባ ያለውን ዓለም አቀፍ የሥብሰባ አዳራሽ ጎበኙ
  • በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ተጀምሮ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ትጋት ለፍጻሜ የበቃው ባለ 480 ካሬ ሜትር ሁለገብ ሕንጻ ተመረቀ
  • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
  • ቅዱስ ሲኖዶስ በልማትና ዘመናዊ አሠራር ላይ ያተኮሩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ለ6 ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን የ2018 ዓ.ም የርክበ ካህናት ጉባኤውን አጠናቀቀ

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የቤተ ክርስቲያን ነገዎችን የተሻለ ለማድረግ ሥልጠና አስፈላጊ ነው ሲሉ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ ገለጹ። Link to: የቤተ ክርስቲያን ነገዎችን የተሻለ ለማድረግ ሥልጠና አስፈላጊ ነው ሲሉ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ ገለጹ። የቤተ ክርስቲያን ነገዎችን የተሻለ ለማድረግ ሥልጠና... Link to: ቤተክርስቲያን ለምታስገነባቸው ሕንጻዎች በልዩልዩ ዘርፍ ሙያዊ ድጋፍ ላደረረጉ ባለሙያዎች የምስጋና መርሐ ግብር ተካሔደ። Link to: ቤተክርስቲያን ለምታስገነባቸው ሕንጻዎች በልዩልዩ ዘርፍ ሙያዊ ድጋፍ ላደረረጉ ባለሙያዎች የምስጋና መርሐ ግብር ተካሔደ። ቤተክርስቲያን ለምታስገነባቸው ሕንጻዎች በልዩልዩ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top